መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / ሞዛይክ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር
mosaic-construction

ሞዛይክ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር

ሞዛይክ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተመሠረተው በአቶ ሳሙኤል ገዛህኝ እና በአቶ ጌትነት ካሳ መስከረም 2009 ዓ.ም ነው። ድርጅቱ ደረጃ ስምንት ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ሲሆን የሚቀበላቸውን ሥራዎችን በጊዜ ገደባቸው እና በጥራት ሠርቶ ያስረክባል።

ድርጅቱ የሚሠራቸው ሥራዎች

  • የግንባታ ሥራዎች
  • የፊኒሽንግ ሥራዎች
  • የሳይት ሥራዎች
  • የግንብ ተኩስ ሥራዎች
  • የቁፋሮ ሥራዎች
  • የኮብል ስቶን ነጠፋ ሥራ
  • የፓርኪንግ ማቆሚያዎች እና አጠቃላይ የኮንስትራክሽን ሥራዎችን በጥራት ይሠራል

ድርጅቱ ሁለት ፎቅ ሕንጻ ሙሉ ሥራውን በስድስት ወር አጠናቆ የማስረከብ አቅም አለም። በገንዘብ ደግሞ አሥራ ስምንት ሚሊዮን ብር ድረስ የሚደርሱ አጠቃላይ የኮንስትራክሽን ሥራዎችን ይሠራል።

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

አቶ ሳሙኤል ወደ ኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩበት ምክንያት ትምሕርታቸውን የተማሩት በሲቪል ኢንጂነሪንግ ስለሆነ ነው። በዚህም ሙያ ለአንድ አመት ተኩል  በፕሮጀክት ማናጀር፣ ሳይት መሀንዲስ ሥራዎች ላይ ተቀጥረው ሠርተዋል፤ በዚህም ወሳኝ ልምዶችን አግኝተዋል። በመቀጠልም ዘርፉ አዋጭ ስለሆነ እና የግል ሥራ የተሻለ ክፍያ እንደሚኖረው በማሰብ ከጓደኛቸው ጋር በመሆን ሞዛይክ ኮንስትራክሽን ድርጅትን መሥርተዋል።

ድርጅቱ በአሁን ሰዓት ለሁለት ቋሚ እና ከሃያ እስከ ሠላሳ ለሚደርሱ ጊዜያዊ ሠራተኞች የሥራ እድል ፈጥሮ አየሠራ ነው። ይህ ድርጅት ሲመሠረት በአሥራ አምስት ሺህ ብር ካፒታል ሲሆን አሁን ካፒታሉ አምስት መቶ ሺህ ብር ደርሷል።

ሞዛይክ ኮንስትራክሽን ሥራዎችን የሚሠራው አንድ ከመንግስት ወረፋ በመጠበቅ ሲሆን ሁለት ደግሞ በሰው በሰው ሰብ ኮንትራክት ሥራዎችን በመውሰድ ነው። እንዲሁም የከፍታን ፓኬጅ በመጠቀም ጨረታዎችን ይከታተላል። አንድ ጨረታ ጃዊ መተከል አካባቢ አሸንፎ የነበረ ሲሆን በነበረው የጸጥታ ችግር ሥራው ሳይሠራ ቀርቷል።

ድርጅቱ ከተመሠረተ አምስት ዓመታትን አስቆጥሯል፤ በዚህ ጊዜ ውስጥ ችግሮች ሲፈጠሩ በተለያዩ መንገዶች እየፈታ ነው የመጣው። ከሚጠቀማቸው መንገዶች መካከል የጓደኛ እና ቤተሰብ ድጋፍ፣ በጣም ሥራ ሲጠፋ ደግሞ ሌሎች ሥራዎችን በመሥራት ድርጅቱን በመደጎም እና በተገኙት አጋጣሚዎች ደግሞ ሥራ በመፈለግ እና በመሥራት ነው።

የኮቪድ ተፅዕኖ

የኮቪድ ተፅዕኖ ከባድ ነበር። በኮቪድ ምክንያት ድርጅቱ የያዛቸው ሥራዎች በጀት የለም ተብሎ ተቋርጠው ነበር፤ እንዲሁም በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ እንደልብ ሥራ መሥራት ባለመቻሉ ተቋርጦ ነበር። በዚህም ምክንያት አቶ ሳሙኤል ለሦስት ወር ወደ አፋር ክልል በመሄድ ሌሎች ሥራዎችን በመሥራት የኮቪድን ጊዜ አሳልፈውታል። ከዚህ ጋር ተያይዞ በጦርነት ምክንያት በጀት የለም ተብሎ የክፍያ መጓተት እና አንድ ሚሊዮን ብር ሲጠየቅ የለም ተብሎ ግማሽ ክፍያ ብቻ የሚለቀቀው። ለሥራ ማስኬጃ የሚያስፈልጉ ነገሮች በአስፈላጊው የጊዜ ገደብ አለመከናወን ከሚጠቀሱ ወቅታዊ ችግሮች አንዱ ነው።

ምክር እና እቅድ

ድርጅቱ በአምስት ዓመት ወደ ደረጃ ሰባት ኮንትራክተር ለማደግ እቅድ የነበረው ቢሆንም በተቀየረው ሕግ መሠረት ደረጃ ሰባት ለመግባት የሰባት አመት የሥራ ልምድ ያስፈልጋል በዚህ ምክንያት በቀጣይ አመት የሰባት አመት የሥራ ልምድ ስለሚኖረው ደረጃ ሰባት ለመግባት እና በሚቀጥሉት ዐሥር አመታት ከደረጃ አንድ እስከ ደረጃ ሥስት ለመድረስ እቅድ አለው።

አዲስ ወደ ኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚገቡ ሰዎች የማቴሪያል፣ ሰዓት እና ገንዘብ አጠቃቀም አውቀው መግባት አለባቸው፤ ይህን ደግሞ በልምድ ነው ማዳበር የሚችሉት። ሌላው ደግሞ በመጀመሪያ ጊዜ ላይ በጣም አሰልቺ ነገሮች ሊኖሩ ስለሚችሉ ራሳቸውን አዘጋጅተው ቢገቡ ጥሩ ነው። በጊዜ ሂደት የገንዘብ እና የጊዜ አጠቃቀም እንዲሁም የሠራተኛ አጠቃቀም እይተሻሻለ ይመጣል፤ የኛም ድርጅት እንደዚህ ነው የተማረው። በመጨረሻ ደግሞ የመንግስትን አሠራር ማወቅ አለባቸው፤ ለምሳሌ ቤቶች ልማት ለመሥራት ያሉት መስፈርቶች ምን ያህል ናችው? ቤቶች ልማት አራት ሚሊዮን ብር ድረስ ሥራ መሥራት ይቻላል፤ እንኝህንና ሌሎች ነገሮችን ራሳቸውን ማስተማር አለባቸው ብለው ይመክራሉ።

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …