መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / ነቢያት አስረሳኸኝ እንጨት እና ብረታ ብረት

ነቢያት አስረሳኸኝ እንጨት እና ብረታ ብረት

ነቢያት አስረሳኸኝ እንጨት እና ብረታ ብረት የተመሠረተው በ 1998 ዓ.ም ነው። የተመሠረተውም በአቶ ነብያት እና ዘጠኝ መሥራች አባላት ነበር። ነገር ግን በተፈጠሩ የተለያዩ አለመግባባቶች እና በነበሩ ብዙ ፈታኝ ሁኔታዎች አንዳንድ አባላት የሥራ ቦታ በመቀየራቸው፣ አንዳንድ አባላት ደግሞ የተሻለ እድል በመፈለጋቸው እና በተለያዩ ምክንያቶች በአሁን ጊዜ ሦስት አባላት ብቻ በድርጅቱ ውስጥ ይገኛሉ። ድርጅቱ በአምስት ሺህ ብር ካፒታል ነበር ሥራ የጀመረው።

እድገት

በአሁን ጊዜ ለሁለት ቋሚ እና ለአሥር ጊዜያዊ ሠራተኞች የሥራ እድል በመፍጠር እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ነቢያት አስረሳኸኝ እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ ሥስት ሺህ ወንበሮችን ከአንድ እስከ ሁለት ወር ጊዜ ውስጥ አምርቶ የማስረከብ አቅም አለው። ድርጅቱ ጨረታዎችን በማሸነፍ ከትልቅ ድርጅቶች ጋር አብሮ ሠርቷል። ለምሳሌ ንግድ ባንክ፣ ሕብረት ባንክ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ከብዙ አንጋፋ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ብዙ ሥራዎች ሠርቷል።

ድርጅቱ የሚያመርታቸው ምርቶች

  • የተማሪዎች አልጋ እና ወንበሮች
  • የቤት እና የቢሮ ፈርኒቸሮች
  • የተለያዩ የዩኒቨርስቲ ወንበሮች
  • የህጻናት የመመገቢያ ጠረጴዛዎች
  • ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ ታንከሮች

 

 

 

 

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

አቶ ነብያት ወደ እንጨት እና ብረታ ብረት ዘርፍ ሊገቡ የቻሉት በትምሕርት እና በሥራ ያካበቱት ልምድ እንደሆነ ተናግረዋል። ይህን ድርጅት ከመመሥረታቸው በፊት የሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ተማሪ ነበሩ። ትምህርታቸውን እንደጨረሱ ዳን ሊፍት እና ሌላም ድርጅት ጋር ተቀጥረው ለሁለት አመት ሠርተዋል። በድርጅቱ ውስጥም ሲሠሩ  የሊፍት፣ ቬንትሌሽን እና ኤር ኮንዲሽኒንግ ሲስተም አሠራር በበቂ ሁኔታ ተምረዋል። ይህም ልምድ ድርጅታቸውን ሲመሠርቱ ጥሩ መሠረት እንዲኖረው እና ድርጅቱ ውጤታማ እንዲሆን አድርጎታል።

አቶ ነብያት የግላቸውን ሥራ መሥራት የመጀመሩት አንድ የኮንትራት ሥራ ባገኙበት አጋጣሚ ሥራውን በሚገባ በማጠናቀቅ ስለቻሉ በዚሁ አጋጣሚ የራሳቸውን ሥራ ሊጀምሩ ችለዋል።

ድርጅቱ ከሚታወቅባቸው ምርቶች የብረት ሥራ በዋናነት ይጠቀሳል፤ ይህም ሊሆን የቻለው የአቶ ነብያት የሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ትምሕርት እና የዐሥራ አምስት አመት የሥራ ልምድ ውጤት ነው።

ድርጅቱ ሥራ የሚያገኘው ጨረታዎች ላይ በመሳተፍ ነው። በአንድ አመት አንድ እና ሁለት ጨረታ ካሸነፈ በቂ ነው። እንደ ሥራው አይነት ደግሞ ይለያያል። አንዳንድ ሥራዎች አመት ሊፈጁ ይችላሉ አንዳንድ ሥራዎች ደግሞ ወራትን ሊፈጁ ይችላሉ። ከዚህም በተጨማሪ በሰው በሰው ሥራ እያገኘም ይሠራል። ድርጅቱ የ2merkato.com አገልግሎት በመጠቀም ብዙ ጨረታዎችን አሸፏል። ለምሳሌ ጎንደር ዩነቨርስቲ፣ አርባምንጭ ዩኒቨርስቲ እና ሌሎችም የ2merkato.com ጨረታ በመጠቀም ቢያንስ አምስት ጨረታዎችን የማሸነፍ አድል አግኝቷል። የድርጅቱ መሥራች አቶ ነብያት በ2merkato.com ጨረታዎችን በነፃ መከታተል እንደሚችሉ ስለሚያውቁ ይከታተላሉ ለምሳሌ ጂአይዜድ(GIZ), ቴሌ(TELE) እና ዓለማቀፍ ጨረታዎችን በዌብሳይቱ ይከታተላሉ። እሳቸው የ2merkato.com አገልግሎት ከስድስት ዐመት በላይ ተጠቅመዋል። በመጠቀማቸው በቂ ልምድ አካብተዋል ማን ምን እንደሚፈልግ? ማን ምን አይነት ጨረታ እንደሚያወጣ? ምን ያህል አቅም ጨረታው ላይ ለመሳተፍ እንደሚያስፈልግ? እና የመሳሰሉትን እውቀቶች ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ዋናውን (የመግቢያውን) በማየት ብቻ ምን አይነት ጨረታ እንደሆነ ማወቅ ይችላሉ።

አቶ ነብያት የግል ሥራ ጥቅምች እና ጉዳቶችን እንደሚከተለው አስረድተዋል። የግል ሥራ የጊዜ ነፃነት አለው። መሠራት ካላበት ደግሞ ማታም ሌሊትም መሥራት ይቻላል። በመቀጠል ውሳኔ ላይ ራስህ መወሰን ትችላለህ ይህ ደግሞ ውሳኔ ብዙ አባላት ቢኖሩ ውሳኔ ለመወሰን የሚጓተተውን ጊዜ ይቀንሳል። የራስ ሥራ የሰዓት እና የገንዘብ ነፃነት አለው። ነገር ግን ሁሉ ነገር አልጋ በአልጋ አይደለም አንዳንዴ አንድ ሥራ አልቆ ለማስረከብ ሲደርስ ተቀባዩ አካል አልቀበልም ይላል። ሌላው ደግሞ ለሥራ ወደ ክፍለ ሀገር ስትሔድ ማኅብረሰቡን መምሰል ይኖርብሃል፤ እንጂ ይህ ቦታ እንዲህ አይነት የማይመች ነገር ስላለ አልሄድም ወይም አይመቸኝም ብለህ ብትቀር የምትጎዳው አንተ ነህ። ሌላው ተፅዕኖ ደግሞ የማኅበረሰቡ ነው። እንዳንድ ሰው ነፃ እንደሆንክ ወይም የራስህን ሥራ እንደምትሠራ ስለሚያውቅ ይመጣል በይሉኝታ ከእንግዳጋ ሆነህ ለመሥራት ያሰብከውን ሥራ ሳትሠራ ጊዜ ያልፋል። እንዲሁም አንዳንድ ኃላፊነቶች የአንተ ሊሆኑ ይችላሉ። ስለዚህ እንዲህ አይነት ነገር እንዳይፈጠር በሥራ ሰዓት ልክ እንደተቀጣሪ ሆኖ መሥራት መቻል አለብህ ሲሉ ሃሳባቸውን አካፍለዋል የድርጅቱ መሥራች።

የኮቪድ ተፅዕኖ

ኮቪድ በጣም ከባድ ነበር ምክንያቱም በብረት ይተላለፋል የሚል የተሳሳተ አመለካከት በማኅበረሰቡ ላይ ነበር። የተባለው ብዙ ንክኪ የሚበዛባቸው ነገሮች(ብረቶች) ላይ ለምሳሌ የበር እጀታዎች፣ ገንዘብ፣ የሊፍት ቁልፎች እና የደረጃ መደገፊያዎች ንክኪ የሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ ነበር፤ ግን የማኅበረሰቡ አመላካከት ይህ ስላልነበር ሠራተኛ በሙሉ ሥራ አቁሞ ነበር። ይህ ደግሞ ድርጅቱ የኢትዮ ቴሌኮምን ጨረታ አሸንፎ በነበረት ወቅት ነበር የተከሰተው። ትልቅ የሥራ እድል ድርጅቱ አጥቷል። ይህ እንዳለ ሆኖ አብሮ የመጣ ጥሩ ነገርም ነበር፤ ወረርሽኙ አንድ አመት ይቆያል ተብሎ ታስቦ ስለነበር ኤምኤስኤፍ የሚባል የስፔን (MSF-Spain) የእንቅስቃሴ መታገድ ለአንድ አመት ሊቆይ ስለሚችል በማለት ለድርጅቱ መኪና ማቆሚያ ሼድ ሰርቶ እንዲጠቀሙበት አድርጓል። ይህ አብሮ የመጣ ጥሩ አጋጣሚ ነው።

ምክር

የእንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ ከቴክኖሎጂ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው ይህም ዘመናዊ ማሽን ካለህ በትንሽ ጊዜ ብዙ መሥራት ትችላለህ። ብዙ አዳዲስ ዘመናዊ ማሽኖች አሉ። እነሱን መጠቀም የሥራውን ጥራት እንዲጨምር እና ጊዜ እንዲቆጠብ ያደርጋል። ሌላው የቴክኖሎጂ ጥቅም ደግሞ ድሮ ድሮ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ነበር የሚወጣው አሁን ግን የትም ቦታ ሆኖነን በእጅ ስልካችች ጋዜጣ ሳናገላብ ቀጥታ ሥራችን መከታተል እንችላለን። ከዚህ በላይ የቴክኖጂ ጥቅም የለም። ስለዚህ ቴክኖሎጂ መጠቀም በጣም በጣም ወሳኝ ነው ሲሉ ምክራቸውን አስተላልፈዋል አቶ ነቢያት።

እንደ ተጨማሪ የሚከተለውን አክለዋል። ትስስር ማለት ብዙ አይነት ነው ለምሳሌ አንድ ሥራ ማሠራት የሚፈልግ ድርጅት የአንድን ድርጅት ማስታወቂያ አይቶ ሲመጣ ያድርጅት ቅድሚያ ክፍያ ሊሰጥ ይችላል። ለምሳሌ የ2merkato.com አግልግሎት በሆነው ከፍታ በኩል ያለውን የድርጅት ማስታወቂያ ማስታወቂያ ላይ አይቶ ከመጣ አመኔታ ስለሚኖረው ቅድሚያ ክፍያ ሊከፍል ይችላል፤ ይህ ደግሞ በጣም ጠቃሚ ነው።

አዲስ የሚገቡ ሰዎች የመንግሥትን አሠራር ማወቅ አለባቸው። ግብር በጊዜው መክፈል አለባቸው ይህም የእፎይታ ጊዜ ይሠጣቸዋል። የሂሳብ ሥራ (ኦዲት) ማድረግ አለባቸው። ዘወትር ቴክኒካል ነገር ላይ ብቻ ማተኮር ሳይሆን የመንግሥትን ሕጋዊ አሠራር ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው። ለምሳሌ አንድ ተማራቂ ተማሪ ይህን ካላወቀ አንድ ዓመት ሊሠራ ይችላል፤ አንድ ዓመቱ ሲያልቅ ግን ይዘጋል። ለምን? ምክንያቱም በሥራው ዓለም እንዴት መሥራት እንዳለበት ግንዛቤው ስለሌለው። ስለዚህ የሆነ ዓመት ተቀጥሮ ቢሠራ በጣም ይመረጣል፤ ይህም ደግሞ አንድ ወሳኝ የማኔጅመንት ልምድ እንዲኖረው ያደርጋል።  አንድ ሰው በብረት እና እንጨት ዘርፍ ለመሠማራት መሠረታዊ ቀላል የእጅ ማሽኖች ግዴታ ያስፈልጉታል። በጣም ከትንሹ ቢጀምር የቤት ኪራይ ከሌለበት ቢያንስ ሀምሳ ሺህ ብር ያስፈልጋል። ማቴርያል መግዛት አለበት፣ ቀላል የሚባሉ ወጭዎች ለጀማሪ ትልቅ ወጭዎች ናቸው። ይህ ማለት የግድ ብዙ ገንዘብ ይኑረው ማለት አይደለም። ምክንያቱም ብዙ ገንዘብ ይዘው ሙያው ከሌለ ኪሳራ ነው የሚሆነው። ስለዚህ የሙያው እውቀት ሊኖር ይገባል፤ በመቀጠል ደግሞ መሠረታዊ የሚባሉ ቀላል የእጅ መሣሪያዎችን ማሟላት ይገባል ሲሉ ምክራቸውን አስተላልፈዋል።

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …