መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / “ደንበኞችን ማርካት ዋና የቢዝነስ የማእዘን ራስ ነው”
leather-product

“ደንበኞችን ማርካት ዋና የቢዝነስ የማእዘን ራስ ነው”

ሳሙኤል ደባልቄ የሌዘር ሥራ

ሳሚ የሌዘር ሥራ የተመሰረተው በ 2007 ዓ.ም ሲሆን፣ ድርጅቱ የምርት ሥራ የጀመረው በ2008 ዓ.ም ነው። የድርጅቱ መስራች የሆነው አቶ ሳሙኤል ሲያስረዳ በሙያው የትምህርት እንዲሁም የሥራ ልምድ በመቅሰም ወደ ድርጅቱ ምስረታ እንደመጣ ሳሚ ይናገራል። ሳሚ ሌዘር ሲመሰረት በአንድ ማሽን በራሱ መኖሪያ ቤት ውስጥ ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት ሁለት ቋሚ ሠራተኞች እና ከሶስት እስከ አምስት ጊዜያዊ ሠራተኞች እንዲሁም አምስት ማሽኖች እንዳሉት ታውቋል።

አቶ ሳሙኤል የሌዘር ሙያን የመረጠበትን ምክንያት ሲገልጽ የሰለጠነው በሌዘር ሙያ ቢሆንም ከዚሀ ድርጅት መመስረት በፊት ሌላ ተያያዥ ሥራዎችን ይሠራ እንደነበር አስረድቷል። ይህ የሥራ እድል ከዲዛይነሮች ጋር የመሥራት አጋጣሚን አንደፈጠረለት ይናገራል። ይህ እድል እንዴት ደንበኞችን ማቆየት እንዳለበት፤ ይህም የሚፈልጉትን ምርት በጥራት ማቅረብ እንዲችል እንዳስተማረው ይናገራል።

ሳሚ ሌዘር ሥራ አጠቃላይ የሌዘር ሥራዎችን በጥራት እንደ ደንበኛው ፍላጎት ያመርታል። ሳሚ ሌዘር ሥራ ከሚያመርታቸው ምርቶች ውስጥ አጠቃላይ የቆዳ ቦርሳዎች ሥራ እንዲሁም ቀላል እና ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ያላቸውን የቆዳ ውጤቶች ያመርታል። በተጨማሪ ቀላል እስክርቢቶ መያዣ፣ የወንዶች ቀበቶ፣ ዋሌት፣ የጀርባ ቦርሳ፣ የሴቶች ቦርሳ ከትንሽ እስከ ትልቅ በማንኛውም ዲዛይን እንደ ደንበኛው ፍላጎት ያመርታል። እንዲሁም የተለያዩ ለየት ያሉ የቆዳ ውጤቶች ለምሳሌ የውሻ መያዣ ኮላር (Collar)፣ የፈረስ መያዣ እና አጠቃላይ የቆዳ ሥራዎች ይሠራል።leather-bag

ሳሚ ሌዘር ሥራ ከተመሰረት ሁለት ዓመት ሆኖታል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ግን “ነገሮች አልጋ በአልጋ ነበሩ ማለት አይደለም” የሚለው ሳሚ ለአምስት ወር በግል ምክያንት ሥራው ተቋርጦ እንደነበር ይናገራል። በአሁኑ ወቅት “ቢዝነሱ የተሻለ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ይህን ስል ግን ገና ብዙ እንደሚቀረኝ አውቃለሁ” ይላል ሳሚ። “ሁላችንም ጥሩ ሥራ ልንሠራ እንችላለን እኔ ግን የምሠራው ደንበኞቼን ለማስደሰት ነው። በዚህ በኩል ደሞ ጥሩ ሥራ እየሠራሁ ነው ብዬ አምናለሁ። ደንበኛ አያያዝ ጥሩ መሆን አለብን፤ እኔ ደሞ ጥሩ ነኝ።  የሥራ ቦታ አካባቢ ሠራተኛ ገብቶ ሲሠራ ከራሱ ጋር ንግግር እያደረገ የሚሰራበት የሥራ አካባቢ መፍጠር ለሥራው በጣም ጠቀሜታ አለው” ሲል አቶ ሳሚ ተናግሯል።

ሥራው ሲጀመር ከቤት በአንድ ማሽን የተጀመረ ሥራ ነበር፤ ቀስ በቀስ ነው አሁን ላለበት አምስት ማሽኖች የደረሰው። ይህም ውጤት የመጣው ጠንክሮ በመሠራቱ ነው። “የግል ሥራ መሥራት ጥቅሙ ቤትም፣ ሥራ ቦታም ዲዛይን ወርክሾፕ አለኝ፤ ይህ ማለት የዲዛይን ሃሳብ ሲመጣ ቤትም ከሆንኩ ቤት፤ ሥራ ቦታም ከሆኩ ሥራ ቦታ ለመሥራት አችላለሁ። ጥሩ ለመሥራት ማሽን ስለበዛ ወይም ስላነሰ ሳይሆን የራስ የሥራ ፈጠራ ቁልፍ ሚና አለው” ይላል ሳሚ።

ሳሚ የግል ቢዝነስ ከሚኖሩት ጥቅሞች ውስጥ የሚከተሉትን አክሏል፦  የምትጠቀማቸው ሰዓቶች ይኖሩሃል፤ የራስ የሚለው ሃሳብ ራሱ ለሥራው ሙሉ አቅምህን እንድትሰጥ ያደርግሀል፤ ይህ ደግሞ የተሻለ ውጤት ያስገኛል።

ሳሚ ድርጅቱን ወደፊት ለማራመድ የጠቀመው የትምህርት ዝግጁነት አንዱ እና ዋናው ሲሆን በመቀጠልም በማንኛውም የሥራ ቦታ ራስን ማላመድ መቻል ወሳኝ ነገር ነው።

ሳሚ ሌዘር ዘመናዊ ምርቶችን ለማምረት ኢንተርኔትን መጠቀም ከጊዜው ጋር ተራማጅ ሥራዎች ለመሥራት እና እንዴት ነው የሚሠሩት፣ በምን መልኩ ቢሠሩ የተሻሉ ይሆናሉ የሚለውን አጠቃላይ ጥያቄ ለመመለስ እንዲሁም ራስን ለማሳደግ ዋና መንገድ እንደሆነ ይናገራል።

በኮቪድ ምክንያት ትዕዛዞች እንደዘገዩ፣ ምክያቱም አብዛኞቹ የሳሚ ሌዘር ደንበኞች የውጭ ዜጎች በመሆናቸው አጠቃላይ የእንቅስቃሴዎች መታገድ ሥራውን አቀዝቅዞበታል። ሆኖም ሳሚ ሌዘር ምርቶቹን በተለያዩ መንገዶች ማስተዋወቁ በዚህ ፈታኝ ጊዜ እገዛ እንዳረገለት አስረድቷል። ሳሚ ሌዘር ከሚጠቀማቸው ማስታወቂያዎች መካከል ባዛር እና ሁለት የጉዞ መፅሔቶች ላይ አስተዋውቋል። ምርት ማስተዋወቅ በጣም ወሳኝ እና ጠቃሚ እንደ ሆነ ሳሚ አስረድቷል።

ሳሚ የከፍታ አገልግሎትን በመጠቀም 2merkato ላይ የሚገኙ በመላ ኢትዮጵያ የሚወጡ ጨረታዎችn እየተከታተለ እንደሆነ በከፍታ አገልግሎት ጨረታዎች ላይ እየተሳተፈ እንደሆነ አስረድቷል።

ሳሚ ሌዘር ሥራዎች ከአምስት አመት በኋላ የሚያመርታቸውን ምርቶች በብዛት እና በጥራት ለኤክስፖርት የማቅረብ ዓላማ እንዳለው ድርጅት ሳሚ ያስረዳል።

አዲስ ቢዝነስ ለሚጀምሩ ሰዎች የሚሠሩትን ሥራ በጥራት መሥራት አለባቸው፤ እንደሚሠሩም ማመን አለባቸው ብዬ አስባለሁ ይላል ሳሚ። ከዚህም ጋር ቴክኖሎጂ መጠቀም በጣም አስፈላጊ ነው፡- ራስን ለማሳደግ እና ምርትን ለማስተዋወቅ። ስለዚህ ማንኛውም አዲስ ቢዝነስ የሚጀምር ሰው ቴክኖሎጂን እንዲጠቀም ሳሚ ይመክራል።

የሳሚ ሌዘር ሙሉ ፕሮፋይልን ለማግኘት፦ Samuel Debalke Demse Leather Manufacturing | ሳሙኤል ደባልቄ ደምሴ የቆዳ ውጤቶች

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …