በምሥረታ ወይም ጀማሪ ደረጃ ላይ የሚገኙ (ገና በመቋቋም ላይ የሚገኙ ወይም ለመቋቋም የሚያስቡ) ኢንተርፕራይዞች፣ የሚያገኙት ድጋፍ ደግሞ እንደሚከተለው ነው።
በምሥረታ ወይም ጀማሪ (Start-up) ደረጃ የሚሰጥ ድጋፍ
እንዲህ ዓይነቱ ድጋፍ የሚያካትተው ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ለመመስረት በመፈለግ በማኅበር እና በግለሰብ በህግ አግባብ ተደራጅተው የራሳቸውን ቁጠባና ከተለያዩ ፋይናንስ ተቋማት ብድር በመውሰድ ወደ ሥራ የገቡትን ነው።
የምስረታ/ጀማሪ ደረጃ ኢንተርፕራይዙ ህጋዊ አቋም ይዞ ማምረትና አገልግሎት መስጠት የሚጀምርበት ደረጃ ነው። በምስረታ/ጀምሪ ደረጃ ላይ ላለ ኢንተርፕራይዝ መንግስት የሚሰጣቸው የድጋፍ ዓይነቶች የሚከተሉት ናቸው፡-
- የመነሻ ካፒታል ማመቻቸት
- ኢንተርፕራይዝ ለመመስረት ፍላጎቱ ያላቸውን በራሳቸው እንዲቆጥቡ ማበረታታትና የራሳቸው ቁጠባ ሲኖራቸው ለብድር ቅድሚያ እንዲያገኙ ማመቻቸት
- ህጋዊ አቋም እንዲኖራቸው ማብቃት
- በምስረታ ላይ ያሉ ኢንተርፕራይዞች በመረጡት ህጋዊ አደረጃጀት ተጠቅመው እንዲቋቋሙ መደገፍ
- በሁሉም ዓይነት ዘርፍ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች የህጋዊ ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እንዲያገኙ ማድረግ
- የቢዝነስ ሥራ አመራር፣ ኧንተርፕረነርሺፕና ሂሳብ አያያዝ ብቃት ማሳደግ
- ኢንተርፕራይዞቹ መሠረታዊ የቢዝነስ ሥራ አመራርና ኧንተርፕረነርሺፕ ክህሎት እንዲኖራቸው ማስቻል
- መሠረታዊ የሂሳብ አያያዝ ስልጠናዎችን መስጠትና ሞዴል የሂሳብ አያያዝ ማኑዋሎችን አዘጋጅቶ መስጠት
- የክህሎትና የቴክኒክ ስልጠናዎችን መስጠት