ቪዥን ፈንድ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአነስተኛ ገንዘብ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ 40/1988 የተቋቋመ አንጋፋ እና አስተማማኝ የገንዘብ ተቋም ነው። ተቋሙ በ91 አገልግሎት መስጫ የቅርንጫፍ ቢሮዎቹ አማካኝነት ተደራሽ እና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። ተቋሙ በአሁኑ ሰዓት በጥቅሉ 734,226 በላይ የብድር እና የቁጠባ ደንበኞችን ለማፍራት የቻለ ሲሆን የሰጠው ብድር መጠን 2.5 ቢልዮን ብር እንዲሁም የመደበኛ ቁጠባ 1 ቢልዮን ብር በላይ ደርሷል።
የተቋሙ ራዕይ
እያንዳንዱ ልጅ ምሉዕ ህይወት እንዲኖር ማስቻል ሲሆን ራዕያችን እያንዳንዱ ልብ ይህን የመፈፀም ፈቃድ እንዲኖረው ማድረግ ነው።
የተቋሙ ተልዕኮ
የመሥራት ፍላጎት እና የሥራ ፈጠራ ችሎታ ላላቸው በአነስተኛና መለስተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ የገጠርና የከተማ ነዋሪዎች በኅብረተ ሰቡ ተቀባይነት ባለው አሠራርና ስርዓት የቁጠባ፤ የብድርና ሌሎች አገልግሎቶች በመስጠት ኢኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ሥነ ልቦናዊ ደረጃቸውን ማሻሻል ነው።
የተቋሙ ዕሴቶች
ተቋሙ ዕሴቶቹን በዚህ መልክ ያስቀምጣል፦
-
-
- እኛ ባለአደራዎ ነን
- እኛ ድሆችን ለመደገፍ ቆመናል
- ለሰዎች ክብር እንሰጣለን
- እኛ ክርስቲያን ነን
- አጋሮች ነን
- ፈጣን ምላሽ ሰጪዎች ነን
-
መደበኛ ቁጠባ
- በዓመት እስከ ብር 5,000 ለሚቆጥቡ 7 በመቶ (7%) ወለድ ያገኛሉ
- በዓመት ከብር 5,000 በላይ እስከ ብር 10,000 ለሚቆጥቡ 7.5 በመቶ (7.5%) ወለድ ያገኛሉ
- በዓመት ከብር 10,000 በላይ ለሚቆጥቡ 8 በመቶ (8%) ወለድ ያገኛሉ
በጊዜ የተገደበ ተቀማጭ ቁጠባ
- ከስድስት ወር ላላነሰ ጊዜ የሚቀመጥ ሆኖ የተቀማጩ መጠን ከብር 20,000 እስከ ብር 50,000 ለሚቆጥቡ በዓመት የሚሰላ 8.5 በመቶ (8.5%) ወለድ ያገኛሉ
- ከስድስት ወር ላላነሰ ጊዜ የሚቆጥቡ ሆኖ የተቀማጩ መጠን ከብር 50,001 እስከ ብር 100,000 ለሚቆጥቡ በዓመት የሚሰላ 9.5 በመቶ (9.5%) ወለድ ያገኛሉ
- ከስድስት ወር ላላነሰ ጊዜ የሚቆጥቡ ሆኖ የተቀማጩ መጠን ከብር 100.001 እና ከዚህ በላይ የሚቆጥቡ በዓመት የሚሰላ 10 በመቶ (10%) ወለድ ያገኛሉ
- ከስድስት ወር ላላነሰ ጊዜ የሚቀመጥ ሆኖ የተቀማጩ መጠን ከብር 500.000 እና ከዚህ በላይ ለሚቆጥቡ በዓመት የሚሰላ ሆኖ በድርድር እስከ 13 በመቶ (13%) ወለድ ያገኛሉ
- የግል ብድር፦ አስተማማኝ በሆነ መለስተኛ የንግድ ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ ነጋዴዎች የሚሰጥ ብድር ሲሆን ብድሩን በቂ ዋስትና በማስያዝ በግል ጠይቆ መውሰድ ይችላል። አንድ ተበዳሪ የሚያገኘው ከፍተኛ የብድር መጠን ብር 1,000,000 ሲሆን የብድር መመለሻ ጊዜ ገደብ 36 ወራት ነው።
- የንግድ ብድር፦ መደበኛ የንግድ እንቅስቃሴና ምንጭ ላላቸው አነስተኛ የንግድ ተቋማት የሚሰጥ ብድር ሲሆን ብድሩን ከ3 እስከ 9 አባላት ባሉት ቡድን ወይም ከ10 እስከ 35 አባላት በሚኖሩት ኅብረት ተደራጅተው ለሚቀርቡ አባላት የሚሰጥ የብድር ዓይነት ነው። አንድ አባል የሚያገኘው ከፍተኛው የብድር መጠን ብር 45,000 ሲሆን የብድር መመለሻ ጊዜ ገደብ 36 ወራት ነው።
- የሠራተኛ ፍጆታ ብድር፦ በግል ወይም በቡድን ተደራጅተው ብድር ለሚፈልጉ ተቀጣሪ ሠራተኞች ለጊዜያዊ የገንዘብ እጥረት የሚሰጥ ብድር ነው። አንድ ተበዳሪ የሚያገኘው ከፍተኛ የብድር መጠን ብር 100,000 ሲሆን የብድር መመለሻ ጊዜ ገደብ 36 ወራት ነው።
- የአግሪ ቢዝነስ ብድር፡- ከግብርና ሥራ ጋር ተያያዥነት ላላቸው የአትክልትና ፍራፍሬ፣ ከብት ማደለብና ሽያጭ፣ እህል ንግድ፣ ወተት ማቀናበር እና ለመሳሰሉት የሚሰጥ ብድር ነው። አንድ አካል የሚያገኘው የብድር መጠን ብር 40,000 ሲሆን የብድር መመለሻ ጊዜ ገደብ 12 ወራት ነው።
- የኢንተርፕራይዝ ብድር፦ የሥራ ንግድ እንቅስቃሴያቸው ከፍ ያለ ከ 3 እስከ 9 አባላት ለሚኖሩት ቡድን የሚሰጥ ብድር ነው። አንድ አባል የሚያገኘው ከፍተኛ የብድር መጠን ብር 30,000 ሲሆን የብድር መመለሻ ጊዜ ገደብ 12 ወራት ነው።
- የእርሻ ብድር፦ ወቅታዊ የገንዘብ ፍሰት ለሌላቸው የአዝመራ ወይም የከብት እርባታ ሥራ ላይ ለተሰማሩ አርሶ አደሮች የሚሰጥ ብድር ሲሆን ብድሩን ከ 3 እስከ 9 አባላት የሚኖሩት በኅብረት ተደራጅተው ለሚቀርቡ አባላት የሚሰጥ የብድር ዓይነት ነው። አንድ አባል የሚያገኝው ከፍተኛ የብድር መጠን ብር 20,000 ሲሆን የብድር መመለሻ ጊዜ ገደብ 12 ወራት ነው።
- የሶላር ብድር፦ ለሶላር ዘመናዊ ምድጃ ግዢ የሚውል የብድር አገልግሎት ሲሆን ለዚህ አገልግሎት የሚውል ብድር እስከ ብር 35,000 ይደርሳል። የብድር ዘመኑም እስከ 24 ወራት የሚደርስ ይሆናል።
- ለውሃና መፀዳጃ ግንባታ አገልግሎት የሚውል ብድር፦ ለውሃ አቅርቦት እና ተዛማጅ አገልግሎቶች እንዲሁም ለሽንት ቤትና ተዛማጅ ግንባታ የሚውል የብድር አገልግሎት ሲሆን ለዚህ አገልግሎት የሚውል ብድር እስከ ብር 35,000 ድረስ ይደርሳል። የብድር ዘመኑም እስከ 24 ወራት የሚደርስ ይሆናል።
- ለአነስተኛ መለስተኛ ኢንዱስትሪ የሚቀርብ ብድር፦ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪ የሚውል የመንቀሳቀሻ ካፒታል (Working Capital) የሚቀርብ ሲሆን ይህ በተመረጡ አካባቢዎች በልዩ ጥናት የሚፈፀም ሲሆን የብር መጠኑ እስከ ብር 5,000,000 ሊደርስ ይችላል። የብድር ዘመኑም እስከ 36 ወራትን ይሸፍናል።
- ሥራ ፈጥረው ለሚሰሩ ሴቶች የሚቀርብ ብድር፦ አገልግሎቱ የራሳቸውን ሥራ ፈጥረው ለሚሠሩ ሴቶች ሥራቸውን ለማሳደግ የሚቀርብ ብድር ሲሆን የብር መጠኑ እስከ 1,500,000 ብር (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ) ሊደርስ ይችላል።
- የትምህርት ቤት ብድር፦ ብድሩ የትምህርት አገልግሎት በመስጠት ላይ ለተሰማሩ ግለሰቦች የቀረበ አገልግሎት ሲሆን ለዚህ አገልግሎት የሚውል ብድር እስከ 600,000 ይደርሳል። የብድር ዘመኑም እስከ 36 ወራት የሚደርስ ይሆናል።
ቅርንጫፍ | ስልክ ቁጥር |
---|---|
ገርጂ መብራት ኃይል (ዋና መሥሪያ ቤት) | +251 116466569 |
ሾላ ቅርንጫፍ | +251 911041922 |
ልደታ ቅርንጫፍ | +251 913256768 |
ኮልፌ ቅርንጫፍ | +251 910039451 |
ቃሊቲ ቅርንጫፍ | +251 913048628 |
ኮተቤ ቅርንጫፍ | +251 913289446 |
ቂርቆስ ቅርንጫፍ | +251 912612295 |
ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ቪዥን ፈንድ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አክሲዮን ማኅበር በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።