መነሻ / የጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ / ወቅታዊ መረጃ / የከተማ ግብርና፦ በአዲስ አበባ በዘንድሮው የመኸር ወቅት ከ5000 ሄክታር በላይ መሬት ሙሉ በሙሉ በዘር ተሸፈነ
የከተማ-ግብርና

የከተማ ግብርና፦ በአዲስ አበባ በዘንድሮው የመኸር ወቅት ከ5000 ሄክታር በላይ መሬት ሙሉ በሙሉ በዘር ተሸፈነ

በአዲስ አበባ ከተማ በዘንድሮው የመኸር ወቅት ከአምስት ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ሙሉ በሙሉ በዘር መሸፈኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደሮችና ከተማ ግብርና ኮሚሽን አስታወቀ።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር መኮንን ሌንጅሶ ከቦሌ ክፍለ ከተማ አመራሮች ጋር በመሆን የከተማ ግብርና የሥራ እንቅስቃሴን በቦሌ ክፍለ ከተማ በመገኘት የመስክ ጉብኝት አድርገዋል።

“ምግባችን ከደጃችን” በሚል መሪ ቃል ክረምት ከመግባቱ በፊት በስድስት ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ አርሶ አደሮች ምርትና ምርታማነታቸውን ለማሳደግ የእርሻ ማረሻ ትራክተር ፣ የአፈር ማዳበሪያና ልዩ ልዩ ምርጥ ዘር ድጋፍ መድረጉ ይታወሳል። በዚህም ድጋፍ ከ5ሺህ በላይ ሄክታር መሬት ሙሉ በሙሉ በዘር መሸፈኑን ኮሚሽነሩ በመስክ ጉብኝቱ አስታውቀዋል።

በዚህም በከተማዋ የግብርና አምራች በሆኑ ክፍለ ከተሞች የተሻለ ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጨምረው ገልጸዋል።

የዜና እና የምስል ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪ ቢሮ የፌስቡክ ገጽ

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …