መነሻ / የጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ / ወቅታዊ መረጃ / በአዲስ አበባ በ2013 በጀት አመት 525 ኪሎ ሜትር የጥገና ስራ ይከናወናል
AARCA-road-repair

በአዲስ አበባ በ2013 በጀት አመት 525 ኪሎ ሜትር የጥገና ስራ ይከናወናል

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በ2013 በጀት አመት በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች 525 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የአስፋልት፣ የድልድይ፣ የድሬይኔጅ፣ የአክሰስ መንገድ እና ሌሎች በርካታ ልዩ ልዩ የጥገና ስራዎችን ለማከናወን አቀደ፡፡

በዚህም 130 ኪ.ሜ የአስፋልት መንገድ ጥገና፣ 68 ኪ.ሜ የጠጠር መንገድ ጥገና፣ 50 ኪ.ሜ የኮብል ስቶን መንገድ ጥገና፣ 20 ኪ.ሜ የእግረኛ መንድና ከርቭ ስቶን ጥገና፣ 257 ኪ.ሜ የድሬይኔጅ መስመር ጥገናና የፉካና ቦይ ጠረጋ ስራዎች ሲሆኑ የማንሆል ክዳን እንዲሁም የድጋፍ ግንብና የድልድይ ጥገና ስራዎችም የሚከናወኑ ይሆናል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በሁሉም የከተማዋ አካባቢዎች መደበኛና ወቅታዊ ተደራሽ ጥገና ማድረግ፣ በነባር መንገዶች የከርቭስቶን ግንባታ ማከናወን፣ የመንገድ ዳር መብራት ጥገና ሥራዎችን ማከናወንና ሌሎች ጥገና የሚያስፈልጋቸው ሥራዎችን በራስ ኃይል ለማከናወን እቅድ ተይዟል ፡፡

የጥገና ስራው የሚከናወነው በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች የትራፊክ እንቅስቃሴን የሚያስተጓጉሉ ብሎም ለእግረኛ እንቅስቃሴ አስቸጋሪ በሆኑ ቦታዎች ላይ ነው፡፡
ከጥገና ስራ ጋር በተያያዘ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በ2012 በጀት አመት 544 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ልዩ ልዩ የጥገና ስራዎችን አከናውኗል፡፡ በዚህም በ2013 በጀት አመት በአዲስ አበባ በተለያየ ምክንያት እየተበላሹ በሕብረተሰቡ ዘንድ ቅሬታን የሚያስነሱ አካባቢዎችን የመልሶ ግንባታና ጥገና ስራዎችን በስፋት ለማናከወንና የህብረተሰቡን የመንገድ ጥያቄዎች ለመፍታት ጥረት እንደሚያደርግም አስታውቋል፡፡

የዜና እና የምስል ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የፌስቡክ ገጽ

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …