መነሻ / ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት / የግል ብድር እና ቁጠባ ተቋማት / “ዛሬ በመቆጠብ ነገን በተሻለ ህይወት ይኑሩ” – አፍሪካ ቪሌጅ ፋይናንሽያል ሰርቪስስ አ.ማ.
africafssc-logo

“ዛሬ በመቆጠብ ነገን በተሻለ ህይወት ይኑሩ” – አፍሪካ ቪሌጅ ፋይናንሽያል ሰርቪስስ አ.ማ.

አፍሪካ ቪሌጅ ፋይናንሽያል ሰርቪስስ አ.ማ. በአዋጅ ቁጥር 626/2009 መሠረት ተቋቁሞ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ በማግኝት እ.ኤ.አ. ከ1999 ጀምሮ በኦሮሚያና በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ውስጥ ፋይናንስ ነክ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ የሚገኝ የፋይናንስ ተቋም ነው።

አፍሪካ ቪሌጅ ፋይናንሽያል ሰርቪስስ አ.ማ.፦ ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ ዓላማ እና አጋር ድርጅቶች

ራዕይ

ተቋሙ የደንበኞችን ፍላጎት ማዕከል ያደረገ ፈጣንና የተቀላጠፈ የፋይናንስ አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ እና ቀጣይነት ያለው ተቋሙን በሀገር ደረጃ መገንባት ነው።

ተልዕኮ

  • በንግድ ሥራ መስኮች ለተሰማሩና ለመሰማራት ለሚፈልጉ የከተማና የገጠር ነዋሪዎች በተለይም ለሴቶች ትኩረት በመስጠት ዘላቂነቱ የተረጋገጠ የፋይናንስ አገልግሎት በስፋት በማቅረብ የተጠቃሚዎችን የገቢ ምንጭ ከፍ ማድረግ
  • አዲስ የሥራ ፈጣሪነትን ማበረታታት እና እንዲሁም የሥራ እድል ፈጣሪነትን ማጎልበት
  • እነዚህን ተግባራዊ ለማድረግ ከአጋር ድርጅቶች እና ተቋማት ጋር የጋራ ፍላጎት በመቅረጽ በአገር የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ ሰፊ አስተዋጽዖ ማድረግ ነው።

ዓላማ

  • ዘላቂነቱ የተረጋገጠና አስተማማኝ የሆነ የብድርና ቁጠባ አገልግሎት በስፋትና በጥራት መስጠት
  • በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደረው አብዛኛው የኅብረተ ሰብ ክፍል በብድርና ቁጠባ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ
  • ለጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ሥራ መስኮች መስፋፋትና መጎልበት አስተዋጽዖ ማድረግ
  • የኅብረተ ሰቡን በተለይ የወጣቱን በራስ የመተማመንና የሥራ እድል የመፍጠር ባሕል ማበረታታና ማጎልበት
  • የኅብረተ ሰቡን የቁጠባ ባሕል ማጎልበት እና ሌሎች ናቸው።

አጋር ድርጅቶች

  • ከተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ የልማት ድርጅቶች ጋር አብሮ እየሠራ ይገኛል
  • እንዲሁም ከግሪን ቴክ ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመሥራት የሥራ ስምምነት ፈጥሯል
  • በዚህም ለሥራና ለአገልግሎት ለሚውሉት ተሽከርካሪዎች ተቋሙ የፋይናንስ አገልግሎት ለማቅረብ በዝግጅት ላይ ነው።

አፍሪካ ቪሌጅ ፋይናንሽያል ሰርቪስ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

  • የውዴታ ግዴታ ቁጠባ፦ ብድር የሚወስዱትን ብቻ የሚመለከት ሆኖ ከመሰጠቱ በፊትና ከተሰጠ በኋላም ተከፍሎ እስከሚያልቅ ድረስ በየወሩ ተበዳሪዎች በተቋሙ ፖሊሲ መሠረት የሚያስቀምጡት ቁጠባ ነው።
  • የፈቃደኝነት ቁጠባ
  • የሳጥን ቁጠባ
  • የደብተር ቁጠባ
  • የጊዜ ገደብ ቁጠባ
  • የልጆችና የወጣቶች ቁጠባ
  • የወለድ አልባ ቁጠባ
  • በየወሩ የሚከፈል ብድር
  • በተወሰነ የጊዜ ገደብ ተጠቃሎ በአንድ የሚከፈል ብድር
  • የመሣሪያ ሊዝ ብድር
  • ለየቤት ውስጥ አገልግሎት የሚውል ብድር
  • ለሽመና፣ ለልብስ ስፌትና ሹራብ ሥራ
  • ለቆዳ ውጤቶች
  • ለደረቅ ምግብ ዝግጅት
  • ለከተማ ግብርና
  • ለብረታ ብረትና የእንጨት ውጤቶች
  • ለግንባታ የሚውሉ ምርቶች
  • ለጽዳትና ለመሳሰሉት ማኅበረ ሰባዊ ስራዎች
  • ለሌሎች የምርት አገልግሎት ሰጪና የንግድ ሥራ መስኮች
  • እድሜያቸው 18 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑ
  • የሽርክናና ሌሎች የንግድ ማኅበራት
  • በግልም ሆነ በቡድን የሚመጡ ተበዳሪዎች
  • ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው እድሮች፣ ኅብረት ሥራ ማኅበራት፣ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር (PLC)
  • የሦስተኛ ወገኖች ገንዘብ ማስተዳደር
  • የምክር አገልግሎት መስጠት

አፍሪካ ቪሌጅ ፋይናንሽያል ሰርቪስስ አ.ማ.፦ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር

ተ.ቁቅርንጫፍስልክአድራሻ
1ዋና መሥሪያ ቤት011 384 21 45ካዛንቺስ ባህራን ሞል 8ኛ ፎቅ
2ኮልፌ ቅርንጫፍ011 279 1128ምድረገነት የገበያ አዳራሽ
3ቡራዩ ንዑስ ቅርንጫፍ 011 284 4152ቡራዩ
4ቢሾፍቱ ቅርንጫፍ011 430 0310ቶርባን ገርባ
5ሞጆ ቅርንጫፍ022 116 1979ሚካኤል ሕንጻ
6መቂ ቅርንጫፍ022 118 1355መቂ
7ባቱ (ዝዋይ)046 444 3584ባቱ (ዝዋይ)
8ሰንዳፋ ቅርንጫፍ011 686 0206ሰንዳፋ
9ሸኖ ንዑስ ቅርንጫፍሸኖ
10ሆለታ ቅርንጫፍ011 237 1012ሆለታ
11አዲስ ዓለም ንዑስ ቅርንጫፍ011 283 0971ኤጀር አስተዳደር አካባቢ

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው አፍሪካ ቪሌጅ ፋይናንሽያል ሰርቪስስ አ.ማ. በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

liyu-logo

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም መንግሥት ባወጣው የአንስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 40/88 መሠረት …