መነሻ / ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት / የግል ብድር እና ቁጠባ ተቋማት / ቤተ-ሐበሻ ቁጠባ እና ብድር ኀላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር

ቤተ-ሐበሻ ቁጠባ እና ብድር ኀላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር

ኅብረት ሥራ ማኅበር ሰዎች የጋራ ፍላጎታቸውን ለማሳካት ያላቸውን ዕውቀት፣ ጉልበት፣ ጊዜ እና ሀብት በማሰባሰብ ችግሮቻቸውን መፍታት የሚያስችል ቁልፍ መሣሪያ ነው። በዚህ መሠረት ቤተ-ሐበሻ ቁጠባ እና ብድር ኀላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ መሥራች አባላት በሕጋዊ መንገድ የተመሠረተ የኅብረት ሥራ ማኅበር ነው።

ቤተ-ሐበሻ ቁጠባ እና ብድር፦ ራእይ፣ ተልዕኮ እና ዐላማ

ራእይ

በሀገራችን ኢትዮጵያ ዘላቂነት ያለው የገንዘብ ተቋም ፈጥሮ በኢኮኖሚ የዳበረ ኅብረተ ሰብ ማየት

ተልዕኮ

ኅብረተ ሰቡን በማስተባበር ዕውቀትና ተገቢውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም በፍላጎት ላይ የተመሠረተ አስተማማኝ የሆነ የፋይናንስ አቅርቦት ለአባላት አንዲኖር ማድረግ

ዐላማ

  • ዘላቂነት ያለው የገንዘብ ተቋም መፍጠር፤ የባንክ ነክ አገልግሎት መስጠት
  • አባላት በኅብረት ሥራ ማኅበራቸው ገንዘብ እንዲቆጥቡ በማድረግ ኅብረተ ሰቡ ኋላቀር ከሆነና ለብዝበዛ ከሚያጋልጥ አራጣ አበዳሪዎች ማላቀቅ
  • በሀገራችን ኢትዮጵያ መንግሥት ባስቀመጠው የልማት ዕቅዶች የበኩሉን አስተዋጽኦ በማድረግ ኀላፊነቱን መወጣት

ቤተ-ሐበሻ ቁጠባ እና ብድር፦ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

መደበኛ ቁጠባ

  • ይህ የቁጠባ ዓይነት በየወሩ የማይቀር የግዴታ ቁጠባ ሆኖ በየወሩ በተከታታይ የሚቆጠብ ነው።
  • የቁጠባ ተቀማጭ በዓመት 7% ወለድ ለቆጣቢ ያስገኛል።

የፈቃደኝነት ቁጠባ

  • ይህ የቁጠባ ዓይነት አባላት በውዴታ የሚቆጥቡት ሆኖ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ አውጥቶ መጠቀም የሚያስችል ነው።
  • የቁጠባ ተቀማጭ በዓመት 7% ወለድ ለቆጣቢ ያስገኛል።

የልጆች ቁጠባ

  • ይህ የቁጠባ ዓይነት ወላጆች ለልጆቻቸው የሚቆጥቡት ነው።
  • የ9% (ዘጠኝ በመቶ) ወለድ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው።

የጊዜ ገደብ ተቀማጭ

  • አንድ ግለሰብ በጊዜ የተገደበ ተቀማጭ ብር ለማስቀመጥ ከማኅበሩ ጋር ስምምነት ውል በመዋዋል ባንኮች ከሚሰጡት የበለጠ የወለድ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው።
 
  • ለማኅበራዊ ጉዳዮች
  • ለሠርግ
  • ለሐዘንና ለመሳሰሉት
  • ለመኪና ግዥ
  • ለአዲስ ንግድ
  • ለነባር ንግድ ማስፋፊያ
  • ለቤት ግንባታ እና እድሳት
  • ለትምህርት ወጪ
  • ለሕክምና ወጪ
  • ለነጋዴዎች አስቸኳይ የገንዘብ ፍላጎት
  • ለኮንዶሚኒየም ቅድመ ክፍያ
ተ.ቁየብድር ዓይነት የብድር መጠን በብርለመበደር የሚያፈልገው ቁጠባ በፕርሰንት
1ለቤት መግዣ እና መሥሪያ3,000,000.0030% የብድሩን መጠን በተከታታይ መቆጠብ
2ለትራንስፖርት መኪና መግዣ2,000,000.0037% የብድሩን መጠን በተከታታይ መቆጠብ
3ለቤት መኪና መግዣ1,400,000.0037% የብድሩን መጠን በተከታታይ መቆጠብ
4ለንግድ እና ለተለያዩ ፍላጎቶች400,000.0025% የብድሩን መጠን በተከታታይ መቆጠብ
5አስቸኳይ ብድር2,500,000.0050% የብድሩን መጠን በተከታታይ መቆጠብ
  • በሕግ መብቱ ያልተገፈፈ
  • የኅብረት ሥራ ማኅበሩ መብት እና ግዴታ ለመፈጸም ፈቃደኛ የሆነ
  • እድሜው 18 ዓመት እና ከዛ በላይ የሆነ
  • የአዲስ አበባና አካባቢው ነዋሪ የሆነ
  • የማይመለስ የመመዝገቢያ ብር 1,000.00 (ብር አንድ ሺሕ) መክፈል የሚችል
  • ወርሃዊ የቁጠባ መነሻ ብር 500 ብር (ብር ዐምስት መቶ) መክፈል የሚችል
  • መነሻውን/ትንሹን የአክስዮን መጠን መግዛት የሚችል
  • 2 ፎቶ ግራፍ
  • የነዋሪነት መታወቅያ ኮፒ
  • አባል ሆኖ ከተመዘገበ ቀን ጀምሮ በየወሩ መቆጠብ የሚችል

ቤተ-ሐበሻ ቁጠባ እና ብድር፦ አድራሻ እና ስልክ

አድራሻ

    1. ከሰሜን ሆቴል ወደ አፍንጮ በር የሚወስደው መንገድ፣ አዱ ሕንጻ፣ 1ኛ ፎቅ
    2. አራዳ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስትያን፣ ገነት ጽጌ ሕንጻ፣ 3ኛ ፎቅ
    3. ሃያ ሁለት፣ ታውን ስኩዌር ሞል ሕንጻ፣ 3ኛ ፎቅ

ስልኮች

    • +251 938 379258
    • +251 943 197243
    • +251 954 358252

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ  የተዘጋጀው ቤተ-ሐበሻ ቁጠባ እና ብድር ኀላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

ኒኦ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ.

ኒኦ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባገኘው ፈቃድ መሠረት በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ላይ …