መነሻ / የቢዝነስ ዜና / የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ 285 ብሔራዊ የጥራት ደረጃዎች መፅደቃቸውን አስታወቀ
ESA-logo

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ 285 ብሔራዊ የጥራት ደረጃዎች መፅደቃቸውን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ከብሔራዊ የደረጃ ዝግጅት ቴክኒክ ኮሚቴ ጋር በመሆን፣ የ285 ብሔራዊ የጥራት ደረጃዎችን በብሔራዊ ደረጃዎች ምክር ቤት ማፅደቁን አስታወቀ። ኤጀንሲው እንዳስታወቀው ለብሔራዊ የደረጃዎች ምክር ቤት ያቀረባቸው 285 የጥራት ደረጃዎች ፀድቀዋል። በስድስት ዘርፎች ተዘጋጅተው ከቀረቡት 285 ደረጃዎች 148 ያህሉ አዲስ ሲሆኑ፣ 44 የሚሆኑት የተከለሱና የተቀሩት 93 ደረጃዎች በፊት የነበሩና እንዲቀጥሉ የተወሰኑ እንደሆኑ ኤጀንሲው አስታውቋል።

እነዚህም

  • በግብርናና በምግብ ዝግጅት 18
  • በመሠረታዊና አጠቃላይ የደረጃ ዝግጅት 28
  • በኬሚካልና ኬሚካል ውጤቶች 72
  • በኮንስትራክሽንና ሲቪል ኢንጂነሪንግ 79
  • በኤሌክትሮ ሜካኒካል 69
  • በአካባቢና ጤና ደኅንነት 19 ደረጃዎች

እንደሆኑ ታውቋል።

በጠቅላላው ለብሔራዊ ደረጃዎች ምክር ቤት የቀረቡት ደረጃዎች 289 እንደነበሩ ያስረዱት ዋና ዳይሬክተሩ፣ 285 የሚሆኑት ሲፀድቁ አራቱ ደረጃዎች እንዲዘገዩ የተደረገው ባለድርሻ አካላትን በበቂ ሁኔታ ያሳተፈ ውይይት እንዲደረግባቸው ትዕዛዝ የተሰጠባቸው ከወረቀት፣ ከፐልፕና ከተዛማጅ ምርቶች ጋር የተገናኙት ደረጃዎች እንደሆኑ አስታውቀዋል። ደረጃን ተግባራዊ ለማድረግ ኤጀንሲው በአገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ በሚያስብል ሁኔታ ከ400 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የደረጃዎች አካዳሚን ገንብቶ ጨርሷል።

የዜና እና የምስል ምንጭ፡ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የፌስቡክ ገጽ

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …