መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / ዋቢ ጋርመንት
wabi-garment

ዋቢ ጋርመንት

ፈለቁ አያሌው ልብስ ስፌት (ዋቢ ጋርመንት) የተመሠረተው በወ/ሮ ፈለቁ 2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ በአሁን ሰዓት በዋናነት የሚያመርታቸው ልብሶች የህጻናት ቱታ እና ቬሎዎችን በስፋት እያመረተ ይገኛል።

ድርጅቱ የሚያመርታቸው ምርቶች

  • የህፃናት አልብሳት ቬሎ፣ ሱሪ፣ ሹራብ
  • የአዋቂዎች አልብሳት ካፖርት፣ ሱሪ፣ ሸሚዝ፣ ቀሚስ
  • ለተለያዩ ሥራዎች የሚሆኑ ጋዋኖች፣ የትምህርት ቤት ዩኒፎርሞች እና የተለያዩ የሥራ የደንብ ልብሶች እና
  • ከአልባሳት ዘርፍ ወጣ ያሉ እንደ መጋረጃ እንዲሁም የሶፋ ጨርቅ እና አጠቃላይ የስፌት ሥራዎች

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

የድርጅቱ መሥራች ይህን ድርጅት ከመጀመራቸው በፊት በቡቲክ ሥራ ተቀጥረው በሚሠሩበት ጊዜ ሰዎች የሚፈልጉትን ነገር እያወቁ ሲመጡ እና ምን ምን ገበያ ላይ ችግር እንዳለ ተመለከቱ። በዚህም መነሻነት ይህን ነገር እኔ መሥራት ብችል ተጠቃሚ እሆናለሁ ብለው በማሰብ የልብስ ዲዛይን ትምህርት ቤት ገብተው ተማሩ። ከዛም በኋላ በ 23,000 ብር መነሻ ካፒታል ዋቢ ጋርመንትን በ2011 ዓ.ም. መሥርተዋል።

ወ/ሮ ፈለቁ ሥራውን ከጀመሩ በኋላ አንዳንድ ያስቸገሯቸው ነገሮች፦ የጥሬ እቃ አቅርቦት ቦታ አለማወቅ፣ ጥራት ያለው ምርት የቱ ነው የሚለው፤ እንዲሁም ሥራ ማግኘት እና የመሳሰሉት ችግሮች ነበሩ። በዘርፉ በጣም የተሻሉ ባለሙያ ሰዎች ስላሉ እነሱን በማናገር ከባለሙያዎች ጋር በመሆን በመማር እራሳቸውን ሊያበቁ ችለዋል።

ድርጅቱ አሁን ላይ የሚያመርታቸውን ምርቶች ለአከፋፋይ በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረበ ይገኛል፤ ለምሳሌ አንድ ቱታ በሁለት መቶ ብር ለአከፋፋዮች ያቀርባል። ይሁን እንጂ በፍሬ መግዛት የሚፈልግ ደንበኛ በሚፈልገው መጠን መግዛት እና የሚፈልገውን ልብስ ማሠራት እንደሚችል የድርጅቱ መሥራች ገልጸዋል።

ዋቢ ጋርመንት ሥራዎችን እየሠራ የሚገኘው ወርክ ሾፕ በሚመጡ ደንበኞች እንዲሁም እራሳቸው የድርጅቱ ሠራተኞች የተለያዩ ሱቆች፣ ማከፋፈያዎች እና ሥራ ይኖራል ብለው የሚያስቧቸው ቦታዎች ጋር በመሄድ እነሱን በማናገር ነው። እንዲሁም 2merkato.com ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ያዘጋጀውን የከፍታ አገልግሎት ፓኬጅ በመጠቀም ጨረታዎችንም እየተከታተሉ ይገኛሉ። ድርጅቱ ምርቱን ከአዲስ አበባ በተጨማሪ ደሴ፣ ጎንደር፣ ደብረ ብርሃን እና አዳማ እያቀረበ ይገኛል።

ድርጅቱ በአሁን ሰዓት ለዐሥር ሠራተኞች የሥራ ዕድል መፍጠር የቻለ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ የካፒታል አቅሙን ወደ አምስት መቶ ሺህ ብር አሳድጓል። አራት ጅምላ ተረካቢ ደንበኞችንም አፍርቷል።

የኮቪድ ተፅዕኖ

በኮቪድ ጊዜ ድርጅቱ ለተወሰነ ጊዜ ሥራ አቁሞ የነበረ ሲሆን፤ በዚህም ጊዜ የፊት መሸፈኛ ማስኮችን እያመረተ በማቅረብ የኮቪድን ጊዜ አሳልፏል።

ምክር እና እቅድ

ድርጅቱ ወደ ፊት የራሱ የምርት መሸጫ ቦታ በማግኘት የሚያመርተውን ምርት በቀጥታ ወደ ተጠቃሚ ለማድረስ እቅድ አለው።

ወ/ሮ ፈለቁ “አዲስ ወደ ሥራ የሚገቡ ሰዎች ትዕግስተኛ መሆን አለባቸው። ሥራ ላይ ኪሳራም ትርፍም አለ። ህልም ሊኖር ይገባል፤ ህልም ካለ ትዕግስትም ይኖራል፤ ዋጋ ይከፈልበታል እንዲሁም ደግሞ ደፋር መሆን አለባቸው። እንዲሁም ሥራ ሲመጣ ምንም አይነት ሥራ ሳይመርጡ መሥራት ውጤታማ ያደርጋል። እኔም በዚህ መልኩ ነው ውጤታማ የሆንኩት” ብለው ምክራቸውን አስተላልፈዋል።

የድርጅቱን አገልግሎት መጠቀም የሚፈልጉ የድርጅቱን ስልክ በዚህ ሊንክ በመግባት ዓይተው መደወል ይችላሉ

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …