መነሻ / የጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ / ወቅታዊ መረጃ / የስራ እድል መፍጠር ቅድሚያ እና ልዩ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

የስራ እድል መፍጠር ቅድሚያ እና ልዩ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

ለወጣቶች የስራ እድል የመፍጠር ጉዳይ ቅድሚያ እና ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ስራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። በተለያዩ ጊዜያት ለስራ ፈጠራ ተብለው የተበተኑ የወጣቶች ተዘዋዋሪ ፈንድ የብድር ገንዘብ በወቅቱ እንዲመለስ በማድረግ ለቀጣይ ወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ መልሶ ማበደር መቻል አለበትም ነው ያሉት።

የአዲስ አበባ ከተማ የስራ እድል ፈጠራ ምክር ቤት በ2013 በጀት ዓመት የስራ እድል ፈጠራ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እና የክፍለ ከተሞች ስራ አስፈጻሚዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።

ከዚህ በተጨማሪም በመስሪያ ሼዶች አካባቢ የሚስተዋሉ የመብራት አቅርቦት እና የመሰረተ ልማት ችግሮች በአፋጣኝ እንዲፈቱ መናገራቸው ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የስራ እድል ፈጠራ ምክር ቤቱ የ2013 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከማዕከል እስከ ክፍለ ከተማ የተሰሩ ስራዎች አፈጻጸም ሪፖርት የገመገመ ሲሆን በዘርፉ ያጋጠሙ ችግሮች እና ቀጣይ የስራ አቅጣጫ ዙሪያ ሰፊ ምክክር ተካሂዷል።

በስራ እድል ፈጠራ ምክር ቤት ላይ የተገኙት ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለሴቶች እና ለወጣቶች የስራ እድል መፍጠር የከተማዋን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች በማፋጠን ረገድ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል። በከተማዋ ያልተነካ ሰፊ የስራ ዕድል መኖሩን የጠቀሱት ምክትል ከንቲባዋ ስራን እና ስራ ፈላጊ ዜጎችን በማቀራረብ በኩል ብዙ ክፍተቶች መኖራቸውንም ገልጸዋል። በዚህም በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ለስራ እድል ፈጠራ ዘርፍ ከእቅድ ጀምሮ እስከ አፈጻጸሙ ድረስ ቅድሚያ በመስጠት በልዩ ትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ ወይዘሮ አዳነች ተናግረዋል።


የዜና ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …