ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የንግድ ፈቃድና ምዝገባ ሲያከናውኑ፣ በሃገር አቀፍ ደረጃ በሥራ ላይ ባለው የንግድና ምዝገባ የዘርፎች አደረጃጀት መሠረት ይሆናል። ሆኖም ጥቃቅና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ይህንን አገልግሎት በ “አንድ ማዕከል” አገልግሎት ያገኛሉ።
የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች “አንድ ማዕከል” አገልግሎት
እንደየአካባቢው ሁኔታ፣ በወረዳ፣ በክፍለ ከተማ እና በከተማ ደረጃ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የ”አንድ ማዕከል” አገልግሎት ያገኛሉ። ኢንተርፕራይዞች በማዕከሎቹ የሚከተሉትን አገልግሎቶች ያገኛሉ፡-
- በኅብረት ሥራ ማኅበር፣ በግል፣ በሽርክና፣ ኃላፊነቱ በተወሰነ የግል ማኅበር ወዘተ መደራጀት፣ መመዝገብና የምስክር ወረቀት ማግኘት
- የግብር ከፋይነት ምዝገባ አገልግሎት ማግኘት
- የንግድ ፈቃድ ማደስ፣ መለወጥና መሰረዝ
- የሂሳብ አያያዝና ኦዲት አገልግሎት ማመቻቸት