በዚህ ዘመን መልዕክቶችን በቴሌግራም፣ በፌስቡክ ሜሴንጀር፣ በዋትስአፕ፣ በቫይበር፣ በዊቻት እና በመሳሰሉት መለዋወጥ ይቻላል፤ ቢሆንም ኢሜይል ለቢዝነስ ወሳኝ እና ከሌሎች ኢንተርኔትን ተጠቅመን ከምንልካቸው መልዕክቶች የበለጠ መደበኛ (formal) የሆነ የመልዕክት መለዋወጫ ዘዴ ነው። በተለይ ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር ስንሠራ (ጨረታም ሆነ የኢምፖርት/ኤክስፖርት ቢዝነስ) በኢሜይል በትክክል መልዕክት መለዋወጥ መቻል በጣም አስፈላጊ ነው። አንዳንድ …
ተጨማሪቢዝነስ እና ቴክ
ቴሌግራም (Telegram) እና ቢዝነስ
ቴሌግራም (Telegram) በአገራችን በጣም ተወዳጅ የሆነ የመልዕክት መለዋወጫ (Instant Messaging) አፕ/መተግበሪያ ነው። ተወዳጅ ከሆነበት ምክንያት አንዱ በአነስተኛ ዳታ መጠቀም መቻሉ ነው። ቴሌግራምን በስልካችንም ሆነ ከስልካችን አካውንት ጋር አገናኝተን በኮምፒውተራችን ላይ መጠቀም እንችላለን። ቴሌግራም በተለይ አገራችን ውስጥ ከሌሎች የመልዕክት መለዋወጫ (Instant Messaging) አፖች/መተግበሪያዎች በላቀ ሁኔታ ተወዳጅ ስለሆነ ለለቢዝነሶች ከፍተኛ ጥቅም አለው። …
ተጨማሪሊንከዲን (LinkedIn) እና ቢዝነስ
ሊንከዲን (LinkedIn) በማይክሮሶፍት ባለቤትነት የተያዘ ለቢዝነሶች፣ ለፕሮፌሽናሎች፣ ለሥራ ፈላጊዎች እና ቀጣሪዎች የተቋቋመ የማኅበራዊ ድረ ገጽ ነው። አባል ለመሆን ምንም አይነት ክፍያ አያስፈልግም። ግን የአባልነት ዓይነቱን ወደ ፕሪሚየም (premium) ከፍ ማድረግ ከፈለግን እና ማስታወቂያ ማውጣት ከፈልግን ግን ከፍያ ያስከፍለናል። ከዚህ በታች የተጠቀሱት አግልግሎቶች በሙሉ በነጻ ናቸው።
ተጨማሪፌስቡክ እና ቢዝነስ
ስድስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ፌስቡክን ይጠቀማሉ። ፌስቡክን በቀላሉ ቢዝነስን ለማሳደግ መጠቀም ስለሚቻል የተጠቃሚው ኢትዮጵያ ውስጥ መብዛት ለቢዝነሶች ጥሩ ዕድል ነው። ፌስቡክን ለቢዝነስ መጠቀም የሚቻልባቸው መንገዶች፦
ተጨማሪየጉግል ጥቅም ለቢዝነሳችን – ጉግል ቢዝነስ
ጉግል ለቢዝነሳችን ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች አሉት፤ ከነኝህም ውስጥ ዋነኛው ጉግል ቢዝነስ (Google Business) ይሰኛል። ጉግል ቢዝነስ የሚባለው የጉግል አገልግሎት ቢዝነሶች ራሳቸውን ጉግል ላይ በማስገባት ደንበኞች በቀላሉ እንዲያገኟቸው የሚያስችል ነው። ቢዝነሶች ሙሉ አድራሻቸውን፣ የሥራቸውን ዓይነት፣ ምስሎች፣ ወዘተ ማስገባት ይችላሉ። የድርጅታቸውም ቦታ በቀላሉ እንዲገኝ የጉግል ማፕ (ካርታ) ላይ ማስገባት ይችላሉ። እንዲሁም አዳዲስ …
ተጨማሪ