መነሻ / Tag Archives: Micro Finance

Tag Archives: Micro Finance

ቤተል የገንዘብ ቁጠባና ብድር

credit-and-saving

ቤተል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኀበር የተቋቋመው በኢትዮጵያ የኀብረት ሥራ ማኅበር አዋጅ መሠረት በቁጥር 985/2009 ሲሆን፤ ሕጋዊ ሰውነት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኀብረት ሥራ ኤጀንሲ በነሐሴ 2005 ዓ.ም. ፈቃድ አግኝቶ በሥራ ላይ ይገኛል። “ቤተል ውስጥ ሁላችንም አለን!!”

ተጨማሪ

ግሬት የገንዘብ ቁጠባና ብድር

ግሬት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር ማኅበረ ሰቡ ከሚያገኘው ገቢ ላይ በመቆጠብ የቁጠባን ባሕል በማዳበር ፈጣን የሆነ የብድር አገልግሎት ለመስጠት፣ በግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ ሥራ አመራር ሃሳብ አመንጪነት እና በሠራተኞች መሥራችነት ጥቅምት 5 ቀን፣ 2012 ዓ.ም. በቦሌ ክፍለ ከተማ ተመሠረተ። ግሬት! ለእድገት ጽኑ መሠረት!

ተጨማሪ

አጋፔ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሰረታዊ ህብረት ሥራ ማህበር

ኅብረት ሥራ ማህበር ማለት ሰዎች የጋራ ፍላጎታቸውን ለማሳካት ያላቸውን እውቀት፣ ጉልበት፣ ጊዜ እና ሀብት በማሰባሰብ ችግሮቻቸውን መፍታት የሚያስችል ቁልፍ መሣሪያ ነው። በዚህ መሠረት አጋፔ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ መሥራች አባላት በሕጋዊ መንገድ የተመሠረተ ኅብረት ሥራ ማኅበር ነው።

ተጨማሪ

የአብሮነት ተምሳሌት በተግባር – ዮቶር የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ተቋም

ዮቶር በዋናነት በአነስተኛ ንግድ ላይ የተሰማሩ የኅብረት ሥራ ማኅበሩ አባላት ንግዳቸውን የሚያንቀሳቅሱበት እና የሚያስፋፉበት እንዲሁም አብሮነታቸውን የሚያጠነክሩበት፤ ብሎም መካከለኛ የገንዘብ ዓቅም በማዳበር የትምህርት፣ የጤና እና ሌሎች ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ለማሟላት የሚውል የገንዘብ አቅርቦትን ለመፍጠር በሠለጠነ የሰው ኃይል እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ ጠንካራ የኀብረት ሥራ ማኅበር በመፍጠር እስከ 2026 ዓ.ም ድረስ የአባላቱን …

ተጨማሪ

ብርሃን ለኢትዮጵያ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር

birhan-le-ethiopia-credi-saving-logo

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ብርሃን ለኢትዮጵያ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በአካል ሄዶ እና  በዌብሳይት በመመልከት በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ተጨማሪ

የኛ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር

“የኛ ሁሌም የኛ የሁላችንም ነው!!” በሚል መሪ ቃል የሚታወቀው የኛ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የሚገኙ እና በትምህርት ደረጃቸው ዝቅተኛ የሆኑትን፣ እንዲሁም መካከለኛውን የኅብረተ ሰብ ክፍሎች በገንዘብ አስተዳደር እና አጠቃቀም እና በተለያዩ ሥልጠናዎች በማገዝ የኑሮና አኗኗር ለውጥን ለማምጣት እና ለመሥራት የተቋቋመ የገንዘብ ቁጠባና …

ተጨማሪ