አንዋር ሱሌማን እና ጓደኞቻቸው የስፖንጅ እና ፎም ውጤቶች የተመሠረተው በ 2010 ዓ.ም በአቶ አንዋር እና አራት መሥራች አባላት ነው። ድርጅቱ የተለያዩ ለአልጋ እና ለትራስ የሚሆኑ ስፖንጆችን የሚያመርት ድርጅት ሲሆን፣ በቀን ሁለት መቶ ሀምሳ ትራሶችን የማምረት አቅም አለው።
ተጨማሪTag Archives: ከፍታ
መስከረም ክበበው የቤት እና የቢሮ እቃዎች
የተመሠረተው በ 2006 ዓ.ም በወ/ሮ መስከረም ክበበው ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የቤት እና የቢሮ እቃዎች የሚያመርት ድርጅት ሲሆን ይህ ድርጅት በአስራ አምስት ቀን ሶስት መቶ ወንበሮችን በጥራት የማምረት አቅም አለው። እንደ ወንበሮቹ ዲዛይን ቀኑ ሊለያይ ይችላል። ድርጅቱ በአሁን ጊዜ ለዐሥራ አራት ቋሚ እና ሁለት ጊዜያዊ ሠራተኞች የሥራ እድል መፍጠር ችሏል።
ተጨማሪውብ ፊኒሺንግ ሶሉሽንስ
ውብ ፊኒሺንግ ሶሉሽንስ የተመሠረተው በ 2011 ዓ.ም በአቶ ካሊድ አብዲ እና ሁለት መሥራች አባላት ነው። ውብ ፊኒሺንግ አጠቃላይ የፊኒሽንግ ሥራዎችን የሚሠራ ድርጅት ነው። ከድርጅቱ ምሥረታ በፊት አቶ ካሊድ ከጓደኞቻቸው ጋር ለሦስት አመት በትውውቅ (በሰው በሰው) ሥራውን ሲሠሩ ከቆዩ በኋላ ተደራጅተን በሙሉ አቅም ብንሠራ ደግሞ የተሻለ ተጠቃሚ እንሆናለን በማለት ነበር ድርጅቱን …
ተጨማሪኤርታሌ ማኑፋክቸሪንግ ማሽነሪ እና ግንባታ ግብዓት አምራች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር
ኤርታሌ ማኑፋክቸሪንግ ማሽነሪ እና ግንባታ ግብዓት አምራች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተመሠረተው በአቶ በፍርዱ ሠይፉ እና በዐሥራ አራት አባላት 1996 ዓ.ም መጨረሻ ነበር። ይህ ማኅበር የማኑፋክቸሪንግ እና የኮንስትራክሽን ሥራዎች የሚሠራ እንዲሁም ሰላሳ የወፍጮ ማሽን ሞልዶች ለወፍጮ ድንጋይ ማምረቻ እና በጣም ዘመናዊ የብረት ማቅለጫ ያለው ድርጅት ነው።
ተጨማሪታደለ ፋስት ፉድስ
ታደለ ፋስት ፉድስ በ 2010 ዓ.ም መጨረሻ ላይ ነው የተመሠረተው። ድርጅቱ ፈጣን (ቶሎ የሚደርሱ) ምግቦችን በሁለት ደቂቃ ውስጥ የሚያደርስ ድርጅት ነው። ይህ ድርጅት የተለያዩ ሳንድዊቾችን ለተገልጋይ በሁለት የተለያየ መንገድ ያቀርባል፦ ምግቡን ይዞ መሄድ የሚፈልግ ይዞ ይሄዳል፤ እዛው አረፍ ብሎ መመገብ የሚፈልግ ደግሞ ይመገባል። ታደለ ፋስት ፉድስ ፈላፈል ሳንድዊችን በአዲስ አበባ …
ተጨማሪብሩክ ኤፍሬም እና ጓደኞቻቸው ቀርከሃ፣ እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ
ድርጅቱ የተመሠረተው በ 2013 ዓ.ም በአቶ ብሩክ ወልደ ሐዋርያት እና አራት መሥራች አባላት በአንድ ሺህ አምስት መቶ ብር ካፒታል ነው። የሚያመርታቸው ምርቶች የቀርከሃ እና አጠቃላይ የእንጨት ሥራዎችን ነው። ድርጅቱ በቀን ሰላሳ ወንበር የማምረት አቅም አለው።
ተጨማሪ2merkato ሥራችንን ያለንበት ቦታ ድረስ ያመጣልናል – ቢዝነስ ሕትመት እና ማስታወቂያ
ቢዝነስ ማስታወቂያ የተመሠረተው በ2004 ዓ.ም ሲሆን፣ የተመሠረተውም የግል ኢንተርፕራይዝ ሆኖ በአቶ ቢሆነኝ ዘመነ ነበር። ድርጅቱ ሲመሠረት ሥራው ብዙም አስቸጋሪ አልነበረም። ቢዝነስ ማስታወቂያ የሰባት ዓመት ጊዜ ያስቆጠረ ቢሆንም በጥሩ ሁኔታ መንቀሳቀስ የጀመረው ግን በ2009 ዓ.ም ነው። ምሥረታና ዕድገት የድርጅቱ መሥራች የሆኑት አቶ ቢሆነኝ ወደ ሕትመት ሥራ ከመግባታቸው በፊት ኢንጂነር የመሆን ህልም ነበራቸው። …
ተጨማሪኢሜይልን እንዴት አድርገን ለቢዝነስ መጠቀም እንችላለን?
በዚህ ዘመን መልዕክቶችን በቴሌግራም፣ በፌስቡክ ሜሴንጀር፣ በዋትስአፕ፣ በቫይበር፣ በዊቻት እና በመሳሰሉት መለዋወጥ ይቻላል፤ ቢሆንም ኢሜይል ለቢዝነስ ወሳኝ እና ከሌሎች ኢንተርኔትን ተጠቅመን ከምንልካቸው መልዕክቶች የበለጠ መደበኛ (formal) የሆነ የመልዕክት መለዋወጫ ዘዴ ነው። በተለይ ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር ስንሠራ (ጨረታም ሆነ የኢምፖርት/ኤክስፖርት ቢዝነስ) በኢሜይል በትክክል መልዕክት መለዋወጥ መቻል በጣም አስፈላጊ ነው። አንዳንድ …
ተጨማሪከፍታ ማዕከል በስዊድን እና ኔዘርላንድስ ኤምባሲዎች እና የአውሮፓ ኅብረት ልዑካን ቡድን ተጎበኘ
ሐሙስ መጋቢት 30፣ 2013 ዓ.ም የከፍታ ማዕከል ከስዊድን እና ከኔዘርላንድስ ኤምባሲዎች፣ እንዲሁም ከአውሮፓ ኅብረት የኢትዮጵያ ልዑክ የመጡ ጎብኚዎችን አስተናግዷል። ጉብኝቱ የተካሄደው የከፍታ አጋር በሆነው የኔዘርላንድስ በጎ አድራጎት ድርጅት ኤስኤንቪ (SNV) እና ከሴቶች እና ወጣቶች ጋር በተያያዘ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ሊዌይ (LI-WAY) አስተባባሪነት ነው። በጉብኝቱ ወቅት ለተገኙት በኢትዮጵያ የስዊድን አምባሳደር ሃንስ …
ተጨማሪ