መነሻ / Tag Archives: addis ababa (page 4)

Tag Archives: addis ababa

መአዛ የጽዳት ዕቃዎች

ኡቡንቱ ኤራ ኅ.የተ.የግ.ማኅበር የተመሠረተው በወ/ሮ መአዛ ታምራት በ2008 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የንጽህና መጠበቂያ እና የጽዳት ዕቃዎችን  በጥራት እና በተመጣጣኝ ዋጋ በማምረት ለገበያ ያቀርባል።

ተጨማሪ

ወይንሸት፣ ፍቅርተ እና ጓደኞቻቸው የቀርከሃ ሥራ

ወይንሸት፣ ፍቅርተ እና ጓደኞቻቸው የቀርከሃ ሥራ ኅብረት ሽርክና ማኅበር የተመሠረተው በወ/ሮ ፍቅርተ ገብሬ እና ሁለት መሥራች አባላት በ2009 ዓ.ም. ነው። የቤት ማስዋቢያ እቃዎች እንዲሁም ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ የፈርኒቸር ሥራዎችን ከእንጨት ውጤቶች ጋር በማቀናጅት (በማመሳጠር) ያመርታል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ የወንድ እና የሴት ጌጣጌጥ ምርቶችን (ማጌጭያዎችን) ያመርታል።

ተጨማሪ

ሮቢ ጋርመንት

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ሮቤል ነጋሽ በ2008 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ በዋናነት የሚሠራው የወንዶች ሙሉ ልብስ ሲሆን በዚህም ሥራ በጣም የዳበረ እና የረዥም ጊዜ ልምድ አለው። ከዚህ በተጨማሪ አጠቃላይ አልባሳትን ያመርታል።

ተጨማሪ

አጋፔ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሰረታዊ ህብረት ሥራ ማህበር

ኅብረት ሥራ ማህበር ማለት ሰዎች የጋራ ፍላጎታቸውን ለማሳካት ያላቸውን እውቀት፣ ጉልበት፣ ጊዜ እና ሀብት በማሰባሰብ ችግሮቻቸውን መፍታት የሚያስችል ቁልፍ መሣሪያ ነው። በዚህ መሠረት አጋፔ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ መሥራች አባላት በሕጋዊ መንገድ የተመሠረተ ኅብረት ሥራ ማኅበር ነው።

ተጨማሪ

ቤተሰብ የገንዘብ ብድርና ቁጠባ ተቋም

ቤተሰብ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር የኅብረት ሥራ ማኅበራትን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 985/2009 መሠረት የተቋቋመ ሕጋዊ ድርጅት ነው። ማኅበሩ ዝቅተኛውን የማኅበረሰብ ክፍልን እና የሥራ ፈጣሪዎችን በተለይ ሴቶችን ማዕከል በማድረግ የጋራ በሆኑት ዕሴቶች ላይ ማለትም ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ችግሮቻቸውን ለመፍታት እንዲችሉ የተቋቋመ የኅብረት ሥራ ማኅበር ነው።

ተጨማሪ

መንሽ የግብርና ማሺነሪ፣ መሣርያዎች ሌሎች የብረት ሥራዎች

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ውብሸት ደለለኝ እና በጓደኞቻቸው በ2002 ዓ.ም. ነው። የጤፍ መውቂያ ማሽን በዋናነት የሚያመርተው ምርት ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ የተለያዩ የእርሻ መሣሪያዎ ች(የግብርና መሣርያዎች)፣ የውሃ መሳቢያ እና መቆፈሪያዎች፣ የባዮ ጋዝ ምድጃዎች እና ማብላያዎች፣ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች እና ለትምህርት ቤት እና ለቢሮ የሚሆኑ የፈርኒቸር ምርቶችንም ያመርታል።

ተጨማሪ