የአዲስ አበባ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 205,477 የሥራ ዕድል ለከተማዋ ነዋሪዎች መፍጠሩን አስታወቀ።
ተጨማሪAddis Assefa
የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ የከተማ ግብርና መስፋፋት የሚቻሉባቸው መንገዶች ላይ ከባለሙያዎች ጋር መከሩ
የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በይፋዊ ትዊተር ገጻቸው በትናንትናው ዕለት እንዳሰፈሩት፣ ከከተማ ግብርና ባለሙያዎች እንዲሁም በዘርፉ ተሰማርተው ውጤታማ ሥራዎችን ከሠሩ ግለሰቦች ጋር ተወያይተዋል። ምክትል ከንቲባው፣ “በየቅጥር ጊቢያችንና በጠባብ መኖሪያዎች ላይ ጭምር እንዴት የከተማ ግብርና መተግበር እንደሚቻል ተወያይተናል” ሲሉ አሳውቀዋል።
ተጨማሪየቢዝነስ ምክር ፈላጊ መመዝገቢያ
የቢዝነስ ምክር ሰጪ መመዝገቢያ
የመስሪያ ቦታዎች ድጋፍ
መንግስት ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ከሚሰጣቸው ድጋፎች አንዱ፣ በራሱ (በመንግስት) በጀት ህንጻ፣ ወርክ ሾፕ እና ሼዶችን በመገንባት ለዕድገት ተኮር ዘርፎች በዝቅተኛ የኪራይ ዋጋ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ነው። የመስሪያ ቦታዎቹ የሚከተሉት መልኮች ሊኖራቸው ይችላል፡- ማምረቻ ህንጻ ወርክ ሾፖች ሼዶች (ማምረቻ) መሸጫ ሕንፃዎች፣ ተለጣፊ ሱቆች፣ መደብሮች፣ ኮንደሚኒየም ሱቆች እና ሼዶች የመስሪያ ቦታዎች ዓይነትና የሚሰጡት …
ተጨማሪሌሎች የብድርና ቁጠባ ተቋማት
በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከአዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም በተጨማሪ፣ ተከታዮቹ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት የቁጠባና የብድር አገልግሎት ይሰጣሉ። ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ተቋማቱን ማናገር ይችላሉ።
ተጨማሪ6131
ከጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ጋር የተያያዙ :- የኢንተርፕራይዝ ምሥረታና አደረጃጀት ፣ የኢንተርፕራይዞች ዕድገት ደረጃና ተያያዥ ጉዳዮች ፣ የባዛር ዝግጅቶች እና ጥቆማ ፣ እንዲሁም ሌሎች መረጃዎች ፣ ጥቆማዎች እና የመሳሰሉትን ለማግኘት 6131 ላይ መደወል ይችላሉ። በአሁኑ ጊዜ ፣ የጥሪ ማዕከላችንን አደራጅተን ጨርሰናል።
ተጨማሪጨረታ
የተለያዩ የጨረታ ማስታወቂያዎች እዚህ ያገኛሉ።
ተጨማሪ“የቢዝነስ ሰሌዳ” መጠቀም
የቢዝነስ ሰሌዳ (Business Canvas) አዲስ ሥራ ለመጀመር ለተነሣ የቢዝነስ ሰው/ ድርጅትም ሆነ ሥራ ላይ ለቆየ፣ ሥራን ውጤታማና ትርፋማ ለማድረግ ሁነኛ መሣሪያ ነው። የቢዝነስ ሰሌዳ፣ እንደ ቢዝነስ ማጤን ያለብንን ዋና ዋና ነገሮች እንዳንስት ይረዳል። ውጤታማና ትርፋማ ለመሆን፣ በሰሌዳው ላይ የተቀመጡትን ነጥቦች ልብ ማለት ይበጃል። ሰሌዳውን በወረቀት ላይ አትሞ፣ በእያንዳንዱ ነጥብ ሥር …
ተጨማሪየስኬታማ ሥራ ፈጣሪ (ኧንተርፕረነር) መለያዎች
አንድ ሰው የተሳካለት ሥራ ፈጣሪ ወይም ኧንተርፕረነር (አዲስና የተለየ የቢዝነስ ሃሳብ ወይም ዘዴ ይዞ የተነሣ) ለመሆን፣ የያዘው ሃሳብና ሃሳቡን ተግባራዊ ማድረጊያ ገንዘብ ወሳኝ መሆናቸው አይጠረጠርም። ሆኖም፣ እነዚህ ሁለቱ ብቻ ኧንተርፕረነሩ የተሳካለት የቢዝነስ ሰው እንዲሆን አያስችሉትም። ኧንተርፕረነር፣ ስኬትን መቀዳጀት እንዲችል ወይም ጉዞው ወደ ስኬት የሚገሰግስ እንዲሆን፣ ዓይነተኛ የሆኑ የሰብዕና መገለጫዎች ያስፈልጉታል። …
ተጨማሪ