መነሻ / Addis Assefa (page 2)

Addis Assefa

መንገዶች ባለሥልጣን በ10 ዓመታት የኢትዮጵያን ወረዳዎች ሁሉ በአስፋልት መንገዶች ለማገናኘት አቅጃለሁ አለ

በመጪዎቹ 10 ዓመታት ሁሉንም የኢትዮጵያ ወረዳዎች በአስፋልት መንገዶች ለማገናኘት እቅድ መያዙን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ። ከዚህም በተጨማሪ ከጎረቤት አገራት ጋር የሚያገናኙ መንገዶች ግንባታ ለማከናወንም መሪ እቅዱ ትኩረት እንደሚያደርግ ተገልጿል። ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በ10 ዓመቱ መሪ የልማት እቅድ ላይ እየተወያየ በሚገኘበት መድረክ ላይ እቅዱን አቅርቧል። ለሦስት ቀናት …

ተጨማሪ

ተቋርጦ የከረመው የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ተመለሰ

በኢትዮጵያ ላለፉት ሦስት ሳምንታት ዝግ ሆኖ የቆየው የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ተመለሰ። የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን መገደል ተከትሎ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በተከሰተው አለመረጋጋት ሳቢያ የኢትዮጵያ መንግሥት የመደበኛና የሞባይል ኢንትርኔት አገልግሎቶችን በመላዋ አገሪቱ እንዲቋረጥ አድርጎ መቆየቱ ይታወሳል። ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ የዋይ-ፋይ የኢንተርኔት አገልግሎት መመለሱ ይታወቃል። በርካታ ተጠቃሚ ያለው የሞባይል ኢንተርኔት …

ተጨማሪ

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በ19.9 ቢሊየን ብር 12 መንገዶች ሊያሠራ ነው

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በ19.9 ቢሊየን ብር ወጪ 12 መንገዶችን ለመገንባት የሚያስችል የውል ስምምነት ፊርማ ከተቋራጮች ጋር ተፈራርሟል። የስምምነት ፊርማ የተከናወነባቸው 12ቱ የመንገድ ፕሮጀክቶች በድምሩ 825.23 ኪ.ሜ ርዝመት ያላቸው መሆኑም ታውቋል። ለግንባታው ከሚያስፈልገው ወጪ መካከል የአሥሩ መንገዶች በኢትዮጵያ መንግሥት የተሸፈነ ሲሆን፣ ሁለቱ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብድር ነው ተብሏል። የውል ስምምነቱን ከፈረሙት …

ተጨማሪ

ሸገር ዳቦ በ400 ማከፋፈያዎች እየተሰራጨ ነው ተባለ

የሸገር ዳቦ በተመጣጣኝ ዋጋ በ400 ማከፋፈያዎች ለአዲስ አበባና አካባቢው ነዋሪዎች እየተሰራጨ እንደሚገኝ ተገለፀ። የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ ሲሳይ ደበበ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፣ ሸገር ዳቦ ፋብሪካ የሚያመርታቸውን ዳቦዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለነዋሪዎች ማሰራጨት ጀምሯል። ፋብሪካው በዋነኛነት የዳቦ ዋጋን የኅብረተሰቡን ገቢ ባገናዘበ አነስተኛ ዋጋ የማቅረብ ዓላማን ይዞ እንደመግባቱ ተደራሽነቱ ላይ በጥብቅ እየተሠራ መሆኑን …

ተጨማሪ

ሚድሮክ ኢትዮጵያ 5 ሊትር ዘይት በ330 ብር ለሸማቾች አቀረበ

ሚድሮክ ኢትዮጵያ ግሩፕ የምግብ ዘይት በተመጣጣኝ ዋጋ በአዲስ አበባ ከተማ እያቀረበ መሆኑን አስታወቀ። መንግስት በምግብ ዘይት ላይ የጣለውን ቀረጥ ከማንሣቱ ጋር ተያይዞ፣ 5 ሊትሩን የምግብ ዘይት በ330 ብር ለሸማቾች እየሸጠ እንደሚገኝም ገልጿል። የሚድሮክ ኢትዮጵያ ግሩፕ የንግድ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር በቀለ ጎላዶ እንዳሉት፣ መንግስት የሸማቶችን የኑሮ ጫና በመጋራት …

ተጨማሪ

ኢትዮጵያ የጎብኚዎች መዳረሻ ስፍራዎቿን በኦን ላይን ማስተዋወቅ ጀመረች

የኢትዮጵያን የጎብኚዎች መዳረሻ ስፍራዎች በኦን ላይን ማስተዋወቅ መጀመሩን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ የቱሪዝም ዘርፉ ኮሮና ወረርሽኝ ያሳደረበትን ተጽዕኖ የሚያገግምበትን አቅጣጫ በማስቀመጥ 3 በሊዮን ዶላር ለማግኘት ማቀዱን በሚኒስቴሩ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ተወካይ አቶ እንደገና ደሳለኝ ለኢዜአ ገልጸዋል። በተጠናቀቀው በጀት አመት በኢትዮጵያ ኮሮና ባስከተለው ቀውስ ከዘርፉ ለማግኘት ከታቀደው ሁለት ሦስተኛውን ገቢ …

ተጨማሪ

የቢዝነስ መመዘኛ ዘዴ

አንድ ቢዝነስ እንዲሰምር፣ ጠንካራ እና ደካማ ጎንን ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል። ከዚህም በመነሣት፣ ከጠንካራ ጎኑ የሚመነጩ ዕድሎችን፣ እንዲሁም ከደካማ ጎኑ የሚነሡ ሥጋቶችንም በቅጡ መረዳት አለበት። እንዲህ ሲሆን፣ ድካሙን አካክሶ፣ ጠንካራ ጎኖቹን አዳብሮ የተሳካ ቢዝነስን ማስኬድ ይችላል። ይህ ሃሳብ፣ የቢዝነስ ጠበብት በእንግሊዝኛው ምህጻረ ቃል “SWOT” ብለው የሚጠሩት የቢዝነስ ሂደት መመዘኛ መስፈርት ሆኖ …

ተጨማሪ

ግብ እንዴት ልቅረጽ?

ለቢዝነሳችንም ሆነ ለግል ሕይወታችን የት እና እንዴት መድረስ እንደምንፈልግ ግልጽ የሆነ ግብ መያዝ ከመባከን ያድነናል። ይሁን እንጂ ሰዎችም ሆኑ ቢዝነሶች ብዙ ጊዜ ግባቸውን ግልጽ በሆነ መንገድ ለማስቀመጥ ይቸገራሉ፤ አንዳንዴ እንደውም ጭራሽ ምንም ግብ ሳይቀርጹ ይቀራሉ። የትኛውም ዓይነት ግብ ሲቀረጽ፣ በሚከተለው መልኩ ቢሆን ለመቅረጽም፣ ለመከታተልም፣ እንዲሁም ለመተግበር ያመቻል። ይህ የግብ አቀራረጽ …

ተጨማሪ

አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ አቅርቦት የሚያገኙበት ዕድል

(ታምራት አበራ) በኢንተርፕራይዝ ተደራጅተው እየሠሩ ሥራዎን የሚያካሂዱበት ካፒታል እያጠርዎ ይቸገራሉ? ወይስ የሚሠሩበት ማሽን ኪራይ ራስ ምታት ሆኖብዎታል? ይህ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚገጥማቸው ትልቁ ችግር ነው። ይህንን ችግር ለመቅረፍ የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ፋይናንስ ፕሮጀክት ነገሬ ብሎ በመሥራት ላይ ይገኛል፤ የእርስዎ ኢንተርፕራይዝ መስፈርቱን የሚያሟላ ከሆነም ከፕሮጀክቱ የፋይናንስ …

ተጨማሪ