መነሻ / ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት / የግል ብድር እና ቁጠባ ተቋማት (page 3)

የግል ብድር እና ቁጠባ ተቋማት

ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተፕራይዞች ምዝገባ ከፈጸሙ በኋላ እንዲሁም ሥራቸውን እየሠሩ እያለ የፋይናንስ ድጋፍ ቢፈልጉ፣ ድጋፍ የሚያገኙባቸውን የግል ማይክሮፋይናንስ (የአነስተኛ ብድር እና ቁጠባ) ተቋማት አገልግሎቶች ዝርዝርን በዚህ ስር ያገኛሉ።

ብርሃን ለኢትዮጵያ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር

birhan-le-ethiopia-credi-saving-logo

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ብርሃን ለኢትዮጵያ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በአካል ሄዶ እና  በዌብሳይት በመመልከት በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ተጨማሪ

አዲስ ራፋይሰን የኅብረት ሥራ ሠራተኞች የገንዘብ ቁጠባና ብድር

addis-raiffeisen-logo

አዲስ ራፋይሰን የኅብረት ሥራ ሠራተኞች የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በ2003 ዓ.ም. በኅብረት ሥራ ሠራተኞችና ባለሙያዎች የተቋቋመ የኅብረት ሥራ የፋይናንስ ተቋም ነው። የኅብረት ሥራ ማኅበሩ የኅብረት ሥራ ባለሙያዎችና ሠራተኞችን በአባልነት በማቀፍ በዚህ ዘርፍ የተሻለ አስተዋፅኦ ለማበርከት የተቋቋመ ማኅበር ነው። ስሙን የወሰደው ከ Friedrich Wilhelm Raiffeisen ሲሆን፤ ራፋይሰን …

ተጨማሪ

የኛ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር

“የኛ ሁሌም የኛ የሁላችንም ነው!!” በሚል መሪ ቃል የሚታወቀው የኛ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የሚገኙ እና በትምህርት ደረጃቸው ዝቅተኛ የሆኑትን፣ እንዲሁም መካከለኛውን የኅብረተ ሰብ ክፍሎች በገንዘብ አስተዳደር እና አጠቃቀም እና በተለያዩ ሥልጠናዎች በማገዝ የኑሮና አኗኗር ለውጥን ለማምጣት እና ለመሥራት የተቋቋመ የገንዘብ ቁጠባና …

ተጨማሪ

“ዛሬ በመቆጠብ ነገን በተሻለ ህይወት ይኑሩ” – አፍሪካ ቪሌጅ ፋይናንሽያል ሰርቪስስ አ.ማ.

africafssc-logo

አፍሪካ ቪሌጅ ፋይናንሽያል ሰርቪስስ አ.ማ. በአዋጅ ቁጥር 626/2009 መሠረት ተቋቁሞ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ በማግኝት እ.ኤ.አ. ከ1999 ጀምሮ በኦሮሚያና በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ውስጥ ፋይናንስ ነክ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ የሚገኝ የፋይናንስ ተቋም ነው።

ተጨማሪ

ሃበሻ ኢንተርፕረነርስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ ኅብረት ሥራ ማኅበር

ሃበሻ ኢንተርፕረነርስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ ኅብረት ሥራ ማኅበር የኅብረት ሥራ ማኅበራትን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 985/09 መሠረት የተቋቋመ ሕጋዊ ድርጅት ነው።  የሥራ ፈጣሪዎች በአንድነት የጋራ የሆኑ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ችግሮቻቸውን ለመፍታት እንዲችሉም የተቋቋመ ማሕበር ነው፡፡

ተጨማሪ

ኑ ነገን ዛሬ እንሥራ – ፍኖት የገንዘብ ቁጠባና ብድር

finot-logo

ፍኖት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር ኅብረተ ሰቡ ከሚያገኘው ገቢ ላይ የተወሰነ ገንዘብ በመቆጠብ ራሱን በራሱ እንዲረዳና የቁጠባ ባህልን በማዳበር ፈጣን የሆነ የብድር አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ በ379 መስራች አባላት (307 ወንድ እና 72 ሴት) መጋቢት 15 ቀን፣ 2011 ዓ.ም. በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ተመሠረተ።

ተጨማሪ

ጆሽዋ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/ የኅብረት ሥራ ማኅበር

saving

ጆሽዋ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/ የኅብረት ሥራ ማኅበር በ1993 ዓ.ም ተመሥርቶ በብድር እና ቁጠባ ዘርፍ እየሠራ ያለ ማኅበር ነው። ከ24,000 በላይ አባላት እና ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ጠቅላላ ሀብት አለው። በቦሌ ደምበል (ኦሎምፒያ) አካባቢ በ1083 ካሬ ሜትር ላይ ባለ 4 ፎቅ ሕንጻ እና ለቢሮ ምቹ የሆኑ ተጨማሪ ክፍሎች ያሉት ግቢ …

ተጨማሪ