ኢትዮጵያ እና ዓለም ባንክ የ100 ሚሊየን ዶላር ብደር ስምምነት ተፈራረሙ ፕሮጀክቱ የገንዘብ እጥረት ያለባቸውን ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች ብድር የሚያገኙበትን መንገድ ለማመቻቸት እና የኮቪድ ወረርሽኝ ስራቸው ላይ ጉዳት ላደረሰባቸው ሴቶች የሚውል መሆኑንም ሚኒስትር ዲኤታዋ ተናግረዋል። የብድር ስምምነቱ በጥቃቅን እና አነስተኛ ስራ ዘርፍ ለተሰማሩ ሴት ስራ ፈጣሪዎች የሚውል ነው ተብሏል። የስምምነት …
ተጨማሪወቅታዊ መረጃ
የደቡብ ክልል የሥራ ዕድል ፈጠራ ምክር ቤት በሀዋሳ ከተማ ተመሰረተ
የደቡብ ክልል የሥራ ዕድል ፈጠራ ምክር ቤት መስራች ጉባኤ በሀዋሳ ተካሄደ። በጉባኤው ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የዘርፉ ባለድርሻ የተገኙበት እንደነበረ ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳየች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በጉባኤው የክልሉ ኢንተርፕራይዞች እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የስራ እድል ፈጠራ ምክር ቤት መስራች ጉባኤ ክልላዊ …
ተጨማሪበጃንሜዳ የነበሩ ነጋዴዎች ዛሬ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ በሚገኘው የገበያ ማዕከል አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ
በጃንሜዳ የነበሩ ነጋዴዎች ከዛሬ ጀምሮ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ በሚገኘው በላፍቶ የአትክልትና ፍራፍሬ የገበያ ማዕከል አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ። ይህንንም የተናገረው የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ነው።
ተጨማሪበአዲስ አበባ ከተማ ከመሬትና መሬት ነክ ከሆኑ ጉዳዮች ጋር ተቋርጦ የነበረው የአገልግሎት እገዳ ተነሳ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከመሬትና መሬት ነክ ከሆኑ ጉዳዮች ጋር ተቋርጦ የነበረው የአገልግሎት እገዳ ከህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ተነስቷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከነሀሴ 20 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ መሬትና መሬት ነክ የሆኑ ጉዳዮች አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ ማገዱ ይታወሳል። የከተማ አስተዳደሩ በመሬትና መሬት ነክ ጉዳዮች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን …
ተጨማሪመግቢያ የተሰኘ የዴሊቨሪ እና የቢዝነስ ሊስቲንግ መተግበሪያ አገልግሎት ላይ ዋለ
ኢቢዝ ኦንላይን ሶሉሽንስ ኃ.የተ.የግል ማኅበር “መግቢያ” (megbia.com) የተሰኘ አዲስ የሞባይል መተግበሪያ መልቀቁን አስታውቋል። ይህ መተግበሪያ ተጠቃሚዎች በአቅራቢያቸው የሚገኙ ቢዝነሶችን በቀላሉ እንዲያገኙ ከመርዳቱም በላይ፣ አዲስ አበባ ውስጥ ከየተኛውም ቦታ ሆነው ምግብ አዘው እንዲደርሳቸው ያስችላል። መተግበሪያው ሙሉ በሙሉ የተሠራው የኢትዮጵያ ትልቁ የቢዝነስ ፖርታል የ 2merkato.com ባለቤት በሆነው ድርጅት ባለሙያዎች ነው። ኢቢዝ በመቶዎች …
ተጨማሪስለ ‘ከፍታ’ ፖርታል የሚያስገነዝብ ሥልጠና እየተካሄደ ነው
የተወዳጁ 2merkato.com ባለቤት የሆነው ኢቢዝ ኦንላይን ሶሉሽንስ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር በአዲስ አበባ ከተማ ባሉ 120 ወረዳዎች ለሚገኙ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች እና የቡድን መሪዎች ሥልጠና እያካሄደ ነው። ኢቢዝ ‘SNV’ ከተባለው የኔዘርላንድስ የልማት ድርጅት ጋር በመሆን እና በአዲስ አበባ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ትብብር ለጥቃቅን …
ተጨማሪባለፉት ሶስት ወራት ከማዕድን ዘርፍ ከ178 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ተገኘ
ባለፉት ሶስት ወራት ከማዕድን ዘርፍ ከ178 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ መገኘቱን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢ/ር ታከለ ኡማ ተናገሩ። ይህንንም ያሉት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የሶስት ወራት አፈፃፀም በተመለከተ ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው። ወደ ውጭ ተልከው የውጭ ምንዛሬ ካስገኙት ማዕድናት መካከል ወርቅ፣ ታንታለም፣ ኳርትዝ፣ ኢመራልድ፣ ሳፋየር እና እምነበረድ ተጠቃሾች …
ተጨማሪየስራ እድል መፍጠር ቅድሚያ እና ልዩ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ
ለወጣቶች የስራ እድል የመፍጠር ጉዳይ ቅድሚያ እና ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ስራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። በተለያዩ ጊዜያት ለስራ ፈጠራ ተብለው የተበተኑ የወጣቶች ተዘዋዋሪ ፈንድ የብድር ገንዘብ በወቅቱ እንዲመለስ በማድረግ ለቀጣይ ወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ መልሶ ማበደር መቻል አለበትም ነው ያሉት። የአዲስ አበባ ከተማ የስራ እድል …
ተጨማሪበአዲስ አበባ በ2013 በጀት አመት 525 ኪሎ ሜትር የጥገና ስራ ይከናወናል
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በ2013 በጀት አመት በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች 525 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የአስፋልት፣ የድልድይ፣ የድሬይኔጅ፣ የአክሰስ መንገድ እና ሌሎች በርካታ ልዩ ልዩ የጥገና ስራዎችን ለማከናወን አቀደ፡፡
ተጨማሪየጥቃቅንና አነስተኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች ምርቶቻቸውን እንዲያሳድጉ ለማገዝ የገንዘብ ድጋፍ ተደረገ
የጥቃቅንና አነስተኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች ምርቶቻቸውን እንዲያሳድጉ ለማገዝ የታለመ የገንዘብ ድጋፍ ተደረገ። ስምምነቱ የተደረገው በኢትዮጵያ ንግድ እና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት፣ ፕሪሳይስ ኢንተርናሽናል ኮንሰልታንት እና የፈጠራ ድርጅት እንዲሁም የግሪን ኢትዮጵያ ማኑፋክቸሪንግ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ኢንተርፕራይዞች መካከል መሆኑ ተገልጿል። ድጋፉ በአምራች ዘርፍ ውስጥ የማያቋርጥ አፈጻጸም እና ቀጣይነት ያለው መሻሻል እንዲኖር ያደርጋል ተብሏል። በገንዘብ …
ተጨማሪ