ወቅታዊ መረጃ

በዚህ ሥር፣ ከጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ ልዩ ልዩ ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ።

የኢትዮጵያን የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ማሳደግ የሚያስችል ዘመቻ ይፋ ተደረገ

textile_leather

የጨርቃ ጨርቅ፣ አልባሳትና ቆዳ ኢንዱስትሪ የሰራተኞች ማህበር ፌዴሬሽን የኢትዮጵያን የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ማሳደግ የሚያስችል ዘመቻ ይፋ አደረገ። ዘርፉን ከማሳደግ ጎን ለጎን አሁን ላይ የጤና ስጋት ከሆነው ኮቪድ19 ጋር ተያይዞ በሃገር ውስጥ ባሉ ፋብሪካዎች የጤና እና የደህንነት የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራን ማከናወንም የዘመቻው አላማ ነው ተብሏል። አሁን ላይ ኢትዮጵያ በኮቪድ19 ምክንያት የእንቅስቃሴ …

ተጨማሪ

ለኢንተርፕራይዞች ብቻ የወጣ ጨረታ

Arada Sub City

የአራዳ ክፍለ ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት በክፍለ ከተማው ሊያሠራቸው የሚፈልጋቸውን ልዩ ልዩ የግንባታ ሥራዎች እንዲሠሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ብቻ የሚያሳትፍ ጨረታ አውጥቷል።

ተጨማሪ

የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ የከተማ ግብርና መስፋፋት የሚቻሉባቸው መንገዶች ላይ ከባለሙያዎች ጋር መከሩ

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በይፋዊ ትዊተር ገጻቸው በትናንትናው ዕለት እንዳሰፈሩት፣ ከከተማ ግብርና ባለሙያዎች እንዲሁም በዘርፉ ተሰማርተው ውጤታማ ሥራዎችን ከሠሩ ግለሰቦች ጋር ተወያይተዋል። ምክትል ከንቲባው፣ “በየቅጥር ጊቢያችንና በጠባብ መኖሪያዎች ላይ ጭምር እንዴት የከተማ ግብርና መተግበር እንደሚቻል ተወያይተናል” ሲሉ አሳውቀዋል።

ተጨማሪ

አንበሳ የከተማ አውቶቡስ ድርጅት 400 ያገለገሉ አውቶቡሶችን ለሥራ ዕድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዝ አስተላለፈ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔና በአንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ቦርድ ውሳኔ መሠረት 400 አገልግሎታቸውን የጨረሱ አውቶቡሶች ለሥራ ዕድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ተላልፈዋል፡፡ ከ20 ዓመታት በላይ አገልግሎት የሰጡት አውቶቡሶች ለኢንተርፕራይዙ የተላለፉትም፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ ጥቅም ላይ እንዲውሉ መሆኑን የድርጅቱ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ተሾመ ንጋቱ ተናግረዋል፡፡ በከተማዋ ከቅርብ ጊዜ …

ተጨማሪ