ኅብረት ሥራ ማህበር ማለት ሰዎች የጋራ ፍላጎታቸውን ለማሳካት ያላቸውን እውቀት፣ ጉልበት፣ ጊዜ እና ሀብት በማሰባሰብ ችግሮቻቸውን መፍታት የሚያስችል ቁልፍ መሣሪያ ነው። በዚህ መሠረት አጋፔ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ መሥራች አባላት በሕጋዊ መንገድ የተመሠረተ ኅብረት ሥራ ማኅበር ነው።
ተጨማሪTag Archives: ማይክሮፋይናንስ
አዲስ ራፋይሰን የኅብረት ሥራ ሠራተኞች የገንዘብ ቁጠባና ብድር
አዲስ ራፋይሰን የኅብረት ሥራ ሠራተኞች የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በ2003 ዓ.ም. በኅብረት ሥራ ሠራተኞችና ባለሙያዎች የተቋቋመ የኅብረት ሥራ የፋይናንስ ተቋም ነው። የኅብረት ሥራ ማኅበሩ የኅብረት ሥራ ባለሙያዎችና ሠራተኞችን በአባልነት በማቀፍ በዚህ ዘርፍ የተሻለ አስተዋፅኦ ለማበርከት የተቋቋመ ማኅበር ነው። ስሙን የወሰደው ከ Friedrich Wilhelm Raiffeisen ሲሆን፤ ራፋይሰን …
ተጨማሪሃበሻ ኢንተርፕረነርስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ ኅብረት ሥራ ማኅበር
ሃበሻ ኢንተርፕረነርስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ ኅብረት ሥራ ማኅበር የኅብረት ሥራ ማኅበራትን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 985/09 መሠረት የተቋቋመ ሕጋዊ ድርጅት ነው። የሥራ ፈጣሪዎች በአንድነት የጋራ የሆኑ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ችግሮቻቸውን ለመፍታት እንዲችሉም የተቋቋመ ማሕበር ነው፡፡
ተጨማሪግሎባል የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/የኅብረት ሥራ ማኅበር
ግሎባል የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/የኅብረት ሥራ ማኅበር በአዋጅ 985/2009 እና ይህን አዋጅ ለማስፈጸም በወጡ ደንቦች መሠረት የተቋቋመት የኅብረት ሥራ ማኅበር ነው።
ተጨማሪሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም
ሸገር ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. በብዙሃን የግል ባለሃብቶች እና በግል ኩባንያዎች የተቋቋመና በብሔራዊ ባንክ ፍቃድ ያገኘ፣ በፋይናንስ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ተሞክሮና እውቀት ባካበቱ የሥራ ኃላፊዎች የሚመራ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም ነው። በአሁኑ ወቅት ቅርንጫፎቹን በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መቀመጫ በሆነችው ፊንፊኔ (አዲስ አበባ) እና በሌሎች በክልሉ በሚገኙ ከተሞች በማስፋፋት የኅብረተ ሰቡን …
ተጨማሪአዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም
አዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም አክሲዮን ማኅበር በአዋጅ ቁጥር 40/1988 ዓ.ም. መሠረት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ በማግኘት በስድስት የአክሲዮን ባለቤቶች የብድርና ቁጠባ አገልግሎት ለመስጠት እ.አ.አ ጥር 27 ቀን፣ 2000 ዓ.ም. በከተማው ያለውን ሥራ አጥነት ለመቅረፍና ድህነትን ለመቀነስ ዓላማ አድርጎ የተቋቋመ ተቋም ነው። በአሁን ሰዓት በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 626/2009 እየሠራ የሚገኝ እና …
ተጨማሪግራንድ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ.
ግራንድ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች በከተማና በገጠር የሚኖሩ ለሥራ ተነሻሽነት ያላቸው ዜጎች በተለይም የባንክ አገልግሎት ዕድል ለተነፈጉ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ነጋዴዎችና አርሶ አደሮች የፋይናንስ አገልግሎቶችን ለመስጠት ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ በማግኘት የተቋቋመ ተቋም ነው። ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ግራንድ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ …
ተጨማሪሀርቡ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም
ሀርቡ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. በ2005 ዓ.ም. በፋሲሊቴተር ፎር ቼንጅ (መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም) ድጋፍ አማካኝነት የተቋቋመ ተቋም ነው። ሀርቡ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. የዕሴት ሰንሰለት ልማት እና የፋይናንስ አገልግሎቶችን ተደራሽነት በመደገፍ የግብርና ምርታማነትን እና የግብርና ግብይትን ለማሳደግ ያለመ ነው። ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ሀርቡ ማይክሮ ፋይናንስ በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው …
ተጨማሪ“ዛሬ የቆጠቡት አነስተኛ ገንዘብ ለነገው ሀብት የመሠረት ድንጋይ ነው።” የምሥራች ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ.
የምሥራች ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ. ለማኅበረሰቡ በዋናነት የአክሲዮን ሽያጭ፣ የቁጠባ አገልግሎት እና የብድር አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ለጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ የሚሆኑ ብድሮችንም አዘጋጅቷል። አግልግሎቱንም አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ ስድስት ቅርንጫፎች ይሰጣል። ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው የምሥራች ማይክሮ ፋይናንስ በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም …
ተጨማሪጋሻ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አክስዮን ማኅበር
ጋሻ አነስተኛ የፋይናንስ (ማይክሮፋይናንስ) ተቋም አክስዮን ማኅበር በአነስተኛ ንግድ ላይ ለተሰማሩ እንዲሁም ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የኅብረተ ሰብ ክፍሎች የብድር፣ የቁጠባ እና የአረቦን አገልግሎት ለመስጠት በ1990 ዓ.ም. ተቋቋመ። ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ለጋሻ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አክስዮን ማኅበር በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ …
ተጨማሪ