ሞዛይክ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተመሠረተው በአቶ ሳሙኤል ገዛህኝ እና በአቶ ጌትነት ካሳ መስከረም 2009 ዓ.ም ነው። ድርጅቱ ደረጃ ስምንት ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ሲሆን የሚቀበላቸውን ሥራዎችን በጊዜ ገደባቸው እና በጥራት ሠርቶ ያስረክባል።
ተጨማሪTag Archives: ሥራ እድል ፈጠራ
ይትባረክ ላቀው ልብስ ስፌት
ይትባረክ ላቀው ልብስ ስፌት የተመሠረተው የግል ኢንተርፕራይዝ ሆኖ በአቶ ይትባረክ ላቀው በ2009 ዓ.ም ነው። ድርጅቱ በዋናነት የሚያመርታቸው ምርቶች የሴቶች እና የህጻናት አልባሳት ሲሆኑ ለህጻናት ከአንድ ዓመት አስከ ስምንት ዓመት ለሚደርሱ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ምርቱን በብዛት ያመርታል። ከዚህ በተጨማሪ አጠቃላይ የአልባሳት ሥራዎችን ይሠራል።
ተጨማሪነቢያት አስረሳኸኝ እንጨት እና ብረታ ብረት
ነቢያት አስረሳኸኝ እንጨት እና ብረታ ብረት የተመሠረተው በ 1998 ዓ.ም ነው። የተመሠረተውም በአቶ ነብያት እና ዘጠኝ መሥራች አባላት ነበር። ነገር ግን በተፈጠሩ የተለያዩ አለመግባባቶች እና በነበሩ ብዙ ፈታኝ ሁኔታዎች አንዳንድ አባላት የሥራ ቦታ በመቀየራቸው፣ አንዳንድ አባላት ደግሞ የተሻለ እድል በመፈለጋቸው እና በተለያዩ ምክንያቶች በአሁን ጊዜ ሦስት አባላት ብቻ በድርጅቱ ውስጥ …
ተጨማሪቴዎድሮስ አባይ የኤሌክትሮኒክስ እና ስፖርት እቃዎች አቅራቢ
ድርጅቱ የተመሠረተው በ 2005 ዓ.ም መጨረሻ በአቶ ቴዎድሮስ አባይ ነው። ይህ ድርጅት የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን እና የስፖርት እቃዎችን የሚያቀርብ ድርጅት ሲሆን የኤሌክትሮኒክስ እና የስፖርት እቃዎችን በበቂ ብዛት እና ጥራት የማቅረብ አቅም አለው።
ተጨማሪብሩክ እና አስማረች ኮንስትራክሽን እና ማኑፋክቸሪንግ
ብሩክ እና አስማረች ኮንስትራክሽን እና ማኑፋክቸሪንግ የተመሠረተው በ 1996 ዓ.ም በ አቶ ብሩክ ዘውዴ እና ዐሥራ አራት መሥራች አባላት ነው። ድርጅቱ ከተግባረ ዕድ የቴክኒክ እና ሙያ ት/ቤት ጋር በመተባበር ብዙ የፈጠራ ሥራዎችን ሠርቷል እየሠራም ይገኛል። እንዲሁም ትልልቅ የማኑፋክቸሪንግ ማሽኖችን በመሥራት ለገበያ ያቀርባል። ቆየት ላሉ ማሽኖች ደግሞ የጥገና አገልግሎት ይሰጣል።
ተጨማሪኤን ደብሊው አልሙኒየም እና ብረት ሥራ
ኤን ደብሊው አልሙኒየም እና ብረት ሥራ የተመሠረተው በ 2004 ዓ.ም. በሁለት መሥራች አባላት ነው። ድርጅቱ ሁለት ዓመታት በጥሩ ሁኔታ ምርት ሲያመርት መቆየቱን የድርጅቱ መሥራች አባል የሆኑት አቶ ነጋሽ ወንድምአገኝ አስረድተዋል። የአቶ ነጋሽ በሙያው ተገቢ የሥራ ልምድ መኖር፣ እንዲሁም ከድርጅቱ ምሥረታ በፊት የነበራቸው የስድስት አመት የሥራ ልምድ እና የቀለም እውቀት ተደምሮ …
ተጨማሪቴዎድሮስ፣ ኤልያስ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት
ቴዎድሮስ፣ ኤልያስ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ የተመሠረተው በ2008 ዓ.ም መጨረሻ ሲሆን፤ በጥሩ ሁኔታ ምርት የማምረት ሂደት የጀመረው በ2009 ዓ.ም ነው። ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ቴዎድሮስ ይሉ እና በአራት መሥራች አባላት ነው። ድርጅቱ ሲመሰረት ጠንካራ እንዲሆን ያደረገው ሁሉም የድርጅቱ መሥራች አባላት በአንድ የእድሜ ክልል እና የኢንጂነሪንግ ትምህርት ምሩቅ መሆናቸው …
ተጨማሪየሚያውቁትን ሥራ መሥራት ለውጤታማነት – ውብዓለም ፈቃደ እና ጓደኞቻቸው የእንጨት ሥራዎች
ውባዓለም ፈቃደ እና ጓደኞቻቸው የእንጨት ሥራዎች የተመሠረተው በአቶ ፈቃደሥላሴ ግርማ እና በአራት መሥራች አባላት በ2006 ዓ.ም ነው። ድርጅቱ የቤት እና የቢሮ እቃዎችን እንዲሁም አጠቃላይ የእንጨት ሥራዎችን ቃል በገባው ጊዜ አምርቶ ያስረክባል። በአምስት መስራች አባላት የተመሠረተው ድርጅት በአሁኑ ወቅት አስር ጊዜያዊ ሠራተኞች ያሉት ሲሆን በአንድ ቀን አምስት አልጋዎችን በጥራት የማምረት አቅም …
ተጨማሪየትጋት ውጤት – ኤርሚያስ ከበደ ጠቅላላ የእንጨት ሥራ ድርጅት
ኤርሚያስ ከበደ ጠቅላላ የእንጨት ሥራ ድርጅት የተመሠረተው በ2000 ዓ.ም በአቶ ኤርሚያስ ከበደ ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የቤት እና የቢሮ እቃዎችን በጥራት ያመርታል። ድርጅቱ ከሶስት እስከ አምስት የሚደርሱ ፎቆችን (የወረዳ ህንጻ አይነቶችን) ሙሉ በሮች እና መስኮቶች ከዐሥራ አምስት እስከ ሀያ ቀን ድረስ የማምረት አቅም ያለው ሲሆን እንዲሁም የመኖሪያ ቤት ከአምስት እስከ ስምንት የሚደርሱ በሮች …
ተጨማሪአጸደ፣ ነሲባ እና ጓደኞቻቸው የእንጀራ መጋገር ሥራ
ይህ ኢንተርፕራይዝ የተመሠረተው በ 2001 ዓ.ም በ ወ/ሮ ነሲባ ራህመቶ እና በዐሥራ ዘጠኝ መሥራች አባላት ነው። ድርጅቱ በሀያ መሥራች አባላት ቢመሰረትም በነበረው አስቸጋሪ ሁኔታ ዘጠኝ አባላት የቀን ሥራ ብንሠራ ይሻለናል ብለው ሲያቋርጡ፣ አንድ አባል ደግሞ በሞት ስለተለየች በአሁን ጊዜ ዐሥር መስራች አባላት በድርጅቱ ውስጥ ይገኛሉ።
ተጨማሪ