መነሻ / Tag Archives: experience sharing (page 4)

Tag Archives: experience sharing

ዮሴፍ እና መስፍን የአልሙኒየም ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ዮሴፍ ንጉሤ እና በጓደኛቸው 2011 ዓ.ም. የኅብረት ሽርክና ማኅበር ሆኖ ነው። ማኅበሩ አጠቃላይ የአልሙኒየም ሥራዎችን በጥራት እና በተጠጣጣኝ ዋጋ የማምረት እና የመገጣጠም ሥራ ይሠራል።

ተጨማሪ

ሰንፔር ኮምፒዩተር ሶሉሽንስ ኃ.የተ.የግ.ማ.

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ዋሲሁን ድጋፉ እና በጓደኛቸው በ2005 ዓ.ም. ነው። ሰንፔር ኮምፒዩተር ሶሉሽንስ የሚሠራው በቴክኖሎጂ ላይ ሲሆን ይህም ኮምፒዩተር ጥገና፣ ኔትወርኪንግ፣ እና የተለያዩ ሶፍትዌሮች እና ዌብሳይቶችን በማልማት (develop በማድረግ) ለሚፈልገው ተጠቃሚ ያቀርባል።

ተጨማሪ

ሰኢድ ሃሰን ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ሰኢድ ሃሰን በ2012 ዓ.ም. የግል ኢንተርፕራይዝ ሆኖ ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የኮንስትራክሽን ሥራዎችን የሚሠራ ድርጅት ሲሆን በይበልጥ ደግሞ በፊኒሺንግ ሥራዎችን ላይ በሰፊው ይሳተፋል።

ተጨማሪ

ዐይናለም የዕደ ጥበብ ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በወ/ሮ አይናለም ሀብትህ ይመር እና ሦስት ጓደኞቻቸው በ2007 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ የሚያመርታቸው ምርቶች በሦስት ዘርፎች ሲሆኑ እነሱም ዕደ ጥበብ፣ የፈርኒቸር ሥራ እና የብረት ሥራዎች ናቸው።

ተጨማሪ

ጀንዲ ሌዘር

jendi-leather-logo

ድርጅቱ የተመሠረተው በወይዘሪት ናዲያ ይመር በ2012 ዓ.ም. ነው። ጀንዲ ሌዘር ጥራት ያላቸውን የቆዳ ውጤቶች በማምረት እና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ራሱን እና ማኅበረ ሰቡን እየጠቀመ ይገኛል። ወደ ፊት ደግሞ ለተጨማሪ ዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር እንዲሁም የሚያመርታቸውን ምርቶች ወደ ውጭ ሃገር በመላክ ለሃገሪቱ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት የበኩሉን አስተዋፅዖ የማበርከት እቅድ አለው።

ተጨማሪ

አብዲ፣ ከኪያ እና ጓደኞቻቸው የሌዘር ምርቶች

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ አብዲ ድሪባ 2012 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ነው። የሚያመርታቸው ምርቶች ጥራታቸውን የጠበቁ አጠቃላይ የቆዳ ምርቶች እንደ ጫማ፣ ጃኬት እና ቦርሳዎችን  ሲሆን፣ እንዲሁም ለቆዳ ሥራ የሚውል ጥሬ እቃ ያቀርባል።

ተጨማሪ

ካታሊስት ላብ ትሬዲንግ

ድርጅቱ የተመሠረተው በ2012 ዓ.ም. መጨረሻ በወ/ት ሠርካለም ተሰማ የግል ኢንተርፕራይዝ ሆኖ ነው። ድርጅቱ የላብራቶሪ እቃዎችን እና የትምህርት መርጃ መሣሪያዎችን ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ዩኒቨርሲቲዎች ያቀርባል።

ተጨማሪ