ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ አብዲ ድሪባ 2012 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ነው። የሚያመርታቸው ምርቶች ጥራታቸውን የጠበቁ አጠቃላይ የቆዳ ምርቶች እንደ ጫማ፣ ጃኬት እና ቦርሳዎችን ሲሆን፣ እንዲሁም ለቆዳ ሥራ የሚውል ጥሬ እቃ ያቀርባል።
ተጨማሪልምድ እና ተሞክሮ
ካታሊስት ላብ ትሬዲንግ
ድርጅቱ የተመሠረተው በ2012 ዓ.ም. መጨረሻ በወ/ት ሠርካለም ተሰማ የግል ኢንተርፕራይዝ ሆኖ ነው። ድርጅቱ የላብራቶሪ እቃዎችን እና የትምህርት መርጃ መሣሪያዎችን ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ዩኒቨርሲቲዎች ያቀርባል።
ተጨማሪዋቢ ጋርመንት
ፈለቁ አያሌው ልብስ ስፌት (ዋቢ ጋርመንት) የተመሠረተው በወ/ሮ ፈለቁ 2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ በአሁን ሰዓት በዋናነት የሚያመርታቸው ልብሶች የህጻናት ቱታ እና ቬሎዎችን በስፋት እያመረተ ይገኛል።
ተጨማሪየበጋእሸት አሰፋ እና ጓደኞቻቸው ብረታ ብረት ሥራ
ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ የበጋእሸት ገብሬ እና አራት መሥራች አባላት 2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ የሚያመርታቸው ምርቶች አጠቃላይ የብረታ ብረት ሥራዎች እንዲሁም የማሽነሪ ሥራዎች ናቸው።
ተጨማሪኒዮን ቢልዲንግ ኮንትራክተር
ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ሁሴን ፍቃዱ የግል ኢንተርፕራይዝ በመሆን በ2008 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች አጠቃላይ ኮንስትራክሽን፣ ሕንጻ ግንባታ እና የውሃ ሰፕላይ ሥራዎችን ይሠራል።
ተጨማሪውለታው ብዙ እንጨት፣ ብረታ ብረት እና አልሙኒየም ሥራ
ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ውለታው ብዙ እና በሦስት ባልደረቦቻቸው በ 2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የእንጨት፣ ብረታ ብረት እና አልሙኒየም ሥራዎችን በጥራት እና በታማኝነት የመሥራት አቅም አለው።
ተጨማሪአብያት የኢንጂነሪንግ እና አርክቴክቸር አማካሪ
አብያት ኮንሰልቲንግ የተመሠረተው በአቶ ናትናኤል እና በሶስት መሥራች አባላት 2012 ዓ.ም ላይ ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የኢንጂነሪንግ እና አርክቴክቸር ሥራዎች የማማከር አገልግሎት ይሠጣል።
ተጨማሪዮዲ ሳሙና
ዮዲ ሳሙና የተመሠረተው በአቶ ተስፋዬ በፍቃዱ እና አራት መሥራች አባላት በ 2012 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈሳሽ ሳሙና እና ደረቅ ሳሙና ምርቶችን ያመርታል።
ተጨማሪቢ ኤም ኤች ጋርመንት
ድርጅቱ የተመሠረተው በ2006 ዓ.ም በአቶ ብርሃን ዲባባ እና በሁለት መሥራች አባላት ነው። ይህ ድርጅት የሚያመርታቸው ምርቶች አጠቃላይ የአልባሳት አይነቶች ናቸው።
ተጨማሪመንግሥቱ የቆዳ ውጤቶች
ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ መንግሥቱ ሺፈራው በ2008 ዓ.ም. ነው። አቶ መንግሥቱ በቆዳ ውጤቶች፣ በቀበቶ እና በተለያዩ የጫማ ሥራዎች ላይ የሰላሣ ዓመት የሥራ ልምድ አካብተዋል።
ተጨማሪ