መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ (page 2)

ልምድ እና ተሞክሮ

በዚህ ገጽ ሥር፣ በሥራቸው ውጤታማ የሆኑ ኢንተርፕራይዞች ተሞክሮ ይቀርባል። ታሪካቸው ከሚወሳው ኢንተርፕራይዞች ጉዞ፣ ለእርስዎ የሚጠቅሙ ተግባራዊ የሆኑ አስተውሎቶች፣ ምክሮች እና ጥቆማዎችን ያገኛሉ። በሥራችሁ ውጤታማ ከሆናችሁ፣ ንገሩንና እዚህ ገጽ ላይ እናወጣችኋለን። ታሪካችሁ ሌሎችን ያስተምራል፣ ቢዝነሳችሁንም ያስተዋውቃል። በ6131 ወይንም በ 0975616161 ደውሉልን።

ከበደ ደስታው እና ጓደኞቻቸው የፊኒሺንግ ሥራ

ከበደ ደስታው እና ጓደኞቻቸው የፊኒሺንግ ሥራ ድርጅት የተመሠረተው በአቶ ከበደ ደስታው እና ሦስት መሥራች አባላት በ2010 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን እና የፊኒሺንግ ሥራዎችን ከውሃ ሥራ ውጪ የሚሠራ ድርጅት ነው።

ተጨማሪ

ቤስ ማኑፋክቸሪንግ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ሲሳይ ደጉ እና በባልደረባቸው ወ/ሮ ቤተልሔም በ2007 ዓ.ም. ነው። ቤስ የተለያዩ ማሽኖች የሚያመርት እና ጠቅላላ የብረታ ብረት ሥራዎችን የሚሠራ ድርጅት ነው።

ተጨማሪ

ሆሞዶ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ

ሆሞዶ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ የተመሠረተው በአቶ ዘላለም ሙላቱ እና በጓደኛቸው በ2010 ዓ.ም. ነው።  ሆሞዶ አጠቃላይ የኮንስትራክሽን ሥራዎችን ከውሃ ሥራ በስተቀር የሚሠራ ድርጅት ነው።

ተጨማሪ

እልልታ ሳሙና እና ዲተርጀንት ማምረቻ

እልልታ ሳሙና እና ዲተርጀንት ማምረቻ የተመሠረተው በወይዘሮ አዲስ ሕይወት እና አራት መሥራች አባላት በ2014 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ የተለያዩ የንጽህና ውጤቶችን የሚያመርት ድርጅት ነው።

ተጨማሪ

ታፍ ሌዘር

taf-leather

ታፍ ሌዘር የተመሠረተው በ 2004 ዓ.ም. በወይዘሮ ትዝታ አሰፋ እና በስድስት ሴት መሥራች አባላት ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የቆዳ ውጤት የሆኑ ምርቶችን ያመርታል።

ተጨማሪ

ብራይት ማኑፋክቸሪንግ

bright_manufacturing_logo

ብራይት ማኑፋክቸሪንግ የተመሠረተው በአቶ ሠለሞን መገርሳ እና በሁለት ጓደኞቻቸው በ2021 (እ.ኤ.አ.) ነው። ድርጅቱ የእንሰት ተክልን በመጠቀም ከግሉተን ነጻ (gluten free) የሆነ ስታርች እና የፋይበር ምርቶችን ያመርታል። እነዚህም ምርቶች ለተለያዩ ተጠቃሚ ደንበኞች፣ የግብርና ውጤት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች፣ ሱፐርማርኬቶች እና የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ያቀርባል። በቅርቡም ወደ ውጭ ሀገር ምርቱን ለመላክ (export ለማድረግ) አውሮፓ …

ተጨማሪ