መነሻ / Tag Archives: kefta (page 12)

Tag Archives: kefta

ኤርታሌ ማኑፋክቸሪንግ ማሽነሪ እና ግንባታ ግብዓት አምራች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር

ኤርታሌ ማኑፋክቸሪንግ ማሽነሪ እና ግንባታ ግብዓት አምራች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተመሠረተው በአቶ በፍርዱ ሠይፉ እና በዐሥራ አራት አባላት 1996 ዓ.ም መጨረሻ ነበር። ይህ ማኅበር የማኑፋክቸሪንግ እና የኮንስትራክሽን ሥራዎች የሚሠራ እንዲሁም ሰላሳ የወፍጮ ማሽን ሞልዶች ለወፍጮ ድንጋይ ማምረቻ እና በጣም ዘመናዊ የብረት ማቅለጫ ያለው ድርጅት ነው። 

ተጨማሪ

ለማ ጠቅላላ ባህላዊ ዕደ-ጥበብ

ድርጅቱ በጥቃቅን እና አነስተኛ ማኅበር በግለሰብ ደረጃ ተደራጅቶ ሥራ የጀመረው በ2009 ዓ.ም በአቶ ለማ መሥራችነት ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የባሕላዊ እቃዎችን በጥራት በማምረት ለገበያ ያቀርባል። ምርቱንም ሽሮሜዳ፣ ፖስታ ቤት እና መርካቶ አካባቢ በአዲስ አበባ እንዲሁም በክልል ከተሞች ደግሞ በባሕር ዳር፣ ሻሸመኔ እና ናዝሬት ለተረካቢዎች ያቀርባል። ድርጅቱ ከሌሎች የባህል ጌጣጌጥ አምራቾች የሚለየው …

ተጨማሪ

ሂሳሊስ ጋርመንት

Sewing Machine

ሂሳሊስ ጋርመንት የተመሠረተው በ 2010 ዓ.ም በወ/ሮ መሠረት ዳዱ ነው። ድርጅቱ የሚያመርታቸው የአልባሳት ምርቶች ከአንድ ዓመት እስከ አስራ ሦስት ዓመት ክልል ውስጥ ለሚገኙ ሕጻናት ነው። የአልባሳቶቹም ዋጋ የማኅበረሰቡን አቅም ያገናዘበ ነው። የአልባሳቶቹ ዋጋዎች ቢለያዩም ከዝቅተኛው ዋጋ መቶ ሰማንያ ብር (ብር 180) ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ዋጋ አራት መቶ ብር (ብር 400) …

ተጨማሪ

ቴዎድሮስ፣ ኤልያስ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት

ቴዎድሮስ፣ ኤልያስ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ የተመሠረተው በ2008 ዓ.ም መጨረሻ ሲሆን፤ በጥሩ ሁኔታ ምርት የማምረት ሂደት የጀመረው በ2009 ዓ.ም ነው። ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ቴዎድሮስ ይሉ እና በአራት መሥራች አባላት ነው። ድርጅቱ ሲመሰረት ጠንካራ እንዲሆን ያደረገው ሁሉም የድርጅቱ መሥራች አባላት በአንድ የእድሜ ክልል እና የኢንጂነሪንግ ትምህርት ምሩቅ መሆናቸው …

ተጨማሪ

የትጋት ውጤት – ኤርሚያስ ከበደ ጠቅላላ የእንጨት ሥራ ድርጅት

ኤርሚያስ ከበደ ጠቅላላ የእንጨት ሥራ ድርጅት የተመሠረተው በ2000 ዓ.ም በአቶ ኤርሚያስ ከበደ ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የቤት እና የቢሮ እቃዎችን በጥራት ያመርታል። ድርጅቱ  ከሶስት እስከ አምስት የሚደርሱ ፎቆችን (የወረዳ ህንጻ አይነቶችን) ሙሉ በሮች እና መስኮቶች ከዐሥራ አምስት እስከ ሀያ ቀን ድረስ የማምረት አቅም ያለው ሲሆን እንዲሁም የመኖሪያ ቤት ከአምስት እስከ ስምንት የሚደርሱ በሮች …

ተጨማሪ

አጸደ፣ ነሲባ እና ጓደኞቻቸው የእንጀራ መጋገር ሥራ

ይህ ኢንተርፕራይዝ የተመሠረተው በ 2001 ዓ.ም በ ወ/ሮ ነሲባ ራህመቶ እና በዐሥራ ዘጠኝ መሥራች አባላት ነው። ድርጅቱ በሀያ መሥራች አባላት ቢመሰረትም በነበረው አስቸጋሪ ሁኔታ ዘጠኝ አባላት የቀን ሥራ ብንሠራ ይሻለናል ብለው ሲያቋርጡ፣ አንድ አባል ደግሞ በሞት ስለተለየች በአሁን ጊዜ ዐሥር መስራች አባላት በድርጅቱ ውስጥ ይገኛሉ።

ተጨማሪ

በከፍታ የቴሌግራም ቻናል የሥራ ትስስር አግኝተናል – ጦቢያ ብረታ ብረት ማሽን ሥራ

ጦቢያ ብረታ ብረት ማሽን ሥራ የተመሠረተው በ2000 ዓ.ም ዐሥራ ሰባት ሺህ ብር ብድር በመበደር ነበር። ድርጅቱ የተመሠረተው በስድስት መሥራች አባላት ሲሆን፣ በነበረው የልምድ፣ የሙያ እና የፍላጎት መከፋፈል ምክንያት አምስት የድርጅቱ መሥራች አባላት የወጡ በመሆኑ በአሁን ወቅት አቶ ሚሊሻ ባህሩ ብቻ ድርጅቱን እያንቀሳቀሱ ይገኛሉ።

ተጨማሪ

ሥራን በኢንተርኔት ነው የምናገኘው – ሶኒያ ኬ ላንዠሪ (Lingerie)

sonia-k-logo

ሶኒያ ኬ ላንዠሪ (Lingerie) የሴቶች የውስጥ አልባሳት ልብስ ስፌት የተመሠረተው በ ወ/ሮ ሶኒያ አሕመድ 2005 ዓ.ም ሲሆን በአንድ መሥራች አባል እና በአንድ የልብስ ስፌት ማሽን  ነበር፡፡ወ/ሮ ሶኒያ የራሳቸውን ቢዝነስ የጀመሩት ራስን መቻል (self-sufficient መሆን) ስለሚፈልጉ ነው። ፈረንሳይ ሀገር በሊትሬቸር የተመረቁት ወ/ሮ ሶኒያ ቢዝነሱን ከመጀመራቸው በፊት በፈረንሳይ ቋንቋ ለሃያ ዓመታት በጅቡቲ …

ተጨማሪ

2merkato ሥራችንን ያለንበት ቦታ ድረስ ያመጣልናል – ቢዝነስ ሕትመት እና ማስታወቂያ

ቢዝነስ ማስታወቂያ የተመሠረተው በ2004 ዓ.ም ሲሆን፣ የተመሠረተውም የግል ኢንተርፕራይዝ ሆኖ በአቶ ቢሆነኝ ዘመነ ነበር። ድርጅቱ ሲመሠረት ሥራው ብዙም አስቸጋሪ አልነበረም። ቢዝነስ ማስታወቂያ የሰባት ዓመት ጊዜ ያስቆጠረ ቢሆንም በጥሩ ሁኔታ መንቀሳቀስ የጀመረው ግን በ2009 ዓ.ም ነው። ምሥረታና ዕድገት የድርጅቱ መሥራች የሆኑት አቶ ቢሆነኝ ወደ ሕትመት ሥራ ከመግባታቸው በፊት ኢንጂነር የመሆን ህልም ነበራቸው። …

ተጨማሪ