በህግ ማስከበር ዘመቻው ምክንያት ባለፉት አራት ወራት ሥራ አቁሞ የነበረው በትግራይ ክልል የሚገኘው መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ የማምረት ሥራውን በመጀመር ምርቱን ለገበያ እያቀረበ መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ገለጹ። ፋብሪካው ምርቱን ለገበያ ማቅረብ መጀመሩ ወደላይ ወጥቶ የነበረውን ዋጋ ለማሻሻል የራሱ የሆነ አዎንታዊ ሚና እንደሚኖረው ጨምረው ተናግረዋል።
ተጨማሪTewodros Mengistu
የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ 285 ብሔራዊ የጥራት ደረጃዎች መፅደቃቸውን አስታወቀ
የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ከብሔራዊ የደረጃ ዝግጅት ቴክኒክ ኮሚቴ ጋር በመሆን፣ የ285 ብሔራዊ የጥራት ደረጃዎችን በብሔራዊ ደረጃዎች ምክር ቤት ማፅደቁን አስታወቀ። ኤጀንሲው እንዳስታወቀው ለብሔራዊ የደረጃዎች ምክር ቤት ያቀረባቸው 285 የጥራት ደረጃዎች ፀድቀዋል። በስድስት ዘርፎች ተዘጋጅተው ከቀረቡት 285 ደረጃዎች 148 ያህሉ አዲስ ሲሆኑ፣ 44 የሚሆኑት የተከለሱና የተቀሩት 93 ደረጃዎች በፊት የነበሩና እንዲቀጥሉ …
ተጨማሪየሸገር ዳቦ ፋብሪካ ከዛሬ ጀምሮ በሙሉ አቅሙ ማምረት ጀመረ
የሸገር ዳቦ ፋብሪካ ከዛሬ መጋቢት 7፣ 2013 ዓ/ም ጀምሮ በሙሉ አቅሙ ማምረት ጀመረ። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የተመራ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ቡድን ፋብሪካው ያለበትን አጠቃላይ ሁኔታ ጎብኝቷል። በጉብኝቱ ላይ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዳቦ ፋብሪካው በዛሬ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ወደ ማምረት እንደሚገባ ከስምምነት ላይ መደረሡን …
ተጨማሪበጃንሜዳ የነበሩ ነጋዴዎች ዛሬ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ በሚገኘው የገበያ ማዕከል አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ
በጃንሜዳ የነበሩ ነጋዴዎች ከዛሬ ጀምሮ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ በሚገኘው በላፍቶ የአትክልትና ፍራፍሬ የገበያ ማዕከል አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ። ይህንንም የተናገረው የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ነው።
ተጨማሪበአዲስ አበባ ከተማ ከመሬትና መሬት ነክ ከሆኑ ጉዳዮች ጋር ተቋርጦ የነበረው የአገልግሎት እገዳ ተነሳ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከመሬትና መሬት ነክ ከሆኑ ጉዳዮች ጋር ተቋርጦ የነበረው የአገልግሎት እገዳ ከህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ተነስቷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከነሀሴ 20 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ መሬትና መሬት ነክ የሆኑ ጉዳዮች አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ ማገዱ ይታወሳል። የከተማ አስተዳደሩ በመሬትና መሬት ነክ ጉዳዮች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን …
ተጨማሪመግቢያ የተሰኘ የዴሊቨሪ እና የቢዝነስ ሊስቲንግ መተግበሪያ አገልግሎት ላይ ዋለ
ኢቢዝ ኦንላይን ሶሉሽንስ ኃ.የተ.የግል ማኅበር “መግቢያ” (megbia.com) የተሰኘ አዲስ የሞባይል መተግበሪያ መልቀቁን አስታውቋል። ይህ መተግበሪያ ተጠቃሚዎች በአቅራቢያቸው የሚገኙ ቢዝነሶችን በቀላሉ እንዲያገኙ ከመርዳቱም በላይ፣ አዲስ አበባ ውስጥ ከየተኛውም ቦታ ሆነው ምግብ አዘው እንዲደርሳቸው ያስችላል። መተግበሪያው ሙሉ በሙሉ የተሠራው የኢትዮጵያ ትልቁ የቢዝነስ ፖርታል የ 2merkato.com ባለቤት በሆነው ድርጅት ባለሙያዎች ነው። ኢቢዝ በመቶዎች …
ተጨማሪስለ ‘ከፍታ’ ፖርታል የሚያስገነዝብ ሥልጠና እየተካሄደ ነው
የተወዳጁ 2merkato.com ባለቤት የሆነው ኢቢዝ ኦንላይን ሶሉሽንስ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር በአዲስ አበባ ከተማ ባሉ 120 ወረዳዎች ለሚገኙ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች እና የቡድን መሪዎች ሥልጠና እያካሄደ ነው። ኢቢዝ ‘SNV’ ከተባለው የኔዘርላንድስ የልማት ድርጅት ጋር በመሆን እና በአዲስ አበባ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ትብብር ለጥቃቅን …
ተጨማሪባለፉት ሶስት ወራት ከማዕድን ዘርፍ ከ178 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ተገኘ
ባለፉት ሶስት ወራት ከማዕድን ዘርፍ ከ178 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ መገኘቱን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢ/ር ታከለ ኡማ ተናገሩ። ይህንንም ያሉት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የሶስት ወራት አፈፃፀም በተመለከተ ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው። ወደ ውጭ ተልከው የውጭ ምንዛሬ ካስገኙት ማዕድናት መካከል ወርቅ፣ ታንታለም፣ ኳርትዝ፣ ኢመራልድ፣ ሳፋየር እና እምነበረድ ተጠቃሾች …
ተጨማሪበአዲስ አበባ በ2013 በጀት አመት 525 ኪሎ ሜትር የጥገና ስራ ይከናወናል
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በ2013 በጀት አመት በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች 525 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የአስፋልት፣ የድልድይ፣ የድሬይኔጅ፣ የአክሰስ መንገድ እና ሌሎች በርካታ ልዩ ልዩ የጥገና ስራዎችን ለማከናወን አቀደ፡፡
ተጨማሪየገበያ ትስስር
እዚህ ላይ የተመዘገቡ ኢንተርፕራይዞችን ዝርዝር፣ ሥራቸውን፣ የድርጅታቸውን ፕሮፋይል እና አድራሻቸውን በመጠቀም አብሮ መሥራት ይቻላል።
ተጨማሪ