ጸጋ ዳቦ እና ኬክ መጋገሪያ በ2005 ዓ.ም በአቶ አሰፋ ወልዴ ተመሠረተ። ደርጅቱ ሲመሠረት ከነበረው የመነሻ አምስት መቶ ብር ካፒታል አሁን ወደአለው ሀምሳ ሺህ ብር ካፒታል ለመድረስ በዘርፉ ያካበቱት የሥራ ልምድ እና የወሰዷቸው ሥልጠናዎች ከፍተኛ አስተዋፅዖ እንዳደረጉላቸው የድርጅቱ መሥራች አቶ አሰፋ ይገልፃሉ። አቶ አሰፋ የዳቦ እና ኬክ መጋገሪያ ሥራ ከመጀመራቸው በፊት …
ተጨማሪልምድ እና ተሞክሮ
የምግብ ዝግጅት ሥራ – ቤተልሔም በለጠ ምግብ ዝግጅት
ቤተልሔም በለጠ ምግብ ዝግጅት የተመሠረተው በወ/ት ቤተልሔም በለጠ ነው። የመሥራቿ የምግብ ሥራ ፍላጎት እና የሥራ ልምድ እንዲሁም እውቀት ተድምሮ ድርጅቱን ስትመሠርት ከነበረው አንድ የሰው ሀይል አሁን ለደረሰበት ዐስራ አንድ ሠራተኞች ሊደርስ ችሏል። ወ/ት ቤተልሔም ድርጅቱን ስትመሠርት የነበራት ሀሳብ ጠንክሮ በመስራት ራስን መለወጥ ብሎም ለሌሎች ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ነው።
ተጨማሪዲኤምቲ (DMT) የቤት እና የቢሮ እቃዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር
ዲኤምቲ (DMT) የቤት እና የቢሮ እቃዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተመሠረተው በ1999 ዓ.ም በአቶ ደረጄ አበራ ሲሆን የተለያዩ የቤት እና የቢሮ አቃዎችን ያመርታል። ከሚያመርታቸው ምርቶች መካከል:- አልጋ ቁምሳጥን የምግብ ጠረጴዛ የቤት በር እና መስኮቶች ሶፋዎች የሶፋ ምርቶቹ ዓይነቶች በሦስት ይከፈላሉ፦ ዝቅተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ የዋጋ ተመን ያላቸው ዝቅተኛ ሶፋዎች ከአስራ …
ተጨማሪማቱት ብዙነሽ እና ጓደኞቻቸው የሕብረት ሥራ ሽርክና ማኅበር
ማቱት፣ ብዙነሽ እና ጓደኞቻቸው የሕብረት ሥራ ሽርክና ማኅበር በአቶ ማቱት ታይሉ እና በሁለት መስራች አባላት 2011 ዓ.ም ላይ ነው የተመሰረተው። የሚያምረተው ምርት የእንጀራ ምርት ነው። ማኅበሩ ሲመሰረት ከነበረው ሦስት አባላት ተነስቶ በአሁኑ ጊዜ ለስድስት ቋሚ እና ስድስት ጊዜያዊ ሠራተኞች የሥራ እድል በመፍጠር እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
ተጨማሪየእንጨት ሥራ – ታደለ ሱልጣን እና ጓደኞቻቸው የእንጨት ሥራ ህብረት ሽርክና ማህበር
ታደለ ሱልጣን እና ጓደኞቻቸው የእንጨት ሥራ ሽርክና ማኅበር የተመሠረተው በ2011 ዓ.ም ግንቦት ወር መጨረሻ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ሁለት ዓመት ሆኖታል። አላማው ሠርቶ ለመለወጥ እና የሥራ እድል በመፍጠር ለሌሎችም የሥራ እድል ማመቻቸት መሆኑን ከመስራች አባላት መካከል አንዱ የሆነው አቶ ታደለ የሺ በላይ ገልጸዋል። አቶ ታደለ ወደ ሥራ ከመግባታቸው በፊት ከቤተሰባቸው ጋር …
ተጨማሪየእንጨት ሥራ -ሶሊና ሶፋ የቤት እና የቢሮ እቃዎች አምራች
ሶሊና ሶፋ የቤት እና የቢሮ እቃዎች አምራች የተመሰረተው በ2001 ዓ.ም በአቶ አብይ ወልደሐና እና በአምስት መሥራች አባላት ነው። በ2001 ዓ.ም ቢመሰረትም ምርት በጥሩ ሁኔታ ማምረት የጀመረው ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ ነው። በአሁን ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ አሉ ከሚባሉ እና አንጋፋ ሶፋ አምራች ድርጅቶች ውስጥ አንዱ ነው። በአዲስ አበባ በሦስት ቅርንጫፎች በጎተራ፣ ጉርድ …
ተጨማሪየልብስ ስፌት ሥራ – ቅድስት ሰለሞን ልብስ ስፌት
ቅድስት ሰለሞን ልብስ ስፌት የተመሰረተው 2005 ዓ.ም በወ/ት ቅድስት ሰለሞን ነው። ድርጅቱ ካለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ በመልካም የእድገት ሁኔታ ምርት በማምረት ሂደት ላይ እንደሚገኝ የድርጅቱ መሥራች አባል ወ/ት ቅድስት ሰለሞን አስረድታለች። የመስራቿ የልብስ ስፌት እውቀት እንዲሁም የሥራ ልምድ ተደምሮ ድርጅቱ ሲመሰረት ከነበረው አንድ ማሽን አሁን ላለው አምስት ማሽን እና አራት …
ተጨማሪየድር እና ማግ ሥራ – ሪል ድር ማጠንጠኛ
ሪል ድር ማጠንጠኛ የተመሰረተው 2005 ዓ.ም ሲሆን መስራቾቹም ሦስት አባላት ናቸው። ድርጅቱ ሁለት ዓመታት ያህል በጥሩ ሁኔታ ሲያመርት መቆየቱን የድርጅቱ መስራች አባል የሆነው አቶ ሀብታሙ አስረድቷል። የአቶ ሀብታሙ በሙያው ተገቢ የሥራ ልምድ መኖር፣ እንዲሁም የእህቱ የቴክስታይል ተማሪ መሆን እና በኳሊቲ ኮንትሮል በፋብሪካ ውስጥ ለረጅም ግዜ መሥራት ከባለቤቱ የሒሳብ ሥራ ክህሎት …
ተጨማሪ“ደንበኞችን ማርካት ዋና የቢዝነስ የማእዘን ራስ ነው”
ሳሙኤል ደባልቄ የሌዘር ሥራ ሳሚ የሌዘር ሥራ የተመሰረተው በ 2007 ዓ.ም ሲሆን፣ ድርጅቱ የምርት ሥራ የጀመረው በ2008 ዓ.ም ነው። የድርጅቱ መስራች የሆነው አቶ ሳሙኤል ሲያስረዳ በሙያው የትምህርት እንዲሁም የሥራ ልምድ በመቅሰም ወደ ድርጅቱ ምስረታ እንደመጣ ሳሚ ይናገራል። ሳሚ ሌዘር ሲመሰረት በአንድ ማሽን በራሱ መኖሪያ ቤት ውስጥ ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት ሁለት …
ተጨማሪ“በደንብ የሚያውቁትን ስራ መሥራት ለውጤታማነት ቁልፍ ነው”
ሳሙዔል ሰማኸኝ (ሳሚ ማተሚያ ድርጅት) ሳሚ ሕትመት እና ተያያዥ ሥራዎች የተመሰረተው በ 2011 ዓ.ም ሲሆን፣ የተመሠረተውም የግል ኢንተርፕራይዝ ሆኖ በአቶ ሳሙኤል ሰማኸኝ ነበር። ድርጅቱ ሲመሰረት ሥራው ብዙም አስቸጋሪ እንዳልነበረ አቶ ሳሙዔል ይናገራል። የድርጅቱ መስራች የሆነው አቶ ሳሙዔል ወደ ሕትመት ሥራ ከመግባቱ በፊት በአይቲ (IT) ሥራ አራት ዓመት ሲሠራ እንደቆየ ያስረዳል። …
ተጨማሪ