መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ (page 7)

ልምድ እና ተሞክሮ

በዚህ ገጽ ሥር፣ በሥራቸው ውጤታማ የሆኑ ኢንተርፕራይዞች ተሞክሮ ይቀርባል። ታሪካቸው ከሚወሳው ኢንተርፕራይዞች ጉዞ፣ ለእርስዎ የሚጠቅሙ ተግባራዊ የሆኑ አስተውሎቶች፣ ምክሮች እና ጥቆማዎችን ያገኛሉ። በሥራችሁ ውጤታማ ከሆናችሁ፣ ንገሩንና እዚህ ገጽ ላይ እናወጣችኋለን። ታሪካችሁ ሌሎችን ያስተምራል፣ ቢዝነሳችሁንም ያስተዋውቃል። በ6131 ወይንም በ 0975616161 ደውሉልን።

አሰፋ የቆዳ ውጤቶች

assefa-leather

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ አሰፋ ሽምባጋ በ2009 ዓ.ም በግል ኢተርፕራይዝነት ነው። ይህ ድርጅት አጠቃላይ የቆዳ ውጤቶችን በጥራት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያመርት ድርጅት ነው።

ተጨማሪ

ቆንጆ ማስታወቂያ

konjo-advertising

ድርጅቱ የተመሠረተው በ2008 ዓ.ም በወይዘሮ ቆንጂት አይፎክሩም እና በአራት መሥራች አባላት ነው። ድርጅቱ የማስታወቂያ እና ጠቅላላ የሕትመት ሥራዎችን ይሠራል። ይህ ድርጅት በኅትመት ሥራ የስድስት ዓመት የሥራ ልምድ አለው።

ተጨማሪ

ኩል ዲዛይን

እሸቱ እና ሣምሪ ልብስ ስፌት አገልግሎት የተመሠረተው በአቶ እሸቱ ደጉ እና በባለቤታቸው በወ/ሮ ሣምራዊት መሥራች አባልነት በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የልብስ ስፌት ሥራዎችን ይሠራል። የዚህ ድርጅት መስራቾች በልብስ ስፌት እና በፋሽን ዲዛይን ሥራ የዐሥራ ሰባት ዓመት ድምር ልምድ አላቸው።

ተጨማሪ

ግሬስ ኢንጂነሪንግ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ተሾመ ደበሌ እና በአራት መሥራች አባላት በ2009 ዓ.ም ነው። ድርጅቱ የሚሠራቸው ሥራዎችን አጠቃላይ የማሽነሪ እና የብረታ ብረት ሥራዎች ናቸው።

ተጨማሪ

ያሬድ እና ጓደኞቹ ቡና እና ቁርስ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ያሬድ ጌታሁን እና በአራት መሥራች አባላት በ2012 ዓ.ም አጋማሽ ነው። ድርጅቱ የሻይ እና ቡና፣ የቁርስ እና ምሳ እንዲሁም እንዳንድ ቀለል ያሉ የሻይ ሰዓት አገልግሎቶችን በተለያዩ ስብሰባዎች ላይ በመገኘት አገልግሎት ይሰጣል።

ተጨማሪ

ዮብ ፈርኒቸር

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ዮናስ ቢያድግልኝ በ2005 ዓ.ም. ነው። ይህ ድርጅት አጠቃላይ የእንጨት ሥራዎችን በጥራት ያመርታል።

ተጨማሪ