መነሻ / ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት (page 3)

ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት

ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተፕራይዞች ምዝገባ ከፈፀሙ በኋላ የፋይናንስ ድጋፍ የሚያገኙባቸውን አማራጮች በዚህ ክፍል ሥር ያገኛሉ።

እንዲሁም ከተለያዩ ኢንተርፕራይዞች ጋር በሽርክና መሥራት የሚፈልጉ ኢንቨስትሮች እና ኢንቨስተር የሚፈልጉ ኢንተርፕራይዞች ዝርዝር እዚህ ይኖራል።

በጋራ እንችላለን – ሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር

sheger-logo

ሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር የቁጠባ ባሕልን ለማሳደግ፣ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ አሁን ከደረሰበት ደረጃ ጋር በተያያዘ በኢኮኖሚው ዘርፍ ጠንካራ ተዋናይ ሆኖ ለመገኘት የሚያስፈልገውን የፋይናንስ ፍላጎት በጋራ ሆኖ ለማሟላት፣ እንዲሁም የገንዘብ አጠቃቀምና አስተዳደር ችግሮችን በጋራ ለመፍታት ዓላማ ባደረጉ የኅብረተ ሰብ ክፍሎች የተቋቋመ የኅብረት ሥራ ማኅበር ነው። ማኅበሩ በ2009 …

ተጨማሪ

ብርሃን ለኢትዮጵያ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር

birhan-le-ethiopia-credi-saving-logo

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ብርሃን ለኢትዮጵያ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በአካል ሄዶ እና  በዌብሳይት በመመልከት በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ተጨማሪ

አዲስ ራፋይሰን የኅብረት ሥራ ሠራተኞች የገንዘብ ቁጠባና ብድር

addis-raiffeisen-logo

አዲስ ራፋይሰን የኅብረት ሥራ ሠራተኞች የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በ2003 ዓ.ም. በኅብረት ሥራ ሠራተኞችና ባለሙያዎች የተቋቋመ የኅብረት ሥራ የፋይናንስ ተቋም ነው። የኅብረት ሥራ ማኅበሩ የኅብረት ሥራ ባለሙያዎችና ሠራተኞችን በአባልነት በማቀፍ በዚህ ዘርፍ የተሻለ አስተዋፅኦ ለማበርከት የተቋቋመ ማኅበር ነው። ስሙን የወሰደው ከ Friedrich Wilhelm Raiffeisen ሲሆን፤ ራፋይሰን …

ተጨማሪ

ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት 5.5 ቢሊዮን ብር ከአዋሽ ባንክ በብድር ሊያገኙ ነው

አዋሽ ባንክ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ለተለያዩ የማክሮ ፋይናንስ ተቋማት 5.5 ቢሊዮን ብር ብድር ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ። ባንኩ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ለማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት (ለአነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋማት) ለማበደር ካቀደው በጀት ውስጥ 1.5 ቢሊዮን ብር የሚሆነውን ብድር ተጠቃሚ ከሚሆኑ ዘጠኝ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ጋር ባለፈው ሐሙስ ሐምሌ 21 ቀን …

ተጨማሪ

የኛ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር

“የኛ ሁሌም የኛ የሁላችንም ነው!!” በሚል መሪ ቃል የሚታወቀው የኛ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የሚገኙ እና በትምህርት ደረጃቸው ዝቅተኛ የሆኑትን፣ እንዲሁም መካከለኛውን የኅብረተ ሰብ ክፍሎች በገንዘብ አስተዳደር እና አጠቃቀም እና በተለያዩ ሥልጠናዎች በማገዝ የኑሮና አኗኗር ለውጥን ለማምጣት እና ለመሥራት የተቋቋመ የገንዘብ ቁጠባና …

ተጨማሪ

“ዛሬ በመቆጠብ ነገን በተሻለ ህይወት ይኑሩ” – አፍሪካ ቪሌጅ ፋይናንሽያል ሰርቪስስ አ.ማ.

africafssc-logo

አፍሪካ ቪሌጅ ፋይናንሽያል ሰርቪስስ አ.ማ. በአዋጅ ቁጥር 626/2009 መሠረት ተቋቁሞ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ በማግኝት እ.ኤ.አ. ከ1999 ጀምሮ በኦሮሚያና በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ውስጥ ፋይናንስ ነክ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ የሚገኝ የፋይናንስ ተቋም ነው።

ተጨማሪ

ሃበሻ ኢንተርፕረነርስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ ኅብረት ሥራ ማኅበር

ሃበሻ ኢንተርፕረነርስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ ኅብረት ሥራ ማኅበር የኅብረት ሥራ ማኅበራትን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 985/09 መሠረት የተቋቋመ ሕጋዊ ድርጅት ነው።  የሥራ ፈጣሪዎች በአንድነት የጋራ የሆኑ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ችግሮቻቸውን ለመፍታት እንዲችሉም የተቋቋመ ማሕበር ነው፡፡

ተጨማሪ