መነሻ / ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት (page 5)

ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት

ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተፕራይዞች ምዝገባ ከፈፀሙ በኋላ የፋይናንስ ድጋፍ የሚያገኙባቸውን አማራጮች በዚህ ክፍል ሥር ያገኛሉ።

እንዲሁም ከተለያዩ ኢንተርፕራይዞች ጋር በሽርክና መሥራት የሚፈልጉ ኢንቨስትሮች እና ኢንቨስተር የሚፈልጉ ኢንተርፕራይዞች ዝርዝር እዚህ ይኖራል።

“ዛሬ የቆጠቡት አነስተኛ ገንዘብ ለነገው ሀብት የመሠረት ድንጋይ ነው።” የምሥራች ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ.

yemisrach-microfinance

የምሥራች ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ. ለማኅበረሰቡ በዋናነት የአክሲዮን ሽያጭ፣  የቁጠባ አገልግሎት እና የብድር አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ለጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ የሚሆኑ ብድሮችንም አዘጋጅቷል። አግልግሎቱንም አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ ስድስት ቅርንጫፎች ይሰጣል። ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው የምሥራች ማይክሮ ፋይናንስ በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም …

ተጨማሪ

ጋሻ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አክስዮን ማኅበር

ጋሻ አነስተኛ የፋይናንስ (ማይክሮፋይናንስ) ተቋም አክስዮን ማኅበር በአነስተኛ ንግድ ላይ ለተሰማሩ እንዲሁም ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የኅብረተ ሰብ ክፍሎች የብድር፣ የቁጠባ እና የአረቦን አገልግሎት ለመስጠት በ1990 ዓ.ም. ተቋቋመ። ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ለጋሻ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አክስዮን ማኅበር በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ …

ተጨማሪ

ለፋይዳ ብድር እና ቁጠባ ተቋም

lefayda-mfi-logo

ለፋይዳ ብድርና ቁጠባ አ.ማ. እ.ኤ.አ ሰኔ 2007 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዕውቅና በሥራ ፈቃድ ቁጥር MF7/029/2007 እና በንግድ ምዝገባ ቁጥር 062/7915/99 የተቋቋመ የብድር ቁጠባና ተጓዳኝ ገንዘብ ነክ ግልጋሎቶችን የሚሰጥ የፋይናንስ ተቋም ነው።

ተጨማሪ

ዳይናሚክ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አክስዮን ማኅበር

ዳይናሚክ በአነስተኛና መካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ገበሬዎች፣ በጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ተቋማትና ግለሰቦች ያለባቸውን የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽ አለመሆን ችግር ለመቅረፍ ግልፅ እና ስትራተጂካዊ ራዕይ፣ ተልእኮና ዓላማ ቀርፆ ከግቡ የሚያደርሱትን የገንዘብ ቁጠባና ብድር አገልግሎቶች በመስጠት ላይ ይገኛል። የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽ መሆን የተገለሉ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ለማብቃት፣ የመበልፀግ እድላቸውን ለማስፋትና …

ተጨማሪ

ምሳሌ የብድር አገልግሎት – ከዳይናሚክ ማይክሮ ፋይናስ ተቋም አ.ማ.

ዳይናሚክ ማይክሮ ፋይናስ ተቋም አ.ማ. የኅብረተ ሰቡን ፍላጎት ያማከለ የፋይናንስ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። ተቋሙ የደንበኞቹን ፍላጎት መነሻ በማድረግ በየጊዜው አሠራሩን በቴክኖሎጂ እያዘመነ የሚገኝ ሲሆን አገልግሎቱን ለበርካታ የኅብረተ ሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ ቅርንጫፎችን እና የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት ላይ ይገኛል። ተቋሙ ወጣቱን የኅብረተ ሰብ ክፍል ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ በአሁኑ ሰዓት ምሳሌ …

ተጨማሪ

ቪዥን ፈንድ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አክሲዮን ማኅበር

vision-fund-logo

ቪዥን ፈንድ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአነስተኛ ገንዘብ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ 40/1988 የተቋቋመ አንጋፋ እና አስተማማኝ የገንዘብ ተቋም ነው። ተቋሙ በ91 አገልግሎት መስጫ የቅርንጫፍ ቢሮዎቹ አማካኝነት ተደራሽ እና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። ተቋሙ በአሁኑ ሰዓት በጥቅሉ 734,226 በላይ የብድር እና የቁጠባ ደንበኞችን ለማፍራት የቻለ ሲሆን የሰጠው ብድር …

ተጨማሪ

መተማመን ብድርና ቁጠባ ተቋም አክሲዮን ማኅበር

metemamen-logo

መተማመን ብድርና ቁጠባ ተቋም ከብሔራዊ ባንክ ባገኘው ፈቃድ መሠረት ሁሉንም የኅብረተ ሰብ ክፍሎች በተለይም ሴቶችና ወጣቶች ለማገልገል የተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ባሁኑ ወቅት በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በሲዳማ፣ በደቡብ ሕዝቦች እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጠቅላላው 29 ቅርንጫፎችና 4 ንዑስ ቅርንጫፎች ያሉት ተቋም ነው። ተቋሙ የኅብረተ ሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ህይወት ለመለወጥ አገልግሎት በመስጠት …

ተጨማሪ

አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አ.ማ.

gears

አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አክሲዮን ማኅበር ዓላማ አድርጎ የተነሳው በልዩ ልዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ለመሳተፍ ፍላጎት፣ ዕውቀት እና ሙያ ኖሯቸው በካፒታል እጥረት ምክንያት መሥራት ላልቻሉ ኢንተርፕራይዞች የተወሰነ የጊዜ ገደብና ቅድመ ሁኔታዎች አስቀምጦ የካፒታል ዕቃን በማቅረብ (በሟሟላት) የፋይናንስ እጥረታቸውን መቅረፍ ነው።  በሃገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀው የሊዝ የፋይናንስ ስርዓት የካፒታል ዕቃዎች …

ተጨማሪ

ንሥር ማይክሮፋይናንስ

ንሥር ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አማ በኢትዮጵያ ንግድ ሕግና በብሔራዊ ባንክ የአነስተኛ ገንዘብ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ 626/2001 መሠረት ከ 2006 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ የሚገኝ አስተማማኝ የፋይናንስ ተቋም ነው። ንሥር ለንግድ ሥራ፣ ለመኪና መግዣ፣ ለትምህርት ክፍያ፣ ለቤት መሥሪያ፣ ለግል ጉዳይ ማስፈጸሚያ እና ለሌሎች ፍላጎትዎ ያበድራል። ንሥር ለንግድ ሥራ እና ለመኪና መግዣ እስከ …

ተጨማሪ

ለኢንተርፕይዞች ማገገሚያና መቋቋሚያ ብድር

ማስተርካርድ ፋውንዴሽን የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕይዞችን ማገገሚያና መቋቋሚያ ፕሮጀክት ይህ ፕሮጀክት የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ከማስተርካርድ ፋውንዴሽንና ከፈርስት ኮንሰልት ጋር በመተባበር የሚተገበር ነው። የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ በኮሮና ወረርሽኝ የተነሳ የደረሰውን የንግድ መቀዛቀዝ ለመገዳደር ጥረት እያደረጉ ያሉ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ማገዝ ነው። ፕሮጀክቱ ዝቅተኛ ወለድ እና የእፎይታ ጊዜ ያለው ብድር በተመረጡ የፋይናንስ …

ተጨማሪ