መነሻ / Tag Archives: ኢትዮጵያ (page 5)

Tag Archives: ኢትዮጵያ

ሮቢ ጋርመንት

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ሮቤል ነጋሽ በ2008 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ በዋናነት የሚሠራው የወንዶች ሙሉ ልብስ ሲሆን በዚህም ሥራ በጣም የዳበረ እና የረዥም ጊዜ ልምድ አለው። ከዚህ በተጨማሪ አጠቃላይ አልባሳትን ያመርታል።

ተጨማሪ

አጋፔ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሰረታዊ ህብረት ሥራ ማህበር

ኅብረት ሥራ ማህበር ማለት ሰዎች የጋራ ፍላጎታቸውን ለማሳካት ያላቸውን እውቀት፣ ጉልበት፣ ጊዜ እና ሀብት በማሰባሰብ ችግሮቻቸውን መፍታት የሚያስችል ቁልፍ መሣሪያ ነው። በዚህ መሠረት አጋፔ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ መሥራች አባላት በሕጋዊ መንገድ የተመሠረተ ኅብረት ሥራ ማኅበር ነው።

ተጨማሪ

ቤተሰብ የገንዘብ ብድርና ቁጠባ ተቋም

ቤተሰብ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር የኅብረት ሥራ ማኅበራትን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 985/2009 መሠረት የተቋቋመ ሕጋዊ ድርጅት ነው። ማኅበሩ ዝቅተኛውን የማኅበረሰብ ክፍልን እና የሥራ ፈጣሪዎችን በተለይ ሴቶችን ማዕከል በማድረግ የጋራ በሆኑት ዕሴቶች ላይ ማለትም ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ችግሮቻቸውን ለመፍታት እንዲችሉ የተቋቋመ የኅብረት ሥራ ማኅበር ነው።

ተጨማሪ

መንሽ የግብርና ማሺነሪ፣ መሣርያዎች ሌሎች የብረት ሥራዎች

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ውብሸት ደለለኝ እና በጓደኞቻቸው በ2002 ዓ.ም. ነው። የጤፍ መውቂያ ማሽን በዋናነት የሚያመርተው ምርት ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ የተለያዩ የእርሻ መሣሪያዎ ች(የግብርና መሣርያዎች)፣ የውሃ መሳቢያ እና መቆፈሪያዎች፣ የባዮ ጋዝ ምድጃዎች እና ማብላያዎች፣ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች እና ለትምህርት ቤት እና ለቢሮ የሚሆኑ የፈርኒቸር ምርቶችንም ያመርታል።

ተጨማሪ

ኤልሳቢ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ.

ኤልሳቢ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአነስተኛ ገንዘብ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 626/2001 መሠረት በአንድ መቶ ሚሊዮን ብር (ብር 100,000,000) ካፒታል የተቋቋመ የፋይናንስ ተቋም ነው። ተቋሙ በቅርንጫፍ ቢሮዎቹ አማካኝነት ተደራሽ እና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። ኤልሳቢ በዋናነት የባንክ አገልግሎት ማግኘት ላልቻሉ ማኅበረ ሰቦች (ጥቃቅን ሥራ ፈጣሪ እና አነስተኛ …

ተጨማሪ

ዮሴፍ እና መስፍን የአልሙኒየም ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ዮሴፍ ንጉሤ እና በጓደኛቸው 2011 ዓ.ም. የኅብረት ሽርክና ማኅበር ሆኖ ነው። ማኅበሩ አጠቃላይ የአልሙኒየም ሥራዎችን በጥራት እና በተጠጣጣኝ ዋጋ የማምረት እና የመገጣጠም ሥራ ይሠራል።

ተጨማሪ

ሰንፔር ኮምፒዩተር ሶሉሽንስ ኃ.የተ.የግ.ማ.

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ዋሲሁን ድጋፉ እና በጓደኛቸው በ2005 ዓ.ም. ነው። ሰንፔር ኮምፒዩተር ሶሉሽንስ የሚሠራው በቴክኖሎጂ ላይ ሲሆን ይህም ኮምፒዩተር ጥገና፣ ኔትወርኪንግ፣ እና የተለያዩ ሶፍትዌሮች እና ዌብሳይቶችን በማልማት (develop በማድረግ) ለሚፈልገው ተጠቃሚ ያቀርባል።

ተጨማሪ

ሳር ቤት የገንዘብ ቁጠባና ብድር

sar-bet-credit-and-saving

ሳር ቤት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በሳር ቤት አካባቢ ተወልደው ባደጉ አብሮ አደጎች መነሻ ሃሳብ አመንጪነት የመኖሪያ አካባቢን መሠረት አድርጎ የተቋቋመ የኅብረት ሥራ ማኅበር ነው። ዋነኛ ዓላማው አድርጎ የተነሳው የአባላቱን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ችግሮች የቁጠባን ባህል በማስረፅ እና በእቅድ በመበደር የሚፈቱበትን መንገድ ማበጀት ነው። ከዚህ በተጨማሪ የአባላቱን …

ተጨማሪ

ሰኢድ ሃሰን ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ሰኢድ ሃሰን በ2012 ዓ.ም. የግል ኢንተርፕራይዝ ሆኖ ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የኮንስትራክሽን ሥራዎችን የሚሠራ ድርጅት ሲሆን በይበልጥ ደግሞ በፊኒሺንግ ሥራዎችን ላይ በሰፊው ይሳተፋል።

ተጨማሪ

ዐይናለም የዕደ ጥበብ ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በወ/ሮ አይናለም ሀብትህ ይመር እና ሦስት ጓደኞቻቸው በ2007 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ የሚያመርታቸው ምርቶች በሦስት ዘርፎች ሲሆኑ እነሱም ዕደ ጥበብ፣ የፈርኒቸር ሥራ እና የብረት ሥራዎች ናቸው።

ተጨማሪ