የተመሠረተው በወ/ሮ ኤልሻዳይ ተካልኝ በግል ኢንተርፕራይዝነት በ2012 ዓ.ም ነው። ድርጅቱ የሚያቀርበው አገልግሎት የእንጀራ ምርት አገልግሎት ነው።
ተጨማሪTag Archives: ከፍታ 2merkato
ሬድዋን ተማም የቤት እና የቢሮ እቃዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት
ድርጅቱ የተመሠረተው በ 2005 ዓ.ም. በዐሥር መሥራች አባላት ሲሆን አሁን ላይ ግን ሦስት አባላት ብቻ በድርጅቱ ውስጥ ይገኛሉ። ድርጅቱ በአሁን ጊዜ የኪችን ካቢኔቶችን በዋናነት በማምረት ላይ ይገኛል።
ተጨማሪአማርድ ቡና
አማርድ ቡና ድርጅት የተመሠረተው በ2007 ዓ.ም በአቶ አብዱ ሲራጅ እና ዘጠኝ መሥራች አባላት ነው። ድርጅቱ የሚሰጠው አገልግሎት በዋናነት የቡና ምርቶች ሲሆን በተጨማሪ የባልትና ውጤቶችንም አብሮ ይሠራል።
ተጨማሪኢኤምቲጂኤም (EMTGM) ጄነራል ትሬዲንግ
ኢኤምቲጂኤም (EMTGM) ጄነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ ማኅበር ከመመሥረቱ ሃያ አመት በፊት ማህደር ተሰማ ብረታ ብረት በሚል ስያሜ ነበር በአቶ ማህደር ተሰማ የተቋቋመው። አቶ ማህደር በድርጅቱ እየሠሩ በነበረበት ወቅት አቶ ኢዩኤል ግርማቸው (አሁን በድርጅቱ ውስጥ በማናጀርነት እያገለገሉ የሚገኙ አባል) ትምህርታቸውን ጨርሰው በ1997 ዓ.ም ወደ ድርጅቱ ተቀላቀሉ። በ2000 ዓ.ም ድርጅቱ ወደ ኃላፊነቱ የተወሰነ …
ተጨማሪሞዛይክ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር
ሞዛይክ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተመሠረተው በአቶ ሳሙኤል ገዛህኝ እና በአቶ ጌትነት ካሳ መስከረም 2009 ዓ.ም ነው። ድርጅቱ ደረጃ ስምንት ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ሲሆን የሚቀበላቸውን ሥራዎችን በጊዜ ገደባቸው እና በጥራት ሠርቶ ያስረክባል።
ተጨማሪይትባረክ ላቀው ልብስ ስፌት
ይትባረክ ላቀው ልብስ ስፌት የተመሠረተው የግል ኢንተርፕራይዝ ሆኖ በአቶ ይትባረክ ላቀው በ2009 ዓ.ም ነው። ድርጅቱ በዋናነት የሚያመርታቸው ምርቶች የሴቶች እና የህጻናት አልባሳት ሲሆኑ ለህጻናት ከአንድ ዓመት አስከ ስምንት ዓመት ለሚደርሱ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ምርቱን በብዛት ያመርታል። ከዚህ በተጨማሪ አጠቃላይ የአልባሳት ሥራዎችን ይሠራል።
ተጨማሪቢ ኤም ደብሊው (B.M.W) ሜታል ኢንጂነሪንግ
ቢ ኤም ደብሊው ድርጅት የተመሠረተው ጥር 2009 ዓ.ም. በአቶ አምሃ ወንድሙ እና በሁለት መሥራች አባላት ነው። ድርጅቱ የተለያዩ ማሽኖችን የማምረት እና የመጠገን እንዲሁም ለማሽኖች የመለዋወጫ እቃዎችን በራሱ ፈጠራ ይሠራል። እኒዚህም እቃዎች በአገር ውስጥ የማይገኙ እቃዎች ሲሆኑ ለእነዚህ እቃዎች የመለዋወጫ እቃ እና የተለያዩ ሞልዶች ያመርታል።
ተጨማሪ“በከፍታ ፓኬጅ ተጠቅመናል”- መንግሥቱ እና ዳዊት ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ
መንግሥቱ እና ዳዊት ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ የተመሠረተው በአቶ መንግሥቱ አባተ በ2009 ዓ.ም ነው። ድርጅቱ የሚሠራቸው ሥራዎች ጠቅላላ የኮንስትራክሽን ሥራዎች በዋናነት እንዲሁም የተለያዩ የአበባ ማስቀመጫ እቃዎችን በተለያየ መጠን እና ዲዛይን በተጨማሪም የህጻናት መጫወቻዎችን በጥራት ያመርታል።
ተጨማሪ“የእኛን ሥራ ብዙ ሰው ይሠራዋል የእኛን ሀሳብ ግን ማንም ሊሠራው አይችልም” ቲኬ ማሽን የመገጣጠም ሥራ
ቲኬ ማሽን የመገጣጠም ሥራ የተመሠረተው በ 2007 ዓ.ም በአቶ ሲሳይ ደጉ እና በጓደኛቸው መሥራች አባልነት ነው። ድርጅቱ የሚሠራው ሥራ ማሽን የመገጣጠም ሥራ (Assembling) ነው። በአጭር ጊዜ ብዙ ማሽኖችን የመገጣጠም እና የማምረት አቅም አለው። ከዚህ በተጨማሪ የአሉሚኒየም ምርቶችን ያመርታል።
ተጨማሪግሪን ሆፕ ሪኒወብል ኢነርጂ
ግሪን ሆፕ ሪኒወብል ኢነርጂ የተመሠረተው በ 2011 ዓ.ም በአቶ አቤል ዘርፉ እና በጓደኛቸው ነው። አረንጓዴ የታዳሽ ኃይል (Green hope Renewable Energy) የሚሠራቸው ሥራዎች በዋናነት የታዳሽ ኃይል ኤሌክትሪክ አቅርቦት (Renewable Energy) የሕንፃ ኤሌክትሪክ መሥመር ዝርጋታ (Building installation) የተለያዩ የኤሌክትሪክ ገመዶች አቅርቦት እንዲሁም ተያያዥ ሥራዎች የጥገና እና የጥሬ እቃ አቅርቦት አገልግሎት ናችወ።
ተጨማሪ