ድርጅቱ የተመሠረተው በ2011 ዓ.ም. በወ/ሮ ገነት የግል ኢንተርፕራይዝ ሆኖ ነው። ይህ ድርጅት የሚያመርታቸው ምርቶች ባህላዊ እና ዘመናዊ ልብሶችን ሲሆን በይበልጥ ደግሞ የሴቶች እና የህጻናት ባህላዊ ልብሶችን ከዘመናዊ ልብሶች ጋር በማጣመር ያመርታል።
ተጨማሪTag Archives: ከፍታ
ጽጌረዳ ካሳሁን ልብስ ስፌት (ኪያ ዲዛይን)
ድርጅቱ የተመሠረተው በወ/ት ጽጌረዳ ካሳሁን 2012 ዓ.ም የግል ኢንተርፕራይዝ ሆኖ ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የልብስ ስፌት ሥራዎችን የሚሠራ ሲሆን በዋናነት ግን የአፍሪካ የባህል ልብሶችን ያመርታል።
ተጨማሪዘኪ ባግስ
ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ዘካርያስ እስጢፋኖስ በ2011 ዓ.ም. የግል ኢንተርፕራይዝ በመሆን ነው። ይህ ድርጅት የሚያመርታቸው ምርቶች አጠቃላይ የቆዳ ቦርሳዎችን ሲሆን ምርቶቹን በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚ እና ነጋዴ ያከፋፍላል።
ተጨማሪግሬስ ኢንጂነሪንግ
ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ተሾመ ደበሌ እና በአራት መሥራች አባላት በ2009 ዓ.ም ነው። ድርጅቱ የሚሠራቸው ሥራዎችን አጠቃላይ የማሽነሪ እና የብረታ ብረት ሥራዎች ናቸው።
ተጨማሪአማርድ ቡና
አማርድ ቡና ድርጅት የተመሠረተው በ2007 ዓ.ም በአቶ አብዱ ሲራጅ እና ዘጠኝ መሥራች አባላት ነው። ድርጅቱ የሚሰጠው አገልግሎት በዋናነት የቡና ምርቶች ሲሆን በተጨማሪ የባልትና ውጤቶችንም አብሮ ይሠራል።
ተጨማሪይትባረክ ላቀው ልብስ ስፌት
ይትባረክ ላቀው ልብስ ስፌት የተመሠረተው የግል ኢንተርፕራይዝ ሆኖ በአቶ ይትባረክ ላቀው በ2009 ዓ.ም ነው። ድርጅቱ በዋናነት የሚያመርታቸው ምርቶች የሴቶች እና የህጻናት አልባሳት ሲሆኑ ለህጻናት ከአንድ ዓመት አስከ ስምንት ዓመት ለሚደርሱ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ምርቱን በብዛት ያመርታል። ከዚህ በተጨማሪ አጠቃላይ የአልባሳት ሥራዎችን ይሠራል።
ተጨማሪ“በጠባብ ማምረቻ በሰፊ ጭንቅላት ነው እየሠራን የምንገኝው” አሹ ኢንተርናሽናል የፈርኒቸር ዓለም
አሹ ኢንተርናሽናል የፈርኒቸር ዓለም ድርጅት የተመሠረተው በአቶ አሸናፊ ንጉሴ በግል ኢንተርፕራይዝነት ነው። አቶ አሸናፊ ድርጅቱን በ2002 ዓ.ም ከመመሥረታቸው በፊት በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ በብዙ የሥራ መስኮች ተሠማርተው ሲሠሩ ቆይተዋል። ይሁን እንጂ ብዙ ሥራዎችን ቢሠሩም በሀገር ውስጥ ሠርቶ መለወጥን የመሠለ ነገር አንደሌለ በመገንዘብ ወደ ሀገራቸው በመመለስ በማኑፋክቸሪንግ ሥራ ላይ ሊሠማሩ …
ተጨማሪደሳለኝ እሸቱ ግንባታ ማጠናቀቅና ሕንጻ ተቋራጭ
ደሳለኝ እሸቱ ግንባታ ማጠናቀቅ ሕንጻ ተቋራጭ ድርጅት የተመሠረተው በ2007 ዓ.ም በግል ኢንተርፕራይዝነት በአቶ ደሳለኝ እሸቱ ነው። ድርጅቱ የሚሠራቸው ሥራዎች አጠቃላይ የፊኒሺንግ ሥራዎች ናቸው።
ተጨማሪግሪን ሆፕ ሪኒወብል ኢነርጂ
ግሪን ሆፕ ሪኒወብል ኢነርጂ የተመሠረተው በ 2011 ዓ.ም በአቶ አቤል ዘርፉ እና በጓደኛቸው ነው። አረንጓዴ የታዳሽ ኃይል (Green hope Renewable Energy) የሚሠራቸው ሥራዎች በዋናነት የታዳሽ ኃይል ኤሌክትሪክ አቅርቦት (Renewable Energy) የሕንፃ ኤሌክትሪክ መሥመር ዝርጋታ (Building installation) የተለያዩ የኤሌክትሪክ ገመዶች አቅርቦት እንዲሁም ተያያዥ ሥራዎች የጥገና እና የጥሬ እቃ አቅርቦት አገልግሎት ናችወ።
ተጨማሪዘ ኬክ ኮርነር
የተመሠረተው በ 2012 ዓ.ም በሼፍ ብርሐኑ ረጋሳ ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የዳቦ እና የኬክ ምርቶችን የሚያመርት ድርጅት ሲሆን፤ የድርጅቱ መሥራች ከድርጅቱ ምሥረታ በፊት ለሃያ ሦስት ዓመታት በሙያቸው ከትልቅ ድርጅቶች ጋር ተቀጥረው ሲሠሩ ቆይተዋል። ድርጅቱ አጠቃላይ የቤከሪ (ዳቦ፣ ኩኪስ፣ ኬኮች፣ ወዘተ መጋገር) ሥራዎችን የሚሠራ ድርጅት ሲሆን በአሁን ጊዜ ግን የኬክ ሥራዎች ላይ …
ተጨማሪ