መነሻ / Tag Archives: 2merkato

Tag Archives: 2merkato

አዲስ ራፋይሰን የኅብረት ሥራ ሠራተኞች የገንዘብ ቁጠባና ብድር

addis-raiffeisen-logo

አዲስ ራፋይሰን የኅብረት ሥራ ሠራተኞች የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በ2003 ዓ.ም. በኅብረት ሥራ ሠራተኞችና ባለሙያዎች የተቋቋመ የኅብረት ሥራ የፋይናንስ ተቋም ነው። የኅብረት ሥራ ማኅበሩ የኅብረት ሥራ ባለሙያዎችና ሠራተኞችን በአባልነት በማቀፍ በዚህ ዘርፍ የተሻለ አስተዋፅኦ ለማበርከት የተቋቋመ ማኅበር ነው። ስሙን የወሰደው ከ Friedrich Wilhelm Raiffeisen ሲሆን፤ ራፋይሰን …

ተጨማሪ

ተዋበ እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ተዋበ ምኔነህ በ2004 ዓ.ም. የግል ኢንተርፕራይዝ ሆኖ ነው። ይህ ድርጅት አጠቃላይ የእንጨት እና የብረታ ብረት ሥራዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ይሠራል።

ተጨማሪ

ጎዳዳ፣ መርጊያ እና ጓደኞቻቸው የሻማ ውጤቶች ማምረቻ

ድርጅቱ የተመሠረተው በ 2006 ዓ.ም በዐሥራ ዘጠኝ መሥራች አባላት ሲሆን አሁን ላይ ግን በዘጠኝ መሥራች አባላት እየሠራ ይገኛል። ከአባላቱም መካከል ሴቶችና አካል ጉዳተኞች ይገኙበታል፡፡ ድርጅቱ የተለያዩ ሻማዎች በተለያየ ዲዛይን ያመርታል እንዲሁም የጧፍ ምርቶችን ያመርታል።

ተጨማሪ

“በጠባብ ማምረቻ በሰፊ ጭንቅላት ነው እየሠራን የምንገኝው” አሹ ኢንተርናሽናል የፈርኒቸር ዓለም

ashu-international-furniture

አሹ ኢንተርናሽናል የፈርኒቸር ዓለም ድርጅት የተመሠረተው በአቶ አሸናፊ ንጉሴ በግል ኢንተርፕራይዝነት ነው። አቶ አሸናፊ ድርጅቱን በ2002 ዓ.ም ከመመሥረታቸው በፊት በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ በብዙ የሥራ መስኮች ተሠማርተው ሲሠሩ ቆይተዋል። ይሁን እንጂ ብዙ ሥራዎችን ቢሠሩም በሀገር ውስጥ ሠርቶ መለወጥን የመሠለ ነገር አንደሌለ በመገንዘብ ወደ ሀገራቸው በመመለስ በማኑፋክቸሪንግ ሥራ ላይ ሊሠማሩ …

ተጨማሪ

“በከፍታ ፓኬጅ ተጠቅመናል”- መንግሥቱ እና ዳዊት ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ

መንግሥቱ እና ዳዊት ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ የተመሠረተው በአቶ መንግሥቱ አባተ በ2009 ዓ.ም ነው። ድርጅቱ የሚሠራቸው ሥራዎች ጠቅላላ የኮንስትራክሽን ሥራዎች በዋናነት እንዲሁም የተለያዩ የአበባ ማስቀመጫ እቃዎችን በተለያየ መጠን እና ዲዛይን በተጨማሪም የህጻናት መጫወቻዎችን በጥራት ያመርታል።

ተጨማሪ

ዘ ኬክ ኮርነር

the-cake-corner

የተመሠረተው በ 2012 ዓ.ም በሼፍ ብርሐኑ ረጋሳ ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የዳቦ እና የኬክ ምርቶችን የሚያመርት ድርጅት ሲሆን፤ የድርጅቱ መሥራች ከድርጅቱ ምሥረታ በፊት ለሃያ ሦስት ዓመታት በሙያቸው ከትልቅ ድርጅቶች ጋር ተቀጥረው ሲሠሩ ቆይተዋል። ድርጅቱ አጠቃላይ የቤከሪ (ዳቦ፣ ኩኪስ፣ ኬኮች፣ ወዘተ መጋገር) ሥራዎችን የሚሠራ ድርጅት ሲሆን በአሁን ጊዜ ግን የኬክ ሥራዎች ላይ …

ተጨማሪ

መስከረም ክበበው የቤት እና የቢሮ እቃዎች

meslerem-furniture

የተመሠረተው በ 2006 ዓ.ም በወ/ሮ መስከረም ክበበው ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የቤት እና የቢሮ እቃዎች የሚያመርት ድርጅት ሲሆን ይህ ድርጅት በአስራ አምስት ቀን ሶስት መቶ ወንበሮችን በጥራት የማምረት አቅም አለው። እንደ ወንበሮቹ ዲዛይን ቀኑ ሊለያይ ይችላል። ድርጅቱ በአሁን ጊዜ ለዐሥራ አራት ቋሚ እና ሁለት ጊዜያዊ ሠራተኞች የሥራ እድል መፍጠር ችሏል።

ተጨማሪ

ኤርታሌ ማኑፋክቸሪንግ ማሽነሪ እና ግንባታ ግብዓት አምራች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር

ኤርታሌ ማኑፋክቸሪንግ ማሽነሪ እና ግንባታ ግብዓት አምራች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተመሠረተው በአቶ በፍርዱ ሠይፉ እና በዐሥራ አራት አባላት 1996 ዓ.ም መጨረሻ ነበር። ይህ ማኅበር የማኑፋክቸሪንግ እና የኮንስትራክሽን ሥራዎች የሚሠራ እንዲሁም ሰላሳ የወፍጮ ማሽን ሞልዶች ለወፍጮ ድንጋይ ማምረቻ እና በጣም ዘመናዊ የብረት ማቅለጫ ያለው ድርጅት ነው። 

ተጨማሪ

ታደለ ፋስት ፉድስ

ታደለ ፋስት ፉድስ በ 2010 ዓ.ም መጨረሻ ላይ ነው የተመሠረተው። ድርጅቱ ፈጣን (ቶሎ የሚደርሱ) ምግቦችን በሁለት ደቂቃ ውስጥ የሚያደርስ ድርጅት ነው። ይህ ድርጅት የተለያዩ ሳንድዊቾችን ለተገልጋይ በሁለት የተለያየ መንገድ ያቀርባል፦  ምግቡን ይዞ መሄድ የሚፈልግ ይዞ ይሄዳል፤ እዛው አረፍ ብሎ መመገብ የሚፈልግ ደግሞ ይመገባል።  ታደለ ፋስት ፉድስ ፈላፈል ሳንድዊችን በአዲስ አበባ …

ተጨማሪ