ተጨማሪ
Tag Archives: ethiopia
የኮንስትራክሽን ጨረታዎችን እንዴት በደረጃ (BC/GC) መፈለግ እንችላለን?
ኢትዮጵያ ላይ የሚወጡ ጨረታዎችን በስልኮቻችን እንዴት መፈለግ እንችላለን?
የንግድ ሕግ ማሻሻያ በተወካዮች ምክር ቤት ጸደቀ
በኢትዮጵያ ከስልሳ (60) ዓመታት በላይ ሥራ ላይ የነበረው የንግድ ሕግ አዋጅ ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በትናንትናው ዕለት (በ16/07/2013 ዓም) በሙሉ ድምጽ ጸድቋል።
ተጨማሪየማምረቻ ተቋማት የሚያጋጥማቸውን የኃይል አቅርቦት ችግር ሊፈታ የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ተፈረመ
በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መካከል የማምረቻ ተቋማት የሚያጋጥማቸውን የኃይል አቅርቦት ችግር ሊፈታ የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ተፈረመ። የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት የማምረቻ ኢንዱስትሪ ተቋማት የሚያጋጥማቸውን የኃይል አቅርቦት ችግር ሊፈታ የሚያስችልና ሁለቱ ተቋማት ሀገራዊና ተቋማዊ ሥራዎችን በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ነው።
ተጨማሪመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ምርቱን ለገበያ ማቅረብ ጀመረ
በህግ ማስከበር ዘመቻው ምክንያት ባለፉት አራት ወራት ሥራ አቁሞ የነበረው በትግራይ ክልል የሚገኘው መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ የማምረት ሥራውን በመጀመር ምርቱን ለገበያ እያቀረበ መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ገለጹ። ፋብሪካው ምርቱን ለገበያ ማቅረብ መጀመሩ ወደላይ ወጥቶ የነበረውን ዋጋ ለማሻሻል የራሱ የሆነ አዎንታዊ ሚና እንደሚኖረው ጨምረው ተናግረዋል።
ተጨማሪየኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ 285 ብሔራዊ የጥራት ደረጃዎች መፅደቃቸውን አስታወቀ
የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ከብሔራዊ የደረጃ ዝግጅት ቴክኒክ ኮሚቴ ጋር በመሆን፣ የ285 ብሔራዊ የጥራት ደረጃዎችን በብሔራዊ ደረጃዎች ምክር ቤት ማፅደቁን አስታወቀ። ኤጀንሲው እንዳስታወቀው ለብሔራዊ የደረጃዎች ምክር ቤት ያቀረባቸው 285 የጥራት ደረጃዎች ፀድቀዋል። በስድስት ዘርፎች ተዘጋጅተው ከቀረቡት 285 ደረጃዎች 148 ያህሉ አዲስ ሲሆኑ፣ 44 የሚሆኑት የተከለሱና የተቀሩት 93 ደረጃዎች በፊት የነበሩና እንዲቀጥሉ …
ተጨማሪኢትዮጵያ እና ዓለም ባንክ የ100 ሚሊየን ዶላር ብደር ስምምነት ተፈራረሙ
ኢትዮጵያ እና ዓለም ባንክ የ100 ሚሊየን ዶላር ብደር ስምምነት ተፈራረሙ ፕሮጀክቱ የገንዘብ እጥረት ያለባቸውን ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች ብድር የሚያገኙበትን መንገድ ለማመቻቸት እና የኮቪድ ወረርሽኝ ስራቸው ላይ ጉዳት ላደረሰባቸው ሴቶች የሚውል መሆኑንም ሚኒስትር ዲኤታዋ ተናግረዋል። የብድር ስምምነቱ በጥቃቅን እና አነስተኛ ስራ ዘርፍ ለተሰማሩ ሴት ስራ ፈጣሪዎች የሚውል ነው ተብሏል። የስምምነት …
ተጨማሪየደቡብ ክልል የሥራ ዕድል ፈጠራ ምክር ቤት በሀዋሳ ከተማ ተመሰረተ
የደቡብ ክልል የሥራ ዕድል ፈጠራ ምክር ቤት መስራች ጉባኤ በሀዋሳ ተካሄደ። በጉባኤው ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የዘርፉ ባለድርሻ የተገኙበት እንደነበረ ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳየች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በጉባኤው የክልሉ ኢንተርፕራይዞች እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የስራ እድል ፈጠራ ምክር ቤት መስራች ጉባኤ ክልላዊ …
ተጨማሪመግቢያ የተሰኘ የዴሊቨሪ እና የቢዝነስ ሊስቲንግ መተግበሪያ አገልግሎት ላይ ዋለ
ኢቢዝ ኦንላይን ሶሉሽንስ ኃ.የተ.የግል ማኅበር “መግቢያ” (megbia.com) የተሰኘ አዲስ የሞባይል መተግበሪያ መልቀቁን አስታውቋል። ይህ መተግበሪያ ተጠቃሚዎች በአቅራቢያቸው የሚገኙ ቢዝነሶችን በቀላሉ እንዲያገኙ ከመርዳቱም በላይ፣ አዲስ አበባ ውስጥ ከየተኛውም ቦታ ሆነው ምግብ አዘው እንዲደርሳቸው ያስችላል። መተግበሪያው ሙሉ በሙሉ የተሠራው የኢትዮጵያ ትልቁ የቢዝነስ ፖርታል የ 2merkato.com ባለቤት በሆነው ድርጅት ባለሙያዎች ነው። ኢቢዝ በመቶዎች …
ተጨማሪ