መነሻ / Tag Archives: ethiopia (page 16)

Tag Archives: ethiopia

አዲስ የአኩሪ አተር ፕሮቲንና ዘይት ፋብሪካ ሥራ ጀመረ

ሪችላንድ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር በቡሬ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ991 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የገነባው የአኩሪ አተር ፕሮቲን እና የምግብ ዘይት ማምረቻ ፋብሪካ ሥራውን ጀመረ። የፋብሪካውን ሥራ መጀመር “ትዊት” ያደረጉት የኢትዮጵያ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል፣ ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር ምርቱን ኤክስፖርት በማድረግ 61 ሚሊየን 680 ሺህ ዶላር ለአገር እንደሚያስገኝ …

ተጨማሪ

የሲሚንቶ ፋብሪካ ኢንቨስትመንትን የሚከለክለው ሕግ ሊነሣ ነው

የሲሚንቶ እጥረትን ለማሻሻል እና እያደገ የመጣውን የሲሚንቶ ፍላጎት ለማሟላት በማሰብ፣ መንግሥት የአዳዲስ የሲሚንቶ ፋብሪካ ኢንቨስትመንቶችን የሚከለክለውን ሕግ ሊያነሣ መሆኑ ተገለጸ። ይህንኑ የሚያስረግጥ ማሻሻያ ደንብ ረቂቅ ለኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና ለንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ቀረቦ ውይይት እንደተደረገበት ተነግሮኛል ሲል አዲስ ማለዳ ዘግቧል። በኬሚካል እና ኮንስትራክሽን ግብዓት የኢንዱስትሪ ልማት ተቋም የሲሚንቶ ኢንዱስትሪ ጥናት እና …

ተጨማሪ

ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጪ የሌሎች የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

Fuel

የነሃሴ ወር የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል የተወሰነ ሲሆን የአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ በነሃሴ ወር በሊትር በብር 26.50 (ሃያ ስድስት ብር ከሃምሳ ሳንቲም) እንዲሸጥ ተወስኗል፡፡ በዓለም ገበያ ላይ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደአስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊያደርግ የሚችል መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ የዜና ምንጭ፦ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የፌስቡክ ገጽ

ተጨማሪ

መንገዶች ባለሥልጣን በ10 ዓመታት የኢትዮጵያን ወረዳዎች ሁሉ በአስፋልት መንገዶች ለማገናኘት አቅጃለሁ አለ

በመጪዎቹ 10 ዓመታት ሁሉንም የኢትዮጵያ ወረዳዎች በአስፋልት መንገዶች ለማገናኘት እቅድ መያዙን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ። ከዚህም በተጨማሪ ከጎረቤት አገራት ጋር የሚያገናኙ መንገዶች ግንባታ ለማከናወንም መሪ እቅዱ ትኩረት እንደሚያደርግ ተገልጿል። ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በ10 ዓመቱ መሪ የልማት እቅድ ላይ እየተወያየ በሚገኘበት መድረክ ላይ እቅዱን አቅርቧል። ለሦስት ቀናት …

ተጨማሪ

ፌስቡክ እና ቢዝነስ

facebook-business-page

ስድስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ፌስቡክን ይጠቀማሉ። ፌስቡክን በቀላሉ ቢዝነስን ለማሳደግ መጠቀም ስለሚቻል የተጠቃሚው ኢትዮጵያ ውስጥ መብዛት ለቢዝነሶች ጥሩ ዕድል ነው። ፌስቡክን ለቢዝነስ መጠቀም የሚቻልባቸው መንገዶች፦

ተጨማሪ

አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ አቅርቦት የሚያገኙበት ዕድል

(ታምራት አበራ) በኢንተርፕራይዝ ተደራጅተው እየሠሩ ሥራዎን የሚያካሂዱበት ካፒታል እያጠርዎ ይቸገራሉ? ወይስ የሚሠሩበት ማሽን ኪራይ ራስ ምታት ሆኖብዎታል? ይህ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚገጥማቸው ትልቁ ችግር ነው። ይህንን ችግር ለመቅረፍ የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ፋይናንስ ፕሮጀክት ነገሬ ብሎ በመሥራት ላይ ይገኛል፤ የእርስዎ ኢንተርፕራይዝ መስፈርቱን የሚያሟላ ከሆነም ከፕሮጀክቱ የፋይናንስ …

ተጨማሪ

ከስጋ እና ወተት ምርት 68.13 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ተገኘ

meat_slaughterhouse

በ2012 በጀት ዓመት 11 ወራት ውስጥ ወደ ውጪ ከተላከ የስጋና ወተት ምርት 68.13 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒቴር ገለጸ፡፡ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የስጋና ወተት ኢንስቲትዩት የ2012 በጀት ዓመት የ11 ወራት የኤክስፖርት አፈፃፀምን በዘርፉ ከተሰማሩ ባለድርሻ አካላት ጋር ገምግሟል፡፡ በበጀት ዓመቱ 11 ወራት ከስጋና ወተት 113.81 ሚሊዮን …

ተጨማሪ

በኢትዮጵያ ዘላቂ የቡና እርሻ ሊቋቋም ነው

coffee-plant

ኤስ ኬ ፎረስት ኩባንያ የተባለው የደቡብ ኮሪያ የደን ልማት ድርጅት በኢትዮጵያ ዘላቂ የቡና እርሻ ለማቋቋም ከኮሪያ የደን አገልግሎት ድርጅት ጋር በመቀናጀት እየሠራ ነው።፡፡ ኩባንያው እሮብ ዕለት እንዳስታወቀው በደቡብ ኢትዮጵያ የአካባቢው ተፈጥሮ እንዲያገግም ለማድረግ 700,000 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ 70,000 የእጣን እና ሌሎች የዛፍ ችግኞችን ለመትከል አቅዷል፡፡ ለዚህም በቡና እርሻ ወስጥ …

ተጨማሪ

የኢትዮጵያን የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ማሳደግ የሚያስችል ዘመቻ ይፋ ተደረገ

textile_leather

የጨርቃ ጨርቅ፣ አልባሳትና ቆዳ ኢንዱስትሪ የሰራተኞች ማህበር ፌዴሬሽን የኢትዮጵያን የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ማሳደግ የሚያስችል ዘመቻ ይፋ አደረገ። ዘርፉን ከማሳደግ ጎን ለጎን አሁን ላይ የጤና ስጋት ከሆነው ኮቪድ19 ጋር ተያይዞ በሃገር ውስጥ ባሉ ፋብሪካዎች የጤና እና የደህንነት የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራን ማከናወንም የዘመቻው አላማ ነው ተብሏል። አሁን ላይ ኢትዮጵያ በኮቪድ19 ምክንያት የእንቅስቃሴ …

ተጨማሪ