ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ያሬድ ጌታሁን እና በአራት መሥራች አባላት በ2012 ዓ.ም አጋማሽ ነው። ድርጅቱ የሻይ እና ቡና፣ የቁርስ እና ምሳ እንዲሁም እንዳንድ ቀለል ያሉ የሻይ ሰዓት አገልግሎቶችን በተለያዩ ስብሰባዎች ላይ በመገኘት አገልግሎት ይሰጣል።
ተጨማሪTag Archives: ethiopia
ዮብ ፈርኒቸር
ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ዮናስ ቢያድግልኝ በ2005 ዓ.ም. ነው። ይህ ድርጅት አጠቃላይ የእንጨት ሥራዎችን በጥራት ያመርታል።
ተጨማሪሙስጠፋ ጀማል ብረታ ብረት
ሙስጠፋ ጀማል ብረታ ብረት ድርጅት በአቶ ሙስጠፋ ጀማል ባላቤትነት የግል ኢንተርፕራይዝ ሆኖ ነው የተመሠረተው። ድርጅቱ በዋናነት የፍሬንች በሮችን የሚሠራ ሲሆን በተጨማሪም አጠቃላይ የብረታ ብረት ሥራዎችን ይሠራል።
ተጨማሪጋሻ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አክስዮን ማኅበር
ጋሻ አነስተኛ የፋይናንስ (ማይክሮፋይናንስ) ተቋም አክስዮን ማኅበር በአነስተኛ ንግድ ላይ ለተሰማሩ እንዲሁም ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የኅብረተ ሰብ ክፍሎች የብድር፣ የቁጠባ እና የአረቦን አገልግሎት ለመስጠት በ1990 ዓ.ም. ተቋቋመ። ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ለጋሻ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አክስዮን ማኅበር በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ …
ተጨማሪፊልጶስ፣ ኤደን እና ታረቀኝ ሽርክና ማኅበር
ፊልጶስ፣ ኤደን እና ታረቀኝ ሽርክና ማኅበር የተመሠረተው በ2004 ዓ.ም በአቶ የማነ አብርሐም እና ሦስት መሥራች አባላት ሲሆን ድርጅቱ የሚያመርታቸው ምርቶች አቸቶ (ኮምጣጤ) እና የለውዝ ቅቤ ናቸው። ድርጅቱ በቀን አንድ ሺህ ሊትር አቸቶ የማምረት አቅም አለው።
ተጨማሪጎዳዳ፣ መርጊያ እና ጓደኞቻቸው የሻማ ውጤቶች ማምረቻ
ድርጅቱ የተመሠረተው በ 2006 ዓ.ም በዐሥራ ዘጠኝ መሥራች አባላት ሲሆን አሁን ላይ ግን በዘጠኝ መሥራች አባላት እየሠራ ይገኛል። ከአባላቱም መካከል ሴቶችና አካል ጉዳተኞች ይገኙበታል፡፡ ድርጅቱ የተለያዩ ሻማዎች በተለያየ ዲዛይን ያመርታል እንዲሁም የጧፍ ምርቶችን ያመርታል።
ተጨማሪደቦ ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አ.ማ.
ደቦ ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አክስዮን ማኅበር የተቀላጠፈ የማይክሮፋይናንስ አገልግሎቶችን በመስጠት ለባለአክሲዮኖች ትርፍ ለማስገኘትና የደንበኞችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ለማሻሻል የተቋቋመ ተቋም ነው። ማኅበሩ በቀዳሚነት የተቀላጠፈና ውጤታማ የሆነ የቁጠባና የብድር አገልግሎቶችን ለደንበኞች ማቅረብ ዓላማው ያደረገ አክስዮን ማኅበር ነው። በአሁኑ ወቅት ደቦ ማይክሮፋይናንስ አዳዲስ አከባቢዎችና ማኅበረሰቦች ጋር በቀጣይነት ለመድረስና የተበዳሪዎችንና የተበዳሪ ቤተሰቦችን ኑሮ ሊያሻሽል …
ተጨማሪዳይናሚክ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አክስዮን ማኅበር
ዳይናሚክ በአነስተኛና መካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ገበሬዎች፣ በጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ተቋማትና ግለሰቦች ያለባቸውን የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽ አለመሆን ችግር ለመቅረፍ ግልፅ እና ስትራተጂካዊ ራዕይ፣ ተልእኮና ዓላማ ቀርፆ ከግቡ የሚያደርሱትን የገንዘብ ቁጠባና ብድር አገልግሎቶች በመስጠት ላይ ይገኛል። የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽ መሆን የተገለሉ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ለማብቃት፣ የመበልፀግ እድላቸውን ለማስፋትና …
ተጨማሪምሳሌ የብድር አገልግሎት – ከዳይናሚክ ማይክሮ ፋይናስ ተቋም አ.ማ.
ዳይናሚክ ማይክሮ ፋይናስ ተቋም አ.ማ. የኅብረተ ሰቡን ፍላጎት ያማከለ የፋይናንስ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። ተቋሙ የደንበኞቹን ፍላጎት መነሻ በማድረግ በየጊዜው አሠራሩን በቴክኖሎጂ እያዘመነ የሚገኝ ሲሆን አገልግሎቱን ለበርካታ የኅብረተ ሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ ቅርንጫፎችን እና የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት ላይ ይገኛል። ተቋሙ ወጣቱን የኅብረተ ሰብ ክፍል ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ በአሁኑ ሰዓት ምሳሌ …
ተጨማሪቪዥን ፈንድ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አክሲዮን ማኅበር
ቪዥን ፈንድ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአነስተኛ ገንዘብ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ 40/1988 የተቋቋመ አንጋፋ እና አስተማማኝ የገንዘብ ተቋም ነው። ተቋሙ በ91 አገልግሎት መስጫ የቅርንጫፍ ቢሮዎቹ አማካኝነት ተደራሽ እና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። ተቋሙ በአሁኑ ሰዓት በጥቅሉ 734,226 በላይ የብድር እና የቁጠባ ደንበኞችን ለማፍራት የቻለ ሲሆን የሰጠው ብድር …
ተጨማሪ