መነሻ / Tag Archives: ethiopia (page 15)

Tag Archives: ethiopia

ባለፉት ሶስት ወራት ከማዕድን ዘርፍ ከ178 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ተገኘ

gold-bullion

ባለፉት ሶስት ወራት ከማዕድን ዘርፍ ከ178 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ መገኘቱን  የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢ/ር ታከለ ኡማ ተናገሩ። ይህንንም ያሉት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የሶስት ወራት አፈፃፀም በተመለከተ ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው። ወደ ውጭ ተልከው የውጭ ምንዛሬ ካስገኙት ማዕድናት መካከል ወርቅ፣ ታንታለም፣ ኳርትዝ፣ ኢመራልድ፣ ሳፋየር እና እምነበረድ ተጠቃሾች …

ተጨማሪ

የስራ እድል መፍጠር ቅድሚያ እና ልዩ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

ለወጣቶች የስራ እድል የመፍጠር ጉዳይ ቅድሚያ እና ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ስራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። በተለያዩ ጊዜያት ለስራ ፈጠራ ተብለው የተበተኑ የወጣቶች ተዘዋዋሪ ፈንድ የብድር ገንዘብ በወቅቱ እንዲመለስ በማድረግ ለቀጣይ ወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ መልሶ ማበደር መቻል አለበትም ነው ያሉት። የአዲስ አበባ ከተማ የስራ እድል …

ተጨማሪ

የጥቃቅንና አነስተኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች ምርቶቻቸውን እንዲያሳድጉ ለማገዝ የገንዘብ ድጋፍ ተደረገ

የጥቃቅንና አነስተኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች ምርቶቻቸውን እንዲያሳድጉ ለማገዝ የታለመ የገንዘብ ድጋፍ ተደረገ። ስምምነቱ የተደረገው በኢትዮጵያ ንግድ እና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት፣ ፕሪሳይስ ኢንተርናሽናል ኮንሰልታንት እና የፈጠራ ድርጅት እንዲሁም የግሪን ኢትዮጵያ ማኑፋክቸሪንግ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ኢንተርፕራይዞች መካከል መሆኑ ተገልጿል። ድጋፉ በአምራች ዘርፍ ውስጥ የማያቋርጥ አፈጻጸም እና ቀጣይነት ያለው መሻሻል እንዲኖር ያደርጋል ተብሏል። በገንዘብ …

ተጨማሪ

አዳዲስ ገፅታ ያላቸው የገንዘብ ኖቶች እና አዲስ የ200 ብር ገንዘብ አገልግሎት ላይ ዋለ

የኢትዮጵያ መንግሥት አዳዲስ የደህንነት ገጽታዎች እና ሌሎችም መለያዎች የተካተቱባቸው የገንዘብ ዓይነቶችን ለግብይት እንደሚያውል በዛሬው ዕለት ተገልጿል። ነባሮቹ የ10፣ የ50 እና የ100 ብር የገንዘብ ዓይነቶች ሙሉ ለሙሉ የሚተኩ ይሆናል። አዲስ የ200 ብር ገንዘብም በተጨማሪነት ለግልጋሎት ይውላል። የ5 ብር ገንዘብ ባለበት ቀጥሎ፣ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ወደ ሣንቲም የሚለወጥ ይሆናል። ይህ የገንዘብ ቅያሪ …

ተጨማሪ

ከወጪ ንግድ ወደ 4 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቀደ

export-containers

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በተያዘው የ2013 በጀት አመት ከ ወጪ ንግድ 3.91 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት በዕቅድ መያዙን አስታወቀ። ከዚህም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ድጋፍና ክትትል ከሚያደርግባቸው የግብርና 2.918 ቢሊዮን እና የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ምርቶች 587.5 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንደሚጠበቅ ጨምሮ አስታውቋል ፡፡

ተጨማሪ

ፓልም የምግብ ዘይት ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ በሃገር ውስጥ በከፊል ሊመረት ነው

መንግስት በዜጎች ላይ የኑሮ ውድነት እንዳይፈጠር መሠረታዊ የምግብ ሸቀጦችን በድጎማ ከውጪ ከሚያሥገባቸው ሸቀጦች ውስጥ አንዱ የሆነውን ፓልም የምግብ ዘይት ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ በሃገር ውስጥ ለማምረት እንቅስቃሴ መጀመሩን በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ትራንስፎርሜሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬከተር አቶ አድማሱ ይፍሩ ተናገሩ፡፡

ተጨማሪ

በመስከረም ወር ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጪ የሌሎች የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

Fuel_Tanker

የመስከረም ወር የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል የተወሰነ ሲሆን የአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ በመስከረም ወር በሊትር በብር 26.97 (ሃያ ስድስት ብር ከዘጠና ሰባት ሳንቲም) እንዲሸጥ ተወስኗል፡፡ በዓለም ገበያ ላይ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደአስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊያደርግ የሚችል መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ የዜና ምንጭ፦ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስቴር የፌስቡክ ገጽ

ተጨማሪ

የሲሚንቶን እጥረት ለመቅረፍ እየተሠራ ነው – ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር

cement-bag

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በኢትዮጵያ የተፈጠረውን የሲሚንቶ ችግር ለመቅረፍ የፋብሪካዎችን የማምረት አቅም ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑን ገለጹ፡፡ ለሲሚንቶ እጥረት መከሰት በዋናነት የመለዋወጫ ችግር፣ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ፣ የግብዓት እጥረት ፣ የአመራርና የባለሙያ የክህሎት ክፍተት መኖር፣ የፀጥታ ችግር፣ የጥሬ እቃ አቅርቦት እና ሌሎች ችግሮች መኖራቸው ነው ያሉት አቶ መላኩ ችግሩን ለመቅረፍ …

ተጨማሪ

ኢትዮ ቴሌኮም ከነገ ጀምሮ የኢንተርኔት እና የድምፅ ጥቅል ቅናሽ ሊያደርግ ነው

ኢትዮ ቴሌኮም በኢንተርኔት እና በድምፅ ጥቅል አገልግሎቶቹ ላይ ቅናሽ ሊያደርግ መሆኑን አስታወቀ። ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆነው ይህ ቅናሽ የሚደረገው ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ነውም ተብሏል። ይህንን ያሳወቁት፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬሕይወት ታምሩ የድርጅቱን የ3 ዓመት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ እና የ2013 በጀት ዓመትን ዋና የትኩረት አቅጣጫ በተመለከተ መግለጫ …

ተጨማሪ

ኔዘርላንድስ ከኢትዮጵያ በመግዛት ቀዳሚ ሀገር ሆነች

የ2012 በጀት ዓመት የወጪ ንግድ ከፍተኛ ገቢ በማስገኘት ኔዘርላንድስ ቀዳሚ ሀገር ሆናለች ተባለ፡፡ አበባ፣ ቡና፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ የኤሌክትሪክ ውጤቶች፣ ጫማ፣ ቆዳ፣ ማርና ሰም፣ የቅባት እህሎች፣ የአልኮል መጠጦች፣ ጫት፣ ሻይ፣ ብረትና የመሳሰሉትን ከኢትዮጵያ በመቀበል 320,162.35 የአሜሪካን ዶላር በማስግኘት ቀዳሚ ሀገር ሆናለች፡፡ ጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ ቡና ጫማ፣ አበባ፣ የቆዳ ውጤቶችን፣ የቅባት …

ተጨማሪ