መነሻ / የቢዝነስ ዜና (page 5)

የቢዝነስ ዜና

በዚህ ስር የቢዝነስ ዜናዎች ይቀርባሉ።

ሚድሮክ ኢትዮጵያ 5 ሊትር ዘይት በ330 ብር ለሸማቾች አቀረበ

ሚድሮክ ኢትዮጵያ ግሩፕ የምግብ ዘይት በተመጣጣኝ ዋጋ በአዲስ አበባ ከተማ እያቀረበ መሆኑን አስታወቀ። መንግስት በምግብ ዘይት ላይ የጣለውን ቀረጥ ከማንሣቱ ጋር ተያይዞ፣ 5 ሊትሩን የምግብ ዘይት በ330 ብር ለሸማቾች እየሸጠ እንደሚገኝም ገልጿል። የሚድሮክ ኢትዮጵያ ግሩፕ የንግድ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር በቀለ ጎላዶ እንዳሉት፣ መንግስት የሸማቶችን የኑሮ ጫና በመጋራት …

ተጨማሪ

ኢትዮጵያ የጎብኚዎች መዳረሻ ስፍራዎቿን በኦን ላይን ማስተዋወቅ ጀመረች

የኢትዮጵያን የጎብኚዎች መዳረሻ ስፍራዎች በኦን ላይን ማስተዋወቅ መጀመሩን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ የቱሪዝም ዘርፉ ኮሮና ወረርሽኝ ያሳደረበትን ተጽዕኖ የሚያገግምበትን አቅጣጫ በማስቀመጥ 3 በሊዮን ዶላር ለማግኘት ማቀዱን በሚኒስቴሩ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ተወካይ አቶ እንደገና ደሳለኝ ለኢዜአ ገልጸዋል። በተጠናቀቀው በጀት አመት በኢትዮጵያ ኮሮና ባስከተለው ቀውስ ከዘርፉ ለማግኘት ከታቀደው ሁለት ሦስተኛውን ገቢ …

ተጨማሪ

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከተለያዩ ማዕድናት የወጪ ንግድ ከ207 ሚሊየን ዶላር በላይ ተገኘ

gold-bars

ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከተለያዩ ማዕድናት የወጪ ንግድ ከ207 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ አግኝታለች። በማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የማዕድን ግብይት ስራዎች ብቃት ማረጋገጥ ዳይሬክተር አቶ በትሩ ኃይሌ ለኢዜአ እንደገለጹት በ2012 በጀት ዓመት ከዘርፉ ለማግኘት የታቀደው ገቢ ከ260 ሚሊየን ዶላር በላይ ነው።

ተጨማሪ

50 ማኅበራት በሸገር ዳቦ ሽያጭ እና ማከፋፈያ ሥራ ሊሠሩ ነው

sheger-bread-shop

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የሥራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት 50 ማኅበራት ለሸገር ዳቦ መሸጫና ማከፋፈያ ሥራ ለመሰማራት ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸው ተገለፀ፡፡ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የሥራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሀም ተ/ሀይማኖት እንደተናገሩት በክ/ከተማው 20 ሲንግል እና 15 ደብል የሆኑ 35 ያገለገሉ የሸገር ባሶች የሥራ እድል ለመፍጠር …

ተጨማሪ

እንስራ የሸክላ ማዕከል ለሸክላ ሠሪዎች ምቹ የስራ ቦታ መሆኑ ተገለጸ

ensra-pottery

እንስራ የሸክላ ማዕከል ለሸክላ ሠሪዎች ምቹ የሥራ ቦታ መሆኑን የጉለሌ ክ/ከተማ የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ገለጸ፡፡ የጉለሌ ክ/ከተማ የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀይለማርያም አባይነህ እንደተናገሩት የከተማው ከንቲባ፣ የክ/ከተማ አስተዳደር እና የሚመለከለታቸው የቢሮ ኃላፊዎች ለዘርፉ ትኩረት ሰጥተው ማእከሉን በሚመች መልኩ በመገንባት ለ23 ሸክላ ሠሪ ኢንተርፕራይዞች …

ተጨማሪ

በቀን 2 ሚሊየን ዳቦ የሚያመርተው የሸገር ዳቦ ፋብሪካ ተመረቀ

sheger-bread

ሸገር ዳቦ ፋብሪካ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድና ኢ/ር ታከለ ኡማ በተገኙበት ተመርቆ በይፋ ስራውን ጀምሯል። የሸገር ዳቦ ፋብሪካ በሰዓት 80ሺህ በቀን ደግሞ 2 ሚሊየን ዳቦ የሚያመርት ሲሆን ለማከፋፈያ የሚውሉ ተሽከርካሪዎችም ተዘጋጅተዋል።

ተጨማሪ

የሲሚንቶ ዋጋ ተመን እና ቁጥጥር በአዲስ አበባ

cement-bag

መንግስት ካስቀመጠው የሲሚንቶ ዋጋ በላይ በሚሸጡ የሲሚንቶ አከፋፋዮች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ አስታወቀ ፡፡ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በሲሚንቶ ግብይት ውስጥ ያሉ ህገ-ወጥ ደላሎችን ከገበያ ሰንሰለቱ በማስወጣት እየናረ የመጣውን የሲሚንቶ ዋጋ ለማስተካከል የመሸጫ ዋጋ በመተመን ከፋብሪካ አውጥተው የሚያከፋፍሉ የመንግስት የልማት ድርጅቶችና መመሪያውን አክብረው ለመስራት የተስማሙ የግል ነጋዴዎች …

ተጨማሪ

ለሲሚንቶ አቅርቦት እጥረት እና ዋጋ ጭማሪ መፍትኄ

cement-factory

በገበያ ላይ እያጋጠመ ያለውን የሲሚንቶ አቅርቦት እጥረትና ዋጋ ጭማሪ ለመፍታት የአቅርቦት መጠንን ማሳደግ እንደሚገባ ተገለጸ። በኢፌዴሪ ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር አካላት የተመራ ልዑክ በገበያ ላይ የተከሰተውን የሲሚንቶ አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ በአምራች ድርጅቶች ላይ የሥራ ጉብኝት አድርጓል፡፡ ለሁለት ቀናት የቆየው የሥራ ጉብኝት ዋና ዓላማም ለምርት እጥረቱ በምክንያትነት የሚነሱ ጉዳዮችን …

ተጨማሪ

“እንሥራ” የሸክላ ስራ ማእከል ተመረቀ

pottery

“እንሥራ” የሸክላ ስራ ማእከል ተመረቀ። የሸክላ ስራ ማእከሉ ግንባታው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቀ ነው። የሸክላ ስራ ማእከሉን ኢ/ር ታከለ ኡማና ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦች መርቀው ስራ አስጀምረውታል። በማእከሉ 1000 በሸክላ ስራ ላይ የተሰማሩ እናቶች የመስሪያና የመሸጫ ቦታዎች ከተሟላ የማምረቻ ቦታ ከተሟላ ቁሳቁሶች ጋር የሚያገኙ ይሆናል።

ተጨማሪ