ሪችላንድ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር በቡሬ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ991 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የገነባው የአኩሪ አተር ፕሮቲን እና የምግብ ዘይት ማምረቻ ፋብሪካ ሥራውን ጀመረ። የፋብሪካውን ሥራ መጀመር “ትዊት” ያደረጉት የኢትዮጵያ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል፣ ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር ምርቱን ኤክስፖርት በማድረግ 61 ሚሊየን 680 ሺህ ዶላር ለአገር እንደሚያስገኝ …
ተጨማሪየቢዝነስ ዜና
የሲሚንቶ ፋብሪካ ኢንቨስትመንትን የሚከለክለው ሕግ ሊነሣ ነው
የሲሚንቶ እጥረትን ለማሻሻል እና እያደገ የመጣውን የሲሚንቶ ፍላጎት ለማሟላት በማሰብ፣ መንግሥት የአዳዲስ የሲሚንቶ ፋብሪካ ኢንቨስትመንቶችን የሚከለክለውን ሕግ ሊያነሣ መሆኑ ተገለጸ። ይህንኑ የሚያስረግጥ ማሻሻያ ደንብ ረቂቅ ለኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና ለንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ቀረቦ ውይይት እንደተደረገበት ተነግሮኛል ሲል አዲስ ማለዳ ዘግቧል። በኬሚካል እና ኮንስትራክሽን ግብዓት የኢንዱስትሪ ልማት ተቋም የሲሚንቶ ኢንዱስትሪ ጥናት እና …
ተጨማሪከአውሮፕላን ነዳጅ ውጪ የሌሎች የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ባለበት ይቀጥላል
የነሃሴ ወር የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል የተወሰነ ሲሆን የአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ በነሃሴ ወር በሊትር በብር 26.50 (ሃያ ስድስት ብር ከሃምሳ ሳንቲም) እንዲሸጥ ተወስኗል፡፡ በዓለም ገበያ ላይ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደአስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊያደርግ የሚችል መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ የዜና ምንጭ፦ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የፌስቡክ ገጽ
ተጨማሪበአዲስ አበባ 125 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እየተገነቡ እንደሆነ ምክትል ከንቲባው ተናገሩ
በአዲስ አበባ ከተማ በተመጣጣኝ ዋጋ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለማቅረብ 125 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በግንባታ ላይ እንደሚገኙ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጅነር) ገለፁ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ሲሆን በዚህ ወቅት ምክትል ከንቲባው የ2012 በጀት አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበዋል። በዚህ ሂደት ላይ …
ተጨማሪመንገዶች ባለሥልጣን በ10 ዓመታት የኢትዮጵያን ወረዳዎች ሁሉ በአስፋልት መንገዶች ለማገናኘት አቅጃለሁ አለ
በመጪዎቹ 10 ዓመታት ሁሉንም የኢትዮጵያ ወረዳዎች በአስፋልት መንገዶች ለማገናኘት እቅድ መያዙን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ። ከዚህም በተጨማሪ ከጎረቤት አገራት ጋር የሚያገናኙ መንገዶች ግንባታ ለማከናወንም መሪ እቅዱ ትኩረት እንደሚያደርግ ተገልጿል። ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በ10 ዓመቱ መሪ የልማት እቅድ ላይ እየተወያየ በሚገኘበት መድረክ ላይ እቅዱን አቅርቧል። ለሦስት ቀናት …
ተጨማሪተቋርጦ የከረመው የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ተመለሰ
በኢትዮጵያ ላለፉት ሦስት ሳምንታት ዝግ ሆኖ የቆየው የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ተመለሰ። የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን መገደል ተከትሎ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በተከሰተው አለመረጋጋት ሳቢያ የኢትዮጵያ መንግሥት የመደበኛና የሞባይል ኢንትርኔት አገልግሎቶችን በመላዋ አገሪቱ እንዲቋረጥ አድርጎ መቆየቱ ይታወሳል። ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ የዋይ-ፋይ የኢንተርኔት አገልግሎት መመለሱ ይታወቃል። በርካታ ተጠቃሚ ያለው የሞባይል ኢንተርኔት …
ተጨማሪየክልል ታርጋ ያላቸው ባለሁለት እግር ተሽከርካሪዎች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ተወሰነ
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የክልል ታርጋ ያላቸው ባለሁለት እግር ተሽከርካሪዎች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ወሰነ። የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ስጦታው አካለ በሰጡት መግለጫ የአዲስ አበባ ታርጋ ካላቸው የሁለት እግር ተሽከርካሪዎች ውጭ ሌሎች ወደ መዲናይቱ መግባትም ሆነ በከተማዋ መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም በተሰሩ ስራዎች እና በተከናወኑ ግኝቶች የክልል …
ተጨማሪየኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በ19.9 ቢሊየን ብር 12 መንገዶች ሊያሠራ ነው
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በ19.9 ቢሊየን ብር ወጪ 12 መንገዶችን ለመገንባት የሚያስችል የውል ስምምነት ፊርማ ከተቋራጮች ጋር ተፈራርሟል። የስምምነት ፊርማ የተከናወነባቸው 12ቱ የመንገድ ፕሮጀክቶች በድምሩ 825.23 ኪ.ሜ ርዝመት ያላቸው መሆኑም ታውቋል። ለግንባታው ከሚያስፈልገው ወጪ መካከል የአሥሩ መንገዶች በኢትዮጵያ መንግሥት የተሸፈነ ሲሆን፣ ሁለቱ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብድር ነው ተብሏል። የውል ስምምነቱን ከፈረሙት …
ተጨማሪሸገር ዳቦ በ400 ማከፋፈያዎች እየተሰራጨ ነው ተባለ
የሸገር ዳቦ በተመጣጣኝ ዋጋ በ400 ማከፋፈያዎች ለአዲስ አበባና አካባቢው ነዋሪዎች እየተሰራጨ እንደሚገኝ ተገለፀ። የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ ሲሳይ ደበበ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፣ ሸገር ዳቦ ፋብሪካ የሚያመርታቸውን ዳቦዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለነዋሪዎች ማሰራጨት ጀምሯል። ፋብሪካው በዋነኛነት የዳቦ ዋጋን የኅብረተሰቡን ገቢ ባገናዘበ አነስተኛ ዋጋ የማቅረብ ዓላማን ይዞ እንደመግባቱ ተደራሽነቱ ላይ በጥብቅ እየተሠራ መሆኑን …
ተጨማሪሚድሮክ ኢትዮጵያ 5 ሊትር ዘይት በ330 ብር ለሸማቾች አቀረበ
ሚድሮክ ኢትዮጵያ ግሩፕ የምግብ ዘይት በተመጣጣኝ ዋጋ በአዲስ አበባ ከተማ እያቀረበ መሆኑን አስታወቀ። መንግስት በምግብ ዘይት ላይ የጣለውን ቀረጥ ከማንሣቱ ጋር ተያይዞ፣ 5 ሊትሩን የምግብ ዘይት በ330 ብር ለሸማቾች እየሸጠ እንደሚገኝም ገልጿል። የሚድሮክ ኢትዮጵያ ግሩፕ የንግድ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር በቀለ ጎላዶ እንዳሉት፣ መንግስት የሸማቶችን የኑሮ ጫና በመጋራት …
ተጨማሪ