ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው ኢንተርፕራይዞቹ በኬር ኢትዮጵያ በተመቻቸላቸው ዕድል የ”ከፍታ” አገልግሎትን ተጠቅመው እንዴት የጨረታ መረጃዎችን በቀላሉ ማግኘት እንደሚችሉ በተጨማሪም እንዴት አድርገው ድርጅታቸውን፣ ምርታቸውን እና አግልግሎታቸውን እንደሚያስተዋውቁ ነው።
ተጨማሪየጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ
በኮንስትራክሽን ዘርፍ የ4 ሳምንት የሙያ ክህሎት ሥልጠናዎች
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለተሰማራችሁ ኢንተርፕራይዞች ከቤት እስከ ከተማ የከተማ ማዕከል (The Urban Center) የ4 ሳምንት የሙያ ክህሎት ሥልጠናዎች በነጻ ይሰጣል። ሥልጠናዎቹ የሚሰጡት በሚከተሉት ዘርፎች ላይ ነው፦ 1. በአልሙኒየም ሥራ 2. በቀለም እና ሕንጻ ማጠናቀቅ ሥራ 3. በእንጨት ሥራ
ተጨማሪማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት 5.5 ቢሊዮን ብር ከአዋሽ ባንክ በብድር ሊያገኙ ነው
አዋሽ ባንክ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ለተለያዩ የማክሮ ፋይናንስ ተቋማት 5.5 ቢሊዮን ብር ብድር ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ። ባንኩ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ለማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት (ለአነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋማት) ለማበደር ካቀደው በጀት ውስጥ 1.5 ቢሊዮን ብር የሚሆነውን ብድር ተጠቃሚ ከሚሆኑ ዘጠኝ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ጋር ባለፈው ሐሙስ ሐምሌ 21 ቀን …
ተጨማሪለኢንተርፕራይዞች በየደረጃው የሚሰጡ ድጋፎች
ይህ ጽሑፍ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በየደረጃው የሚሰጡ ድጋፎችን ያካተተ ሲሆን ዓላማውም ኢንተርፕራይዞች ማግኘት የሚችሉትን የድጋፍ ዓይነቶች በቀላሉ ተረድተው ተጠቃሚ ኢንዲሆኑ ለማድረግ ነው። ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽሕፈት ቤት በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።
ተጨማሪከፍተኛ ኢንዱስትሪ ዕድገት ደረጃ
ወደ ከፍተኛ ኢንዱስትሪ ዕድገት ደረጃ የሚሸጋገሩ ኢንተርፕራይዞች ሊያሟላቸው የሚገቡ መስፈርቶች በሥራ ዕድል ፈጠራ ሀ) በኢንዲስትሪ ዘርፍ የተሰማራ ኢንተርፕራይዝ የፈጠረው ቋሚ የሥራ ዕድል የኢንተርፕራይዙን አባላት ጨምሮ 101 በላይ ሆኖ በአገግልሎት ዘርፍ ደግሞ ከ 31 በላይ መሆን አለበት። ለ) በኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማራ ኢንተርፕራይዝ በዓመት ውስጥ በጊዜያዊነት የፈጠረው የሥራ ዕድል ከ 31 ሰዎች …
ተጨማሪየሮያሊቲ ክፍያ ለባህላዊ ወርቅ አምራቾች ሙሉ በሙሉ ተነሳላቸው
በባህላዊ መንገድ ወርቅ እያመረቱ ለባንክ የሚያቀርቡ አምራቾች ለክልል ሲከፍሉ የነበረው የሮያሊቲ ክፍያ ሙሉ በሙሉ በክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች መነሳቱ ተገለጸ። ይህን የገለጹት የማዕድን እና የኢነርጂ ሚኒስትሩ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) በፌስቡክ ገጻቸው ነው፤ ውሳኔውንም የሚመሰገን ነው ያሉት ሚኒስትሩ አክለውም “ይህ እርምጃ ለባህላዊ የማዕድን ምርት እንደሀገር የሰጠነው ትኩረት ማሳያ ነው” ብለዋል። የባህላዊ እና …
ተጨማሪየከተማ ግብርና፦ በአዲስ አበባ በዘንድሮው የመኸር ወቅት ከ5000 ሄክታር በላይ መሬት ሙሉ በሙሉ በዘር ተሸፈነ
በአዲስ አበባ ከተማ በዘንድሮው የመኸር ወቅት ከአምስት ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ሙሉ በሙሉ በዘር መሸፈኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደሮችና ከተማ ግብርና ኮሚሽን አስታወቀ። የኮሚሽኑ ኮሚሽነር መኮንን ሌንጅሶ ከቦሌ ክፍለ ከተማ አመራሮች ጋር በመሆን የከተማ ግብርና የሥራ እንቅስቃሴን በቦሌ ክፍለ ከተማ በመገኘት የመስክ ጉብኝት አድርገዋል።
ተጨማሪየኢንተርፕራይዞችን የገበያ ትስስር ለማሳደግ ኤግዚብሽንና ባዛር ጠቃሚ መሆኑ ተገለጸ
በኮቪድ ተፅዕኖ ተቀዛቅዞ የነበረውን የኢንተርፕራይዞችን የገበያ ትስስር ለማሳደግ ኤግዚብሽንና ባዛር ጠቃሚ መሆኑን የአዲስ አበባ የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ገለጸ። በ2014 አዲስ ዓመት ዋዜማ ኤግዚብሽንና ባዛር በዐሥራ አንዱም ክፍለ ከተሞች አንድ ሺህ ዐሥር ኢንተርፕራይዞች መሳተፋቸውን በቢሮው የገበያ ልማትና ግብይት ዳይሬክቶሬት ገልጿል፡፡
ተጨማሪለኢንተርፕይዞች ማገገሚያና መቋቋሚያ ብድር
ማስተርካርድ ፋውንዴሽን የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕይዞችን ማገገሚያና መቋቋሚያ ፕሮጀክት ይህ ፕሮጀክት የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ከማስተርካርድ ፋውንዴሽንና ከፈርስት ኮንሰልት ጋር በመተባበር የሚተገበር ነው። የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ በኮሮና ወረርሽኝ የተነሳ የደረሰውን የንግድ መቀዛቀዝ ለመገዳደር ጥረት እያደረጉ ያሉ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ማገዝ ነው። ፕሮጀክቱ ዝቅተኛ ወለድ እና የእፎይታ ጊዜ ያለው ብድር በተመረጡ የፋይናንስ …
ተጨማሪበኮቪድ-19 ለተጎዱ ኢንተርፕራይዞች የሚውል 207 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ስምምነት ተፈረመ
ዛሬ በገንዘብ ሚኒሰቴር በተደረገ የፊርማ ስነ-ሰርዓት ላይ በኢትዮጰያ መንግስት እና በዓለም ባንክ የ907 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈረመ። ከዚህ ውስጥ 200 ሚሊዮን ዶላር በኢትዮጵያ ውስጥ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ለተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች የሚውል ነው። የ200 ሚሊዮን ዶላሩ ድጋፍ ዒላማ ያደረገው በተለይ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ክፉኛ ተጎድተው፣ ነገር ግን ቢደገፉ በሥራቸው አዋጭ ሆነው …
ተጨማሪ