ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ አልአዛር ዓለም እና በአቶ ሄኖክ በ1996 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የእንጨት እና የብረታ ብረት ሥራዎችን የሚሠራ ድርጅት ሲሆን በነዚህ ሥራዎች ውስጥ ውስጥ የዲዛይን እና ፈኒቸር ሥራዎች ይካተታሉ።
ተጨማሪTag Archives: ከፍታ
ድባብ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር
ድባብ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር ሁሉንም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ነዋሪዎችን አባል ለማድረግ ዓላማ ይዞ የተቋቋመ የኅብረት ሥራ ማኅበር የፋይናንስ ተቋም ነው።
ተጨማሪእቴጌ ዳቦ እና ብስኩት
ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ሳሙኤል በለጠ፣ በሁለት ሴቶች እና አንድ ወንድ መሥራች አባላት በ2010 ዓ.ም. ነው። ይህ ድርጅት የሚያመርታቸው ምርቶች ምግብ እና መጠጥ ሲሆኑ በአሁን ጊዜ በዳቦ፣ ኩኪስ እና ጨው ምርቶች ላይ በስፋት እየሠራ ይገኛል።
ተጨማሪ“የከፍታ ፓኬጅ ህይወታችንን አቅልሎልናል” ገነት፣ ሰብለ እና ጓደኞቻቸው የኅትመት ሥራ
ድርጅቱ የተመሠረተው በወ/ሮ የምሥራች ባልቻ እና አራት መሥራች አባላት በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ ኅትመት ሥራዎችን የሚሠራ እና የጽሕፈት መሣርያ (ስቴሽነሪ) እቃዎችን የሚያቀርብ ድርጅት ነው።
ተጨማሪግሎባል የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/የኅብረት ሥራ ማኅበር
ግሎባል የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/የኅብረት ሥራ ማኅበር በአዋጅ 985/2009 እና ይህን አዋጅ ለማስፈጸም በወጡ ደንቦች መሠረት የተቋቋመት የኅብረት ሥራ ማኅበር ነው።
ተጨማሪተዋበ እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ
ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ተዋበ ምኔነህ በ2004 ዓ.ም. የግል ኢንተርፕራይዝ ሆኖ ነው። ይህ ድርጅት አጠቃላይ የእንጨት እና የብረታ ብረት ሥራዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ይሠራል።
ተጨማሪኑ ነገን ዛሬ እንሥራ – ፍኖት የገንዘብ ቁጠባና ብድር
ፍኖት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር ኅብረተ ሰቡ ከሚያገኘው ገቢ ላይ የተወሰነ ገንዘብ በመቆጠብ ራሱን በራሱ እንዲረዳና የቁጠባ ባህልን በማዳበር ፈጣን የሆነ የብድር አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ በ379 መስራች አባላት (307 ወንድ እና 72 ሴት) መጋቢት 15 ቀን፣ 2011 ዓ.ም. በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ተመሠረተ።
ተጨማሪገነት ልብስ ስፌት
ድርጅቱ የተመሠረተው በ2011 ዓ.ም. በወ/ሮ ገነት የግል ኢንተርፕራይዝ ሆኖ ነው። ይህ ድርጅት የሚያመርታቸው ምርቶች ባህላዊ እና ዘመናዊ ልብሶችን ሲሆን በይበልጥ ደግሞ የሴቶች እና የህጻናት ባህላዊ ልብሶችን ከዘመናዊ ልብሶች ጋር በማጣመር ያመርታል።
ተጨማሪጽጌረዳ ካሳሁን ልብስ ስፌት (ኪያ ዲዛይን)
ድርጅቱ የተመሠረተው በወ/ት ጽጌረዳ ካሳሁን 2012 ዓ.ም የግል ኢንተርፕራይዝ ሆኖ ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የልብስ ስፌት ሥራዎችን የሚሠራ ሲሆን በዋናነት ግን የአፍሪካ የባህል ልብሶችን ያመርታል።
ተጨማሪዘኪ ባግስ
ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ዘካርያስ እስጢፋኖስ በ2011 ዓ.ም. የግል ኢንተርፕራይዝ በመሆን ነው። ይህ ድርጅት የሚያመርታቸው ምርቶች አጠቃላይ የቆዳ ቦርሳዎችን ሲሆን ምርቶቹን በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚ እና ነጋዴ ያከፋፍላል።
ተጨማሪ