መነሻ / Tag Archives: ከፍታ (page 4)

Tag Archives: ከፍታ

መአዛ የጽዳት ዕቃዎች

ኡቡንቱ ኤራ ኅ.የተ.የግ.ማኅበር የተመሠረተው በወ/ሮ መአዛ ታምራት በ2008 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የንጽህና መጠበቂያ እና የጽዳት ዕቃዎችን  በጥራት እና በተመጣጣኝ ዋጋ በማምረት ለገበያ ያቀርባል።

ተጨማሪ

ወይንሸት፣ ፍቅርተ እና ጓደኞቻቸው የቀርከሃ ሥራ

ወይንሸት፣ ፍቅርተ እና ጓደኞቻቸው የቀርከሃ ሥራ ኅብረት ሽርክና ማኅበር የተመሠረተው በወ/ሮ ፍቅርተ ገብሬ እና ሁለት መሥራች አባላት በ2009 ዓ.ም. ነው። የቤት ማስዋቢያ እቃዎች እንዲሁም ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ የፈርኒቸር ሥራዎችን ከእንጨት ውጤቶች ጋር በማቀናጅት (በማመሳጠር) ያመርታል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ የወንድ እና የሴት ጌጣጌጥ ምርቶችን (ማጌጭያዎችን) ያመርታል።

ተጨማሪ

ሮቢ ጋርመንት

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ሮቤል ነጋሽ በ2008 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ በዋናነት የሚሠራው የወንዶች ሙሉ ልብስ ሲሆን በዚህም ሥራ በጣም የዳበረ እና የረዥም ጊዜ ልምድ አለው። ከዚህ በተጨማሪ አጠቃላይ አልባሳትን ያመርታል።

ተጨማሪ

ቤተሰብ የገንዘብ ብድርና ቁጠባ ተቋም

ቤተሰብ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር የኅብረት ሥራ ማኅበራትን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 985/2009 መሠረት የተቋቋመ ሕጋዊ ድርጅት ነው። ማኅበሩ ዝቅተኛውን የማኅበረሰብ ክፍልን እና የሥራ ፈጣሪዎችን በተለይ ሴቶችን ማዕከል በማድረግ የጋራ በሆኑት ዕሴቶች ላይ ማለትም ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ችግሮቻቸውን ለመፍታት እንዲችሉ የተቋቋመ የኅብረት ሥራ ማኅበር ነው።

ተጨማሪ

መንሽ የግብርና ማሺነሪ፣ መሣርያዎች ሌሎች የብረት ሥራዎች

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ውብሸት ደለለኝ እና በጓደኞቻቸው በ2002 ዓ.ም. ነው። የጤፍ መውቂያ ማሽን በዋናነት የሚያመርተው ምርት ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ የተለያዩ የእርሻ መሣሪያዎ ች(የግብርና መሣርያዎች)፣ የውሃ መሳቢያ እና መቆፈሪያዎች፣ የባዮ ጋዝ ምድጃዎች እና ማብላያዎች፣ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች እና ለትምህርት ቤት እና ለቢሮ የሚሆኑ የፈርኒቸር ምርቶችንም ያመርታል።

ተጨማሪ

ኤልሳቢ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ.

ኤልሳቢ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአነስተኛ ገንዘብ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 626/2001 መሠረት በአንድ መቶ ሚሊዮን ብር (ብር 100,000,000) ካፒታል የተቋቋመ የፋይናንስ ተቋም ነው። ተቋሙ በቅርንጫፍ ቢሮዎቹ አማካኝነት ተደራሽ እና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። ኤልሳቢ በዋናነት የባንክ አገልግሎት ማግኘት ላልቻሉ ማኅበረ ሰቦች (ጥቃቅን ሥራ ፈጣሪ እና አነስተኛ …

ተጨማሪ

ዮሴፍ እና መስፍን የአልሙኒየም ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ዮሴፍ ንጉሤ እና በጓደኛቸው 2011 ዓ.ም. የኅብረት ሽርክና ማኅበር ሆኖ ነው። ማኅበሩ አጠቃላይ የአልሙኒየም ሥራዎችን በጥራት እና በተጠጣጣኝ ዋጋ የማምረት እና የመገጣጠም ሥራ ይሠራል።

ተጨማሪ