መነሻ / Tag Archives: ከፍታ (page 3)

Tag Archives: ከፍታ

ቀንዲል ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ.

kendi-logo

ቀንዲል በአብዛኛው ሀገሪቱ ክልሎች በከተማና በገጠር የሚኖሩ ለሥራ ተነሳሽነት ያላቸው ዜጎች በተለይም ለባንክ አገልግሎት ዕድል ለተነፈጉ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ነጋዴዎችና አርሶ አደሮች የፋይናንስ አገልግሎት ለመስጠት ከብሔራዊ ባንክ ፍቃድ በማግኘት የተቋቋመ ነው። ለቁም ነገር ተበደሩ፣ በጊዜው ክፈሉ፣ ዘወትር ቆጥቡ!

ተጨማሪ

ግሬት የገንዘብ ቁጠባና ብድር

ግሬት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር ማኅበረ ሰቡ ከሚያገኘው ገቢ ላይ በመቆጠብ የቁጠባን ባሕል በማዳበር ፈጣን የሆነ የብድር አገልግሎት ለመስጠት፣ በግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ ሥራ አመራር ሃሳብ አመንጪነት እና በሠራተኞች መሥራችነት ጥቅምት 5 ቀን፣ 2012 ዓ.ም. በቦሌ ክፍለ ከተማ ተመሠረተ። ግሬት! ለእድገት ጽኑ መሠረት!

ተጨማሪ

ተደራሽ የገንዘብ ቁጠባና ብድር

credit-and-saving

ተደራሽ ማኅበረ ሰብ አቀፍ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር “ትንሽ ቆጥበው ትልቅ ይሁኑ” የሚል መሪ ቃል ይዞ የተመሠረተ ተቋም ነው።

ተጨማሪ

ታፍ ሌዘር

taf-leather

ታፍ ሌዘር የተመሠረተው በ 2004 ዓ.ም. በወይዘሮ ትዝታ አሰፋ እና በስድስት ሴት መሥራች አባላት ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የቆዳ ውጤት የሆኑ ምርቶችን ያመርታል።

ተጨማሪ

ብራይት ማኑፋክቸሪንግ

bright_manufacturing_logo

ብራይት ማኑፋክቸሪንግ የተመሠረተው በአቶ ሠለሞን መገርሳ እና በሁለት ጓደኞቻቸው በ2021 (እ.ኤ.አ.) ነው። ድርጅቱ የእንሰት ተክልን በመጠቀም ከግሉተን ነጻ (gluten free) የሆነ ስታርች እና የፋይበር ምርቶችን ያመርታል። እነዚህም ምርቶች ለተለያዩ ተጠቃሚ ደንበኞች፣ የግብርና ውጤት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች፣ ሱፐርማርኬቶች እና የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ያቀርባል። በቅርቡም ወደ ውጭ ሀገር ምርቱን ለመላክ (export ለማድረግ) አውሮፓ …

ተጨማሪ

ዓለም እና ተገኘወርቅ የሌዘር ምርቶች ማምረቻ

ዓለም እና ተገኘወርቅ የሌዘር ምርቶች ማምረቻ የኅብረት ሽርክና ማኅበር የተመሠረተው በአቶ ተገኘወርቅ ጫንያለው በ2008 ዓ.ም. ነው። ይህ ድርጅት አጠቃላይ የቆዳ ውጤቶችን በጥራት የሚያመርት ድርጅት ሲሆን በይበልጥ ደግሞ ጫማዎችን በስፋት እያመረተ የሚገኝ ድርጅት ነው።

ተጨማሪ

መአዛ የጽዳት ዕቃዎች

ኡቡንቱ ኤራ ኅ.የተ.የግ.ማኅበር የተመሠረተው በወ/ሮ መአዛ ታምራት በ2008 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የንጽህና መጠበቂያ እና የጽዳት ዕቃዎችን  በጥራት እና በተመጣጣኝ ዋጋ በማምረት ለገበያ ያቀርባል።

ተጨማሪ

ወይንሸት፣ ፍቅርተ እና ጓደኞቻቸው የቀርከሃ ሥራ

ወይንሸት፣ ፍቅርተ እና ጓደኞቻቸው የቀርከሃ ሥራ ኅብረት ሽርክና ማኅበር የተመሠረተው በወ/ሮ ፍቅርተ ገብሬ እና ሁለት መሥራች አባላት በ2009 ዓ.ም. ነው። የቤት ማስዋቢያ እቃዎች እንዲሁም ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ የፈርኒቸር ሥራዎችን ከእንጨት ውጤቶች ጋር በማቀናጅት (በማመሳጠር) ያመርታል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ የወንድ እና የሴት ጌጣጌጥ ምርቶችን (ማጌጭያዎችን) ያመርታል።

ተጨማሪ