በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለተሰማራችሁ ኢንተርፕራይዞች ከቤት እስከ ከተማ የከተማ ማዕከል (The Urban Center) የ4 ሳምንት የሙያ ክህሎት ሥልጠናዎች በነጻ ይሰጣል። ሥልጠናዎቹ የሚሰጡት በሚከተሉት ዘርፎች ላይ ነው፦ 1. በአልሙኒየም ሥራ 2. በቀለም እና ሕንጻ ማጠናቀቅ ሥራ 3. በእንጨት ሥራ
ተጨማሪTag Archives: addis ababa
ሙሉጌታ ሰማኸኝ በሽር የኅትመት እና ማስታወቂያ ሥራ
ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ሙሉጌታ ሰማኸኝ በ2009 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የኅትመት እና የማስታወቂያ ሥራዎችን ይሠራል።
ተጨማሪመጣለም ጌጤ ጠቅላላ የእንጨት፣ ብረታብረት እና አልሙኒየም ሥራዎች
መጣለም ጌጤ ጠቅላላ የእንጨት፣ ብረታብረት እና አልሙኒየም ሥራዎች የግል ኢንተርፕራይዝ በመጣለም ጌጤ በ2006 ዓ.ም. ተመሰረተ።
ተጨማሪጀንዲ ሌዘር
ድርጅቱ የተመሠረተው በወይዘሪት ናዲያ ይመር በ2012 ዓ.ም. ነው። ጀንዲ ሌዘር ጥራት ያላቸውን የቆዳ ውጤቶች በማምረት እና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ራሱን እና ማኅበረ ሰቡን እየጠቀመ ይገኛል። ወደ ፊት ደግሞ ለተጨማሪ ዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር እንዲሁም የሚያመርታቸውን ምርቶች ወደ ውጭ ሃገር በመላክ ለሃገሪቱ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት የበኩሉን አስተዋፅዖ የማበርከት እቅድ አለው።
ተጨማሪእሸት አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ.
እሸት አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ. በ2000 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ አግኝቶ የቁጠባ እና ብድር አገልግሎት በመስጠት የገጠሩንና የከተማውን ማኅበረ ሰብ የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል በመሥራት ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው።
ተጨማሪአብዲ፣ ከኪያ እና ጓደኞቻቸው የሌዘር ምርቶች
ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ አብዲ ድሪባ 2012 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ነው። የሚያመርታቸው ምርቶች ጥራታቸውን የጠበቁ አጠቃላይ የቆዳ ምርቶች እንደ ጫማ፣ ጃኬት እና ቦርሳዎችን ሲሆን፣ እንዲሁም ለቆዳ ሥራ የሚውል ጥሬ እቃ ያቀርባል።
ተጨማሪካታሊስት ላብ ትሬዲንግ
ድርጅቱ የተመሠረተው በ2012 ዓ.ም. መጨረሻ በወ/ት ሠርካለም ተሰማ የግል ኢንተርፕራይዝ ሆኖ ነው። ድርጅቱ የላብራቶሪ እቃዎችን እና የትምህርት መርጃ መሣሪያዎችን ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ዩኒቨርሲቲዎች ያቀርባል።
ተጨማሪዋቢ ጋርመንት
ፈለቁ አያሌው ልብስ ስፌት (ዋቢ ጋርመንት) የተመሠረተው በወ/ሮ ፈለቁ 2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ በአሁን ሰዓት በዋናነት የሚያመርታቸው ልብሶች የህጻናት ቱታ እና ቬሎዎችን በስፋት እያመረተ ይገኛል።
ተጨማሪየበጋእሸት አሰፋ እና ጓደኞቻቸው ብረታ ብረት ሥራ
ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ የበጋእሸት ገብሬ እና አራት መሥራች አባላት 2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ የሚያመርታቸው ምርቶች አጠቃላይ የብረታ ብረት ሥራዎች እንዲሁም የማሽነሪ ሥራዎች ናቸው።
ተጨማሪኒዮን ቢልዲንግ ኮንትራክተር
ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ሁሴን ፍቃዱ የግል ኢንተርፕራይዝ በመሆን በ2008 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች አጠቃላይ ኮንስትራክሽን፣ ሕንጻ ግንባታ እና የውሃ ሰፕላይ ሥራዎችን ይሠራል።
ተጨማሪ