መነሻ / Tag Archives: MSE

Tag Archives: MSE

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የ4 ሳምንት የሙያ ክህሎት ሥልጠናዎች

TUC_NSP_2merkato_poster_ad_20221031-04

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለተሰማራችሁ ኢንተርፕራይዞች ከቤት እስከ ከተማ የከተማ ማዕከል (The Urban Center) የ4 ሳምንት የሙያ ክህሎት ሥልጠናዎች በነጻ ይሰጣል። ሥልጠናዎቹ የሚሰጡት በሚከተሉት ዘርፎች ላይ ነው፦ 1. በአልሙኒየም ሥራ 2. በቀለም እና ሕንጻ ማጠናቀቅ ሥራ 3. በእንጨት ሥራ

ተጨማሪ

ተዋበ እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ተዋበ ምኔነህ በ2004 ዓ.ም. የግል ኢንተርፕራይዝ ሆኖ ነው። ይህ ድርጅት አጠቃላይ የእንጨት እና የብረታ ብረት ሥራዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ይሠራል።

ተጨማሪ

ኑ ነገን ዛሬ እንሥራ – ፍኖት የገንዘብ ቁጠባና ብድር

finot-logo

ፍኖት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር ኅብረተ ሰቡ ከሚያገኘው ገቢ ላይ የተወሰነ ገንዘብ በመቆጠብ ራሱን በራሱ እንዲረዳና የቁጠባ ባህልን በማዳበር ፈጣን የሆነ የብድር አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ በ379 መስራች አባላት (307 ወንድ እና 72 ሴት) መጋቢት 15 ቀን፣ 2011 ዓ.ም. በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ተመሠረተ።

ተጨማሪ

አጸደ፣ ነሲባ እና ጓደኞቻቸው የእንጀራ መጋገር ሥራ

ይህ ኢንተርፕራይዝ የተመሠረተው በ 2001 ዓ.ም በ ወ/ሮ ነሲባ ራህመቶ እና በዐሥራ ዘጠኝ መሥራች አባላት ነው። ድርጅቱ በሀያ መሥራች አባላት ቢመሰረትም በነበረው አስቸጋሪ ሁኔታ ዘጠኝ አባላት የቀን ሥራ ብንሠራ ይሻለናል ብለው ሲያቋርጡ፣ አንድ አባል ደግሞ በሞት ስለተለየች በአሁን ጊዜ ዐሥር መስራች አባላት በድርጅቱ ውስጥ ይገኛሉ።

ተጨማሪ

ለችግሮች መፍትኄ በመፈለግ ለስኬት መብቃት – ዛጎል ዲዛይን

ዛጎል ጋርመንት ዲዛይን በመቅደስ ተስፋዬ እና አምስት መሥራች አባላት በ2011 ዓ.ም ተመሠረተ። አሁን ላይ አምስት መሥራች አባላት ናቸው በሥራ ላይ የሚገኙት። ዛጎል ጋርመንት ዲዛይን በሦስት የልብስ ስፌት ማሽኖች ነው ሥራ የጀመረው። ዛጎል ዲዛየን የሚያመርተው አጠቃላይ የአልባሳት ምርቶችን ነው። እንዲሁም ደንበኛ በሚፈልገው ዲዛይን የሚፈልገውን ዲዛይን ሳምፕል በማምጣት ባመጡት ሳምፕል መሠረት የሚፈልጉትን …

ተጨማሪ

ዓላማ እና የሙያ ፍቅር – ሰዋሰው የቆዳ ውጤቶች

ሰዋሰው የቆዳ ውጤቶች የተመሠረተው በ2011 ዓ.ም በአቶ ሰዋሰው ፍቅሬ ነው።ድርጅቱ በቡልቡላ አካባቢ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12  አስተዳደር ሥር የተመሠረተ ቢሆንም በቂ የሆነ የኢንተርፕራይዞች ሼድ በወረዳው ባለመኖሩ ተቸግሮ ነበር። ይህ ችግር ወረዳው ከቦሌ ወረዳ 13 ጋር በገባው ስምምነት መሠረት ሰዋሰው የቆዳ ውጤቶች የሼድ ተጠቃሚ እንዲሆን ያደረገ ሲሆን ይህም ለሰዋሰው የቆዳ …

ተጨማሪ

የኢንተርፕራይዞችን የገበያ ትስስር ለማሳደግ ኤግዚብሽንና ባዛር ጠቃሚ መሆኑ ተገለጸ

BoJCED-Tamiru-Debela

በኮቪድ ተፅዕኖ ተቀዛቅዞ የነበረውን የኢንተርፕራይዞችን የገበያ ትስስር ለማሳደግ ኤግዚብሽንና ባዛር ጠቃሚ መሆኑን የአዲስ አበባ የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ገለጸ። በ2014 አዲስ ዓመት ዋዜማ ኤግዚብሽንና ባዛር በዐሥራ አንዱም ክፍለ ከተሞች አንድ ሺህ ዐሥር ኢንተርፕራይዞች መሳተፋቸውን በቢሮው የገበያ ልማትና ግብይት ዳይሬክቶሬት ገልጿል፡፡

ተጨማሪ

የምግብ ዝግጅት ሥራ – ቤተልሔም በለጠ ምግብ ዝግጅት

betelhem-belete

ቤተልሔም በለጠ ምግብ ዝግጅት የተመሠረተው በወ/ት ቤተልሔም በለጠ ነው።  የመሥራቿ የምግብ ሥራ ፍላጎት እና የሥራ ልምድ እንዲሁም እውቀት ተድምሮ ድርጅቱን ስትመሠርት ከነበረው አንድ የሰው ሀይል አሁን ለደረሰበት ዐስራ አንድ ሠራተኞች ሊደርስ ችሏል። ወ/ት ቤተልሔም ድርጅቱን ስትመሠርት የነበራት ሀሳብ ጠንክሮ በመስራት ራስን መለወጥ ብሎም ለሌሎች ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ነው።

ተጨማሪ

ዲኤምቲ (DMT) የቤት እና የቢሮ እቃዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር

dmt-sofa-1

ዲኤምቲ (DMT) የቤት እና የቢሮ እቃዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተመሠረተው በ1999 ዓ.ም በአቶ ደረጄ አበራ ሲሆን የተለያዩ የቤት እና የቢሮ አቃዎችን ያመርታል። ከሚያመርታቸው ምርቶች መካከል:- አልጋ ቁምሳጥን የምግብ ጠረጴዛ የቤት በር እና መስኮቶች ሶፋዎች የሶፋ ምርቶቹ ዓይነቶች በሦስት ይከፈላሉ፦ ዝቅተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ የዋጋ ተመን ያላቸው ዝቅተኛ ሶፋዎች ከአስራ …

ተጨማሪ

ማቱት ብዙነሽ እና ጓደኞቻቸው የሕብረት ሥራ ሽርክና ማኅበር

ማቱት፣ ብዙነሽ እና ጓደኞቻቸው የሕብረት ሥራ ሽርክና ማኅበር በአቶ ማቱት ታይሉ እና በሁለት መስራች አባላት 2011 ዓ.ም ላይ ነው የተመሰረተው። የሚያምረተው ምርት የእንጀራ ምርት ነው። ማኅበሩ ሲመሰረት ከነበረው ሦስት አባላት ተነስቶ በአሁኑ ጊዜ ለስድስት ቋሚ እና ስድስት ጊዜያዊ ሠራተኞች የሥራ እድል በመፍጠር እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

ተጨማሪ