ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ አሰፋ ሽምባጋ በ2009 ዓ.ም በግል ኢተርፕራይዝነት ነው። ይህ ድርጅት አጠቃላይ የቆዳ ውጤቶችን በጥራት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያመርት ድርጅት ነው።
ተጨማሪYohannes Teshome
25 ጨረታዎችን በከፍታ ፓኬጅ ተጠቅመን አሸንፈናል – ቤተልሔም አዳነ የጽሕፈት መሣሪያ
ድርጅቱ የተመሠረተው በቤተልሔም አዳነ 2011 ዓ.ም የግል ኢንተርፕራይዝ በመሆን ነው። ይህ ድርጅት የጽሕፈት መሣሪያዎችን እና የፅዳት እቃዎችን በተባለው ጊዜ በጥራት ለተገልጋዮች ያቀርባል።
ተጨማሪአሚጎስ የቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር
አሚጎስ የቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር የተቋቋመው በኢትዮጵያ የኅብረት ሥራ ማኅበር አዋጅ መሠረት በቁጥር 147/1998 ሲሆን ሕጋዊ ሰብእናውን ከአራዳ ክፍለ ከተማ የኅብረት ሥራ ማኅበር ማደራጃ ቢሮ እና ከንግድ ሚኒስቴር በጥር 2005 ዓ.ም. ፍቃድ አግኝቶ በሥራ ላይ ይገኛል። አሚጎስ በቀዳሚነት የሚንቀሳቀሰው የአባላት መደበኛ ቁጠባ እና አክሲዮን በመሰብሰብ የተሻለ የብድር አገልግሎት በማቅረብ …
ተጨማሪቆንጆ ማስታወቂያ
ድርጅቱ የተመሠረተው በ2008 ዓ.ም በወይዘሮ ቆንጂት አይፎክሩም እና በአራት መሥራች አባላት ነው። ድርጅቱ የማስታወቂያ እና ጠቅላላ የሕትመት ሥራዎችን ይሠራል። ይህ ድርጅት በኅትመት ሥራ የስድስት ዓመት የሥራ ልምድ አለው።
ተጨማሪደነቀ፣ ሠናይት እና ቀለሙ የተለያዩ አበቦች፣ ችግኞች ማምረት እና መሸጥ እንዲሁም የገጸ-ምድር ማስዋብ አገልግሎት
ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ደነቀ ጃንጉሌ እና በጓደኞቻቸው በ2006 ዓ.ም ነው። ይህ ድርጅት በገጸ-ምድር ማስዋብ እና በችግኝ አቅርቦት ሥራ የዐሥራ ሦስት ዓመት ልምድ አለው።
ተጨማሪአዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም
አዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም አክሲዮን ማኅበር በአዋጅ ቁጥር 40/1988 ዓ.ም. መሠረት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ በማግኘት በስድስት የአክሲዮን ባለቤቶች የብድርና ቁጠባ አገልግሎት ለመስጠት እ.አ.አ ጥር 27 ቀን፣ 2000 ዓ.ም. በከተማው ያለውን ሥራ አጥነት ለመቅረፍና ድህነትን ለመቀነስ ዓላማ አድርጎ የተቋቋመ ተቋም ነው። በአሁን ሰዓት በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 626/2009 እየሠራ የሚገኝ እና …
ተጨማሪኩል ዲዛይን
እሸቱ እና ሣምሪ ልብስ ስፌት አገልግሎት የተመሠረተው በአቶ እሸቱ ደጉ እና በባለቤታቸው በወ/ሮ ሣምራዊት መሥራች አባልነት በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የልብስ ስፌት ሥራዎችን ይሠራል። የዚህ ድርጅት መስራቾች በልብስ ስፌት እና በፋሽን ዲዛይን ሥራ የዐሥራ ሰባት ዓመት ድምር ልምድ አላቸው።
ተጨማሪግሬስ ኢንጂነሪንግ
ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ተሾመ ደበሌ እና በአራት መሥራች አባላት በ2009 ዓ.ም ነው። ድርጅቱ የሚሠራቸው ሥራዎችን አጠቃላይ የማሽነሪ እና የብረታ ብረት ሥራዎች ናቸው።
ተጨማሪናሆም፣ እሴተ እና ጓደኞቻቸው የኮንስትራክሽን እና የግንባታ ዲዛይን አማካሪ ድርጅት
ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ማርቆስ አሠፋ እና በአራት መሥራች አባላት በ2012 ዓ.ም ነው። ደርጅቱ የኮንስትራክሽን፣ የዲዛይን ሥራዎችን እና ተያያዥ የማማከር አገልግሎቶች ይሠጣል።
ተጨማሪእንደ እናት እንጀራ ማከፋፈያ
የተመሠረተው በወ/ሮ ኤልሻዳይ ተካልኝ በግል ኢንተርፕራይዝነት በ2012 ዓ.ም ነው። ድርጅቱ የሚያቀርበው አገልግሎት የእንጀራ ምርት አገልግሎት ነው።
ተጨማሪ